0 0
Read Time:3 Minute, 50 Second

PDF View

ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በተካሄደ ሴራ እሁድ የካቲት 27, 2014 ሞጣ በጥይት ስትታረስ ውላለች። የአማራ ሕዝብ ዋና ጠላት ብአዴን በምሥራቅ ጎጃም የሞጣን ፋኖዎች በአፈና ትጥቅ እንዲያስፈቱ ባሰማራቸው የከተማው ፖሊስ፣ የአድማ ብተናና የከተማው ሚሊሽያ በከፈቱት ተኩስ የፋኖ አሰልጣኝ የአሥር አለቃ መዝገቡ ሕይወት ተቀጥፋለች። በሕወሃት አፍላ ወረራ ከሥንት የጠላት ጥይት ያመለጠው ጀግናው ፋኖ መዝገቡ ከበአዴን ተከፋዮች በተተኮሰ ጥይት ከተመታ በኋላ ወደባህርዳር ለሪፈራል እየተወሰደ ባለበት ያቆሰሉት አካሎች የሆነኝ ብለው ጨርሰውታል። ሌሎችም የቆሰሉና በእሥር ላይ ያሉም እንዳሉ እየተነገረ ነው። በደቡብ ወሎ ቆቦ አካባቢ በግዳጅ ላይ ላሉ ፋኖዎች መድሃኒትና ቅያሪ ልብስ በመውሰድ ላይ የነበሩ አሥራ አምስት ፋኖዎች የማረኩትን የቡድንና የነፍስወከፍ መሣሪያ ከሕወሃት በብዙ ኪሎሜትር እርቀት ላይ በውርጌሳ አካባቢ በመሸገው የመከላከያ ኃይል እንዲፈቱ ተገደዋል። ክፍለ ጦሩ ፋኖዎቹን አሥሮ አንገላቷቸውም ነበር።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአብይ አህመድ የደህንነት ሹም አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፋኖን ካበሻቀጠና ከዛተበት በኋላ የአብይ አህመድ መንግሥት በደንገጡሩ የአማራ ብልጽግና በኩል ፋኖን ለማጥፋት የደገሰው ድግስ እነሆ በኦፊሴል ተጀምሯል። ቀደም ሲል በየካቲት ወር መግቢያ ላይ በጋይንት ፋኖ ፍትሃለው ወርቅነህና ሌሎች ሃያ ፋኖዎች እጅና እግራቸውን ታሥረው በበአዴን ትእዛዝ ተረሽነዋል። ፋኖን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የክልሉን ልዩ ሃይል ለመበታተን ዕቅድ እንዳለ በቅርቡ ከፍትህ መጽሔት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ ጀ/ል ተፈራ ማሞ አጋልጠው ነበር። የአብይ አህመድ መንግሥት ፋኖን ድራሹን ለማጥፋት ባቀደው መሠረት በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢ ከቀበሌ ጀምሮ መመሪያ ወርዶ ተፈፃሚ እየሆነ ነው። የተጠበቀው መከራ እያስገመገመ ክልሉን እያዳረሰ ነው።
ጀግናው የሞጣ ፋኖ ትጥቄን አልፈታም! እምቢኝ! አሳፈረኝ! በማለት እራሱን እየተከላከለ ወደጫካ እየተመመ ነው። የሞጣ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት ልጆቹን በሚያሳድዱት ላይ ቁጣውን እየገለጠ ነው። በኦሮሞ አማጽያን በቀላሉ ልትጠቃ የምትችለውን ሞጣን የሚጠብቁትን ልጆቿን ትጥቅ ማስፈታት ከአባይ ማዶ ላሰፈሰፉት አማራ ጠል ወራሪዎች በርን ቧ አድርጎ መክፈት እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ተጠቃሚው የአብይ አህመድ መንግሥት ሲሆን፣ ሕወሃትም ከፋኖ መዳከም መጠነ ሠፊ ትርፍ እንደሚያገኝ የሚያክራክር አይደለም።
የአብይ አህመድና የሕወሃት የጋራ አጀንዳ አማራውን አዳክሞ እርስቱን በመከፋፈል የቻሉትን አማራ አጥፍተው የተረፈውን ረግጦ መግዛት ለመሆኑ ባለፉት ወራቶች በተቀናጀ መልክ ከኮረም እስከሰሜን ሸዋ፣ ከጭፍራ እስከደብረታቦር አንዱ ሲያፈገፍግ ሌላው ሲከተል፣ እግረመንገዳቸውንም የመሳሪያ ርክክብ ሲያደርጉ ያወደሙትን ልማትና፣ ያስጨረሱትን ወገናችንን ማየት ብቻ በቂ ነው። ስለሆነም ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት ማለት በጠ/ሚ አብይ አህመድ ሸፍጥና ሴራ ምክንያት ሁሉም እርስቱ ገና ያልተመለሰለትን አማራውን ለሕወሃት ተጨማሪ ወረራ ለማዘጋጀት እንደሆነ ግልጽ ነው።
ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ! ከሕወሃት በተጨማሪ የህልውናህ ጠላቶች የሆኑት ብአዴንና የኦሮም ብልጽግና ልጆችህን ሲበሏቸው ዝም ብለህ ታያለህ ብለን አንጠረጥርም። ልጆችህ ላንተ ሕልውና ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ነው። በቅርቡ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜንና


ደቡብ ወሎ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገው ሕወሃትን ገፍተው አሁን ያለበት አድርሰውታል። ዛሬ በአዴንና አጋሩ የኦሮሞ ብልጽግና ሲያሳድዱት ከጎኑ ልትቆምለት ይገባል። ጠላቶችህን ማሳፈር የምትችለው ከልጅህ ጎን ቆመህ ዛሬስ አበዛችሁት ስትላቸው ብቻ ነው። ብአዴንና ካድሬዎቹ ማንነታቸውን የሸጡት አንተን ልክ እንደጠላቶችህ “ጨቋኝ አማራ” ብለው ከጠሩብህ ጊዜ ጀምሮ መሆኑን አትርሳ!
ጀግናው የአመራ ፋኖ በያለህበት! በአማራ ክልል የትም ቦታ ኑር በጠላቶችህ አይን ያው አማራ ነህ። የሚጠብቅህ ለግንባርህ ጥይት ወይም ለአንገትህ ገጀራ ነው። ሊለያዩህ የሚሞክሩት በመሃልህ ያሉትን ጎጠኞች አትስማ! ያነገብከው አንዱ መርህ “አማራ አንገቱ አንድ ነው” የሚለው መሆኑን አትርሳ። ከውጭ ከመጡት የበለጠ ከማህልህ የወጡት ጠላቶችህ እጅግ የሚያመውን ዱላ እንደሚያሳርፉብህ በበቂ ማስረጃ ያወቅክ ይመስለናል። ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጠን መሣሪያ አላስታጥቅም ያለህ ብአዴን አይደለምን? ስንቅስ አልከለከልህምን? ስትሰለጥን አላሳደደህምን? ሆደሰፊነትና ይሉኝታ ከእንግዲህ ወዲህ ሊያስጠቁህ አይገባም እንላለን! አንተን ክፉ እንዳይነካህ የሚሳሳልህና የሚወክልህ እንዲሁም እስከአሁን ላደረግከው ተጋድሎ ዕውቅና የሚሰጥህ ይቅር አራት ኪሎ ባሕርዳርም የለም። የወገንህ ህልውና፣ የራስህን መጪ እጣ ፋንታና፣ እግዚአብሔር የሰጠህን ሰብአዊ ክብር፤ ከሚጠሉህ
ጠላቶችህ እጅ በልመና የሚለግሱህ ሳይሁን በራስህ የተባበረ ክንድና ትግል እምታስከብረው ነው።
ጀግናው የአማራ ፋኖ ሆይ! የጄ/ል አሳምነው ፅጌ፣ የጎቤ መልኬ፣ ያስቻለው ደሴና የአሰልጣኝ ፋኖ የአሥር አለቃ መዝገቡ ደም የፈሠሰው በከንቱ አለመሆኑን ያንተ በስፋት መደራጀት በቂ ማስረጃ ነው። ይህም ነው የአማራውን ጠላቶች በያሉበት ብርክ ያስያዛቸው። አንተ ትጥቅ የታጠቅከው ለመፍታት አይደለም። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል አርባ ሦስት ዙር ሠልጥኖና ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቆ ከደጀን ማዶ በተጠንቀቅ ቆሞ ትእዛዝ በመጠበቅ ላይ ባለበት ሁኔታ አንተን ትጥቅ ማስፈታት ማለት መልዕክቱ ግልጽ ነው።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የምትኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሆይ! አረመኔውን ሕወሃት ለመጣል ሁላችንም ለብዙ አመታት መስዋዕት የከፈልንለትን ትግል የቀለበሰው ዘረኛው የአብይ አህመድ መንግሥት ዛሬ በፋኖ ላይ የጀመረው ዘመቻ ነገ ወደናንት እንደሚመጣ እንደማትዘነጉ ተስፋ አለን። እንደአበደ ውሻ ሁሉን የሚናከሰው ኦሮሙማ ነገ እናንተን ለመሰልቀጥ ሲመጣ መጀመሪያ ልጆቻችሁን እንደሚበላ እያስታወሳችሁ ዛሬ ከፋኖ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈላችሁና እንዲሁም ባለፉት አራት አመታት በኢዜማ አማላጅነትና በአብይ አህመድ አሳሳች አንደበት የተጠለፋችሁ የዲያስፖራ ወገኖቻችን ሆይ! አብይ አህመድ ከሕወሃት ጋር እየተናበበ ኢትዮጵያን እንደሃገር እያሳጣን ነው። ለዚህም ማሳመኛ የአራት ዓመት ሳይሆን የአንድ ቀን ውሎ ማስረጃ በቂ ነው። አብይ አህመድና ብአዴን በፋኖ ላይ የከፈቱት ዘመቻ ሃገሪቷን አሁን ካለችበት እጅግ ወደከፋ ቀውስ እንደሚያስገባት የሚያከራክር አይደለም። ሰሞኑን እንኳን የአዲስ አበባ ስም እንደሚለወጥና 60% የፌደራል ፖሊስ ኦሮሞ እንደሚሆን ሰምተናል። እንዲሁም የአድዋ የድል በዓል በአድዋ ድልድይ ሥር ብቻ እንዲከበር ተወስኖ ነበር። ተረኞቹ ብዙ የታሪክ ቅርሶች እያወደሙ ነው። ስለዚህ በተለይ በአማራው ህልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ ለማስቆም፣ ሃገራችንን እንደ አንድ ሃገር ለማስቀጠልና ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
የተባበረ ክንድ ያሸንፋል!
የአማራ ህልውና ይከበር!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ/ም
ሰሜን አሜሪካ
2 [email protected] Phone: +1 301 264 5673

ከአማራ-ሕዝባዊ-ኃይል-ፋኖ-የውጭ-ጉዳይ-ኮሚቴ-የተሰጠ-ወቅታዊ-መግለጫ

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator