ከአካባቢው ተወላጅ ለአሚማ የደረሰው የተማጽኖ ደብዳቤ!

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ጸሀፊው በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሞ ወረዳ የተወለደ ሲሆን በአጠቃላይ ቆዬት ያለውንና መፍትሄ የታጣለትን አማራውን የመግደል፣የመዝረፍና የማፈናቀል ሴራን በመፍታት በተለይም በተመሳሳይ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ በሁለንተናዊ ችግር እየተሰቃዩ ለሚገኙ ከ40 ሽህ በላይ ተፈናቃይ አማራዎች እንድንደርስላቸው የተማጽኖ መልዕክቱን አስፍሯል።

ጸሀፊው በመላ ኦሮሚያ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ሳይዘነጋ በዚህ ጽሁፍ በዝርዝር ሊነግረን የፈለገው በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ነው!

የጸሀፊው መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል:_

ዓመታትን ያስቆጠረው ሴራ እና
ሰሚ ያጣው ጭሆት በወለጋ!

የወለጋው ግፍ እና ሰቀቀን
በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ አለም!

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ አዲስ አለም ቀበሌ አማራው ላይ ያለው መቆሚያ ያጣው ግፍ እና በደል!

በዚሁ ቀበሌ ከባለፈው መስከረም ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ የኦነግ ሸኔ መንቀሳቀሻ መሆኑ እየታወቀ በስፍራው ያሉትን የኦሮሞ ማህበረሰብ ካሸሹ በኋላ የነበሩትን የጸጥታ አካላት ከ40,000 በላይ ተፈናቃይ ባለበት ሁኔታ ወዲያው ቦታዉን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ።

ህዝቡም የልዩ ሃይሉን መውጣት ተከትሎ ቢቃወምና ቢማፀንም ሰሚ አላገኘም ነበር።

ይህን ክፍተት በመጠቀም ይኸው ጨፍጫፊ ቡድን ኦነግ ሸኔ መስከረም 28 ቀን 2014 እሁድ ቀን ህዝቡ እየተገበያየ ባለበት ላይ ከተማዉ ዉስጥ በመግባት ንፁሃንን መጨፈጨፍ ጀመረ።

ጭፍጨፋዉን በጣም አስከፊና አሳዛኝ ከሚያደርገው ዋናው ነገር የአማራ ሚሊሾችን ህዝቡን መታደግ እንዳይችሉ ቀደም ብለው ወደ ወረዳ በመዉሰድ በወረዳው አመራሮች መታገታቸው ነው።

ይህ ጭፍጨፋ ከመንግስት አካላት የሎጂስቲክ ድጋፍ እየተደረገለት ኦነግ ሸኔ ያለምንም ማቋረጥ ሳምንታትን የፈጀ ከባድ ጦርነት ሲያካሂድብን የነበረ ቢሆንም አንድም የደረሰ የጸጥታ አካል አልነበረም።

የውጊያው አስከፊነት:_
ይህ ጭፍጨፋ በኦነግ በኩል ወራትን የፈጀ ዝግጅት ነበረው።

ዝግጅትና ሰብስቡም:_ከአቢ ደንጎሮ፣
ከአሙሩ ወረዳ፣ ከጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ፣ ከጊዳ አያና ፣ ከአከዩ ቀበሌ፣ ከሲደንና ኡልማይ ቀበሌ፣ከአጋምሳ ቀበሌ እና ከሌሎች የተለያዩ ቀበሌዎች በመውጣጣት የተፈጸመ ግፍ ነው።

ይኸውም በአራቱም አቅጣጫዎች መሸሽ እንዳይቻል መንገዶችን ጥርቅም አድርገው በመዝጋት ትልቅ ከበባ እና ጥቃት ሲደረግ ያልደረሱ አካላት ዛሬ ፊታቸውን በጨው አጥበው፣ ህጋዊ መስለው ህዝቡን እየታደጉ እየተከላከሉ ያሉትን አካላት ለመበተንና ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው።

እኛ በቦታ ያለነው አማሮች ከፌደራል የበላይ ፍትሃዊ አካል እስካላገኝ ድርስ ሌላማንም ሊፈታልን እንደማይችል ጠንቅቀን እናውቃለን ይላሉ።

ትናንት ስንጨፈጭፍ እጁን አጣጥፎ የተቀመጠ አካል አረ እንዲያውም የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ኦሮሞዎችን ቀድሞ በማስወጣት እኛን በእጅ አዙር ሲያስወጉን የነበሩ አካላት አሁን ላይ ገብተን ካልዳኘናቹህ እያሉን ነው።

አመራሮቹ ጥፋታቸውን ለማካካስና ጥፋተኛ እያሉ ሲፈርጁን እነደቆዩት ሁሉ አሁንም እኛ ጉዳያቹህን ካላየንላቹህ በመከላከያ ትመታላቹህ እያሉ እየዛቱብን ነው ሲሉ ተናገረዋል።

ገለልተኛ የሆነ ከፍተኛ አካል ጉዳዩን ይመለከትልን እንጅ በእነዚህ አመራሮች ድጋሚ በህግ ሺፋን አንበላም ሲሉ ተደምጠዋል የሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች።

ሸኔ ጋር መዋጋትም እርስበርስ ግጭት ይባል ጀመረ እንዴ? “ጂራፍ እራሷን ገርፋ ትጮሃለች” እንደሚባለው እነሱ ሸኔ ጋር ተባብረው ጨፍጭፈውን አማርኛ ተናጋሪ አማጺ ቡድን በማለት ሞታችንንና በደላችንን ቀሙን።

አልሞት ባይ ተጋዳይ ስለሆነ ያደረግነውን የነብስ አድን ትግል በመቆልመም የመንግስት አካላት የእርስ በርስ ግጭት እንጂ ዘር ተኮር አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ (የአሮሚያ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ)።

ያሰሙት የድረሱልን ጥሪ:_
ለመንግስትና ለግል ሚዲያዎች:_

“እባካቹህ እኛ የወለጋ አማራዎች አማራ ሆነን ከመፈጠራችን ውጭ ሌላ ምንም አይነት ወንጀል ሳይኖርብን በማንነታችን ብቻ በደል እየደረሰብን ላለነው ወገኖች ድምጻችንን ለአለም አሰሙልን” ሲሉ ተማጽነዋል።

ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ:-

ባለታሪክ እና አገር ወዳድ ውድ ኢትዮያጵዊያንና ትውልደ ኢትዮጵዊያን እኛ የወለጋ አማራዎች በተለይም ምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ አለም የምንገኘው አማሮች
በህክምና እጦት እየተሰቃዬን ነው፤ በርካቶች ህይወታቸው አልፏል።

እናቶች በወሊድ ምክንያት ሞተዋል፤ ስለዚህ በተቻላቹህ መጠን የሰብዓዊ ድጋፋቹህን ታደርጉልን ዘንድ እንሻለን።

ለመንግስት:_
የሚመለከታቹህ ባለስጣናት በሙሉ ይህ በደላችን በከፍተኛ የፌድራል አካል ወይም በገለልተኛ አካል ይታይልን እንጅ በእጅ አዙር በተደጋጋሚ ያስጨፈጨፈን አካል አላማው ሳይሳካላቸው ሲቀር አሁን እየዛቱብን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ማሰሰቢያ:_
በወለጋ ጭፍጨፋዎች ላይ የመንግስት እጅ አለበት ስንል:_

ጉሊሶ ላይ መከላከያን በአሻጥር አስወጥቶ ማስጨፍጨፉ፤

ሀሮ አዲስ አለም ላይ ልዩ ሃይሉንና የአማራ ሚሊሾችን ወደ ወረዳ ወስዶ ንፁሃንን ማስጨፍጨፍ እና በሌሎች ቦታዎችም በተመሣሣይ በማድረግና ሲጨፈጨፉም ጸጥ ከማለታቸዉም በላይ ለሸኔ የመሣሪያ ድጋፍ እንደሚያርጉ ምርኮኛቹ ተናግረዋል።

ይህ አካል መልሶ እኔው ካልፈረድኩባቹህ እያለን ይገኛል። የወገን ያለ! በህግ አምላክ! ፍትህ!

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator