0 0
Read Time:8 Minute, 4 Second

“…በኤሌክትሪክ ገመድ ግርፋት ደርሶብኛል። በዚህ ምክንያት የግራ ጆሮዬ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የመስማት ችግር ገጥሞኛል፤ ይህም አሁን በህክምና ተረጋግጧል፤ ለዚህም የተሻለ ህክምና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ እንዲሁም ማንነት/ብሄር ተኮር ስድብ ሰድበውኛል፡፡”

ሰለሞን ደሴ እንግዳየሁ_

በእነ ደበበ በሻህውረድ መዝገብ (12 ሰዎች)

በአያያዝ ወቅት የሰብአዊ መብት ጥሰት

ተፈጽሞብናል፤ ይጣራልን በሚል ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታ ካቀረቡት መካከል፣

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)

ሰኔ 25/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ በኩል ከ38 ተጎጅዎች ተሰብስቦ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የተደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍ/ቤቱ በኩል ተቀባይነት አግኝቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዲመረምር እና ሪፖርቱን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የተሰጠበት መሆኑ ታውቋል።

በአያያዝ እና በእስር ወቅት የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል ያሉ በእነ መላክ ምሳሌ መዝገብ የ16 ሰዎችን አቤቱታ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከአሁን ቀደም ማጋራቱ ይታወቃል።

በአጠቃላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል በሚል አቤቱታ ያቀረቡ በ3 መዝገቦች እንዲደራጁ የተደረጉ ግለሰቦች 38 ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል የሁለተኛውን መዝገብ:_

ደበበ በሻህውረድ (12 ሰዎች) ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንዲጣራላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ እንደሚከተለው አጋርተናል።

(1) በእነ ደበበ በሻህውረድ ወንድምኩን መዝገብ፣

12 ሰዎች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንዲጣራላቸው ያቀረቡት የሰብአዊ መብት ጥሰት:_

አቤቱታ አቅራቢዎች:_

1ኛ. ደበበ በሻህውረድ ወንድምኩን፣

2ኛ. ይስሀቅ አይቸው ተስፋዬ፣

3ኛ. ውበት አካል ቢተው፣

4ኛ. ኤርሚያስ መኩሪያ ጓንጉል፣

5ኛ. ንብረት አበጀ አዳሙ፣

6ኛ. ቅድስት ከበደ ሰብስቤ፣

7ኛ. ሰለሞን ደሴ እንግዳየሁ፣

8ኛ. ቢኒያም አለማየሁ ወ/ገብርኤል፣

9ኛ. ዜና ሃይሉ ወልዴ፣

10ኛ. አንዷለም አሻግሬ ጌታነህ፣

11ኛ. ምንይበል ጀግኔ አንተነህ እና

12ኛ. ባሳዝን እርገጤ መንገሻ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ጉዳዩ፡- ከአያያዝ ጋር በተገናኘ የተፈጸመ

የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ እርምጃ

እንዲወሰድ የቀረበ አቤቱታ:_

ተጠርጣሪዎች በ21/09/15 ዓ.ም ለችሎት በፖሊስ ተይዘን በቀረብን ወቅት በተያዝን ጊዜ የተፈጸመብን የሰብዓዊ መብት መደፈርና ጥሰት ለፍ/ቤቱ አቅርበን ችሎቱ ጉዳዩን በጽሁፍ እንድናቀርብ ባለው መሰረት ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን:_

1) ደበበ በሻህውረድ ወንድምኩን:_

የተያዝኩት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ከመኖሪያ ቤቴ ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ እስከ 18/09/2015 ቀን ገላን ሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በዚህም ቦታ ጨለማ ቦታ ብቻዪን አስረውኛል፤ በኤሌክትሪክ ገመድ ገርፈውኛል፤ የግድያ ዛቻ እንዲሁም በረሃብ ቀጥተውናል፡፡

ከባድ ድብደባ ተፈጽሞብኛል በዚህ የተነሳ የግራ ሽንጤ አካባቢ ከባድ ውልቃት ገጥሞኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ ኤ32 ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ ወስደውብኛል፡፡

2) ይስሀቅ አይቸው ተስፋዬ:_

ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ እስከ 18/09/2015 ቀን ገላን ቦታ ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ስያዝ በልጆቼ እና ባለቤቴ ፊት ክላሽ አምጣ እያሉ ከ6 እስከ 8 ሰዓት ደብድበውኛል።

በዚህም ምክንያት የቀኝ ጎኔ ጎድን ጉዳት ደርሶብኛል፡፡

የቀኝ እጄን ከትንሿ ጣት አጠገብ ያለችውን ጣቴን ጥፍሬን ነቅለውታል፡፡

ገላን ከወሰዱኝ በኋላ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ በጨለማ እያስወጡ ባደረሱብኝ ድብደባ የግራ እጄ ትንሿ ጣት ተሰብራለች፡፡

ከፍተኛ ስድብ እና ረሃብ እንዲደርስብኝ አድርገዋል እንዲሁም መድሃኒት ተከልክያለሁ፡፡

…የምኒሊክ እና የቴዎድሮስን ዘር እናጠፋለን በማለት ማንነት ተኮር ስድብ እና ዛቻ ፈጽመውብኛል፡፡

ይህ ቦታ ፖሊስ ጣቢያ አይደለም የመግረፊያ ቦታ ነው ተጠንቅቀህ ቃልህን ስጥ እያሉ እያስፈራሩ ሰድበውኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ 16,800 ( አስራ ስድስት ሺ ስምንት መቶ ብር)፤

የእጅ የብር አምባር እና ማሰሪያው ክር የሆነ የአንገት መስቀል የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እዳሉም አላውቅም፡፡

3) ውበት አካል ቢተው:_

ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በቦክስ ተመትቻለሁ፤ በኤሌክትሪክ ገርፈውኛል፤ ሴራሚክ ላይ እንድተኛ አድርገውኛል እንዲሁም ማንነትን መሰረት ያደረገ የስድብ ጥቃት ተፈጽሞብኛል፡፡

ከ04/09/2015 እስከ 19/09/2015 ድረስ ያለሟቋረጥ ባደረሱብኝ ድብደባ ደም ሲፈሰኝ ነበር፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ 2 ሞባይል ስልክ እና 8,000(ስምንት ሺ) ብር የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

4) ኤርሚያስ መኩሪያ ጓንጉል:_

ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ድረስ ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡ እዚያ በቆየሁበት ወቅት ለብቻዬ መጋዘን ውስጥ አስረው በረሃብ ቀጥተውኛል፡፡

በቆይታዬም ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሰውብኛል፤ በኤሌክትሪክ ገመድ ገርፈውኛል፤ በወረቀት ማስያዣ የጣቶቼን ጫፍ ቀጥቅጠው ጉዳት አድርሰውብኛል።

እንዲሁም አማራን እና ኦርቶዶክስን እናጠፋዋለን በማለት ማንነት/ብሄር እና ኃይማኖት ተኮር ስድብ ሰድበውኛል፡፡

አንተን እንገላለን፤ ልጆችህን ጅብ እናስበላለን በማለት በእኔ እና በቤተሰቦቼ ላይ የግድያ ዛቻ ፈጽመውብኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ መኪና፣ ላፕቶፕ፣ ህጋዊ የተመዘገበ ሽጉጥ እና ሞባይል ስልክ የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

5) ንብረት አበጀ አዳሙ:_

ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡

በቆይታዬ ከፍተኛ ሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሰውብኛል፣ በጨለማ ቤት አስረውኛል፤ በኤሌክትሪክ ገመድ ገርፈውኛል፤ እንዲሁም ማንነት/ብሄር ተኮር ስድብ ሰድበውኛል፡፡ የግድያ ዛቻ ተፈጽሞብኛል፡፡

6) ቅድስት ከበደ ሰብስቤ:_

ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 1፡30 ሰዓት ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡

በቆይታዬ ከፍተኛ ሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሰውብኛል፡፡

3 (ሶስት) ቀን ያለ ምግብ እንድቀመጥ አድርገውኛል፡፡ ወገቤን መትተውኝ በዚህ ምክንያት 13 ቀን ደም እንደ ውኃ ሲፈሰኝ ነበር።…

ለ22 ቀናት ያህል ብቻዬን ሴት እስረኛ በሌለበት ቆሻሻ ቤት ውስጥ ከአይጥ ጋር በማስቀመጥ አስረውኛል፡፡

በድብደባው የተነሳ ማህጸኔ ስለተጎዳ እና በጣም የህመም ስሜት ስለሚሰማኝ የማስታገሻ መድኃኒት እየወሰድኩ ነው፡፡

ከወንድ እስረኞች ጋር ሽንት ቤት እንድጠቀም አድርገውኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ፣ ሽጉጥ ከ8 ጥይት ጋር፣ ፓስፖርት እና መንጃ ፈቃድ የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

7) ሰለሞን ደሴ እንግዳየሁ:_

ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡

በዚህ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ በኤሌክትሪክ ገመድ ግርፋት ደርሶብኛል። በዚህ ምክንያት የግራ ጆሮዬ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የመስማት ችግር ገጥሞኛል፤ ይህም አሁን በህክምና ተረጋግጧል፤ ለዚህም የተሻለ ህክምና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ እንዲሁም ማንነት/ብሄር ተኮር ስድብ ሰድበውኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ 2 ሞባይል ስልኮች፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕ እና ሌዘር ቦርሳ የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

😎 ቢኒያም አለማየሁ ወ/ገብርኤል:_

ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ታስሬ ፌደራል ፖለስ እስር ቤት ካቆዩኝ በኋላ በበነጋታው በ28/08/2015ወደ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡ በዚህ ማጎሪያ ካምፕ ውስት ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውብኛል፡፡

በእጅ፣ በእግር እና በሽቦ ደብድበው ባደረሱብኝ ጉዳት ምክንያት የቀኝ ጎኔ አጥንት የተሠነጠቀ በመሆኑ እስከ አሁን ለመተንፈስ ያስችግረኛል፤ ከፍተኛ የሆነ የህመም እና የስቃይ ስሜት ይሰማኛል፡፡ በዚህ ድብደባ ምክንት የቀኝ ጣት አጥንቴ ወልቋል፡፡ እንዲሁም ማንነት/ብሄር ተኮር ስድብ ሰድበውኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ ጫማ፣ ቀበቶ እና መነጸር የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

9) ዜና ሃይሉ ወልዴ:_

ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፤ ለ13 ቀን በማላውቀው ቤት በጨለማ ውስጥ አስረውኛል፡፡

ከተያዝኩ በኋላ የማያባራ በሽጉጥ እና በአፈሙዝ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡ በረሃብ ተቀጥቻለሁ፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ ሞባይል እና 15,500( አስራ አምስት ሺ አምስት መቶ) ብር የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

10) አንዷለም አሻግሬ ጌታነህ:_

የተያዝኩትግንቦት 5 ቀን 2015 ይዘውኝ እስከ ከ18/9/15 ዓ.ም ምግብ ሳላገኝ እና ከቤተሰብ ተሰውሬ ገላን ማጎሪያ ቆይቻለሁ፡፡

እዚሁ ቦታ በጨለማ ቤት አስረውኛል፤ ከፍተኛ የሆነ ስብዕና የሚነካ ስድብ እና ዛቻ ተፈጽሞብኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ 1 ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ፣ 1 አይከል ስልክ እና ኤቲኤም የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

11) ምንይበል ጀግኔ አንተነህ:_

የተያዝኩት ግንቦት 01 ቀን 2015 ዓ.ም 7 ሰአት ከአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ስራ ላይ እያለሁ አስረው በጋዎን ጨርቄ አፍነው የወሰዱኝ ሲሆን ለ2 ቀን በጨለማ ቤት በማፈን አቆይተውኛል፡፡

ከ2 ቀን በኋላ ከጨለማው ቤት በማውጣት ከማላውቀው ቦታ ለ18 ቀን አቆይተውኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ/ስያዝ 1 ሳምሰንግ ሞባይል፣ መታወቂያ የወሰዱብኝ ሲሆን አሁን የት እንዳሉም አላውቅም፡፡

12) ባሳዝን እርገጤ መንገሻ:_

ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ከአዲስ አበባ አፍነው ወስደውኝ ገላን በሚባል ቦታ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

ከተያዝኩ በኋላ አስከ 18/9/2015 ዓ.ም ገላን ማጎሪያ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡

በዚህ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ በረሃብ ተቀጥቻለሁ፤ ድብደባ እና ማንነትተኮር ስድብ ተፈጽሞብኛል፤

ከ2 ሰአት በላይ በዝናብ እንድደበደብ አድርገውኛል፤ ሽንት በተሸናበት ፍራሽ ላይ እና ባዶ ሴራሚክ ላይ እንድተኛ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ጥሰት ፈጽመውብኛል፡፡

በጊዜው እነዚህ ሰዎች ሲይዙኝ ሳምሰንግ እና ኤቴል ሞባይል፣ ዋሌት፣ ኤቲኤም እና የተለያዩመታወቂያዎችን ወስደውብኛል፡፡

ስለሆነም የተከበረው ፍ/ቤት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት መደፈር እና ጥሰት ላይ የፌደራል ፖሊስ ምርመራ አድርጎ ለችሎቱ ውጤቱን እንዲያሳውቅ እንዲታዘዝልን እናመለክታለን።

ፈጻሚዎቹ አማራ ተኮር የማንነት ጥቃት ያደረሱ ሲሆን ዛቻው ደግሞ:_

አሁን ትዕዛዝ ሰጥተን እናሳርዳችኋለን፤ ኦርቶዶክስን እናጠፋለን፤

ኦሮሚያ አዲስ አበባ ያሉ አማራዎችን በሰአታት እናጠፋችኋለን፤

መንግስቱ የእኛ ፍ/ቤቶች እና ፖሊሶች የእኛ ስለሆኑ እንደፈለግን እናደርጋችኋለን፤

አማራ ካልጠፋ አገሪቱ ሰላም አትሆንም እርምጃ እንወስድባችኋለን በማለት ነው፡፡

የድርጊቱ ፈጻሚ ግለሰቦችና ተቋማት:_

በማንነታችን ምክንት ከሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ በመውሰድ ገላን በተባለ ስውር ማጎሪያ ስፍራ በ12ቱ ግለሰቦች ላይ የአካል፣ የስነልቦና፣ የገንዘብ ጥቃትና ቅሚ በጠቅላላው ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደረሱብን ግለሰቦች እና ተቋማት የሚከተሉት በመሆናቸው ምርመራ እንዲደረግባቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡

ግለሰቦች:_

1) ኮ/ር ኢጃራ…….. የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ኃለፊ፣ …. እያንዳንዷን አፈና እየዞረ

ይከታተል የነበረ፡፡

2) ለሚስ ተስፋዬ……. ምክትል የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ኃለፊ፣

በተመሳሳይ አፈናውን እና አፈሳውን ያስተባብር ይመራ የነበረ፡፡

3) ም/ኢ/ር ኢፋ ( ቁፋ ወይም ኡፋ)……. የፌደራል ፖሊስ አፋኝ ቡድን መሪ:_

3.1 በየቤቱ እየገባ በጨለማ ንብረታችን እንዲወሰድ ምክንያት የነበረ፣

3.2 ማንነት ተኮር ስድብና ዛቻ በማያባራ መልኩ ሲፈጽምብን የነበረ፣

3.3 በእኛ ላይ ኢሰብኣዊ አያያዝ በበላይነት ሲመራ የነበረ፣

4) ተስፋዬ ……… ኦሮሚያ ገላን እኛን 16ቱን ታፋኞች ከተረከበ በኋላ:_

4.1 በ28ቱ ሰዎች ላይ የግፍ ጥግ የሆነ ሰብአዊ ጥሰት የፈጸመብን እና እንዲፈጸምብን ያደረገ፣

4.2 በሁሉም ሰዎች ላይ በማፈራረቅ ድብደባ፣

4.3 በራሀብ እንድንቀጣ እና ቤተሰብ እንዳጠይቀን አድርጓል/ከልክሏል።

4.4 የአካል እና የስነልቦና ስብራት አድርሶብናል።

5.ቦጋለ …….. ተስፋዬ ከሚባለው ጋር በመተባበር እና በመቀናጀት:_

5.1 ጭምብል እና ማስክ በማድረግ ድብደባ ፈጽሞብናል።

5.2 ማንነት ተኮር ስድብ ሰድቦናል።

5.3 መድሀኒት እንዳንወስድ ከልክሎናል።

5.4 ምግብ እንዳናገኝ በረሃብ ቀጥቶናል።

6) ጥላሁን ……..

6.1 ከሁሉም በበለጠ ድብደባ፣ ዛቻ፣ ማስፈራራት እና ማንነት ተኮር ስድብ ፈጽሞብናል።

6.3 ሹጉጥ ግንባራቸው ላይ በመደገን ረሽናችኋለሁ እያለ ሲዝትብን ነበረ ነው።

7.ኢ/ር ረሺድ አብዲ ……. የፌ/ፖ/ወ መርማሪ ሲሆን ገላን ማጎሪያ በማስገባት በሽጉጥ

16ቱ ሰዎች ላይ የማስፈራሪያ ዛቻ ፈጽሟል፡፡

😎 ሌሎች ተባባሪዎች:_

1) ፍቃዱ፣

2) አሸናፊ እና

3) ከበደ የተባሉ ይገኙበታል።

በተቋም ደረጃ:_

1) ብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣

2) የፌደራል ፖሊስ እና

3) የኦሮሚያ ፖሊስ ናቸው።

ስለሆነም የተከበረው ፍ/ቤት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት መደፈር እና ጥሰት ላይ የፌደራል ፖሊስ ምርመራ አድርጎ ለችሎቱ ውጤቱን እንዲያሳውቅ እንዲታዘዝልን እናመለክታለን።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator