2 0
Read Time:1 Minute, 37 Second

አቶ የሱፍ ኢብራሂም

አቶ የሱፍ ኢብራሂም “በአማራ ዙሪያ” በሚል ስለድርድሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ እንዳሉት “የትግራይ ብሄርተኝነት ከትህነግ በፊት እንደነበረ ይታወቃል። በትንሹ አራት የትግራይ ትውልዶች “እምበር ተጋዳላይ ትግራይ ….. አምኃራይ …” እያሉ 360⁰ ጨፍረዋል፤ የዘፈኑ መልዕክት (ከግጥሙና ከከበሮው ውጭ) በማኒፌስቶና በህገ-መንግስት ውስጥ ተካቶም ይገኛል።

“ትህነግ ስብስብ ብቻ ሳይሆን የጥላቻ፣ የጥፋት እና የዓሉታዊ ትርክት ምልክትም ነው። የአማራ ህዝብ ግንባር ቀደም የትህነግ ጥቃት ኢላማ ነው።” ሲሉም አጋርተዋል።

አማራ “በሚዲያ፣ በማኒፌስቶ፣ በቻርተር፣ በሕገ-መንግስት፣ በፖሊሲ፣ በድፕሎማሲ፣ በስርዓትና በመዋቅር ጥቃት ደርሶበታል። በመጨረሻም ወረራ ተፈፅሞበታል።” ሲሉ የገለጹት አቶ የሱፍ ቡድኑ በጥቅሉ በአማራ ሕዝብ ትላንት፣ ዛሬና ነገ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ስለማሳደሩ አስፍረዋል።

የአማራ ሕዝብ ትግሉን የሚመራው በኢትዮጵያዊነት ስሜትና ማዕቀፍ ቢሆንም ለረጅም ዘመን የዘር ጥቃት ሰለባ እና የተጎጅ-ተወቃሽ ሲሆን ድምፅ የሚሆነው የተደራጀ ሃይል ባለመኖሩ በማንነቱ ለመደራጀትና ለመታገል ምክንያት እንደሆነው የጠቆሙት አቶ የሱፍ “ይሄ ጉዳይ የቀን ቅዥት የሆነባቸው አካላት መርኅ አልባ ተቃውሞ ሲያሰሙ ይስተዋላል” በማለት አጋርተዋል።

የአማራ መደራጀትና ትግል ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር ያለውን ፋይዳ ጭምር አይገነዘቡም፤ ይሁን እንጅ በኑሮ ተጨባጭ የተረጋገጠን እውነታ ለማስተባበልና ለማሸነፍ አይቻልም ሲሉም አክለዋል።

የአማራ ህዝብ ከትህነግ ጋር በተገናኘ ልዩ ጉዳዬች እንዳሉት እንደማይካድ፣ ይህም በመንግስት ሚዲያዎች ሳይቀሩ በጥለቀትና በዝርዝር ሲዘግብ እንደከረመ አውስተዋል።

“”የአማራ የውክልና ጥያቄ” የአማራ ትግል ተፈጥሯዊ የሆነ ቀጣይ ምዕራፍ ነው!” ያሉት አቶ የሱፍ ከትህነግ ጋር የሚደረገው ድርድር ይዘት በግልፅ ሳይታወቅ፣ ትህነግ የአማራን ሕዝብ በቀጥታ የሚመለከቱ ጉዳዬችን ማንሳቱ እንደማይቀር እየታመነና የፌዴራል መንግስቱ ቢያንስ በመርህ ደረጃ የአንደኛው ክልል ወኪል ሆኖ ለመከራከር እንደማይችል እየታወቀ “የአማራን የውክልና ጥያቄ” በደፈናው ማንጓጠጥና ማውገዝ ሸፍጥ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

ከ30 ዓመታት በኋላ የፌዴራሊዝም፣ የሕገ-መንግስቱና የሉዓላዊነት ባለቤቶች “ብሄር ብሄረሰቦች” እንዳልሆኑ ለመካድ የሚሞክር ካለ የህልም ዓለም ፖለቲከኛ ብቻ ነው ሲሉም ልክ አለመሆኑን አስምረዋል።

የአማራና የአፋር መወከል ለኢትዮጵያ መንግስት ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆነው ማሰቡ የተሻለ እንደሚሆን በመጠቆም ይህም ችግሩ እንደሚባለው በትህነግና በፌዴራል መንግስቱ የስልጣን ሽኩቻ አማካኝነት የተፈጠረ ሳይሆን በሃገር ላይ በተለይም የፌዴሬሽኑ አባል በሆኑ ክልሎች (ሕዝቦች) ላይ ትህነግ ሕገ-ወጥ ፍላጎቱን በጦርነት ለመጫን በመሞከሩ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ለማሳየት ይጠቅማል ነው ያሉት።

በጨረሻም አቶ የሱፍ የአማራ ህዝብ የውክልና ጥያቄ በተጨማሪ ኃይል፣ ተከታታይ ውይይትና ምክክር እየታገዘ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ይህ እንዳይቀጥል የሚያደርገውም አንዳች ምድራዊ ምክንያት እንደሌለ ነው በጽሁፋቸው ያመላከቱት።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator