0 1
Read Time:5 Minute, 11 Second

Date: 15 May 2023

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራን ዘር በማጥፋት ወንጀል ተጠያቂውን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል!

ህግ አውጭው፣ ህግ   ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው የአማራን ጭፍጨፋ እያወቀ ዝም በማለቱ ተባባሪነቱን ያመላክታል። አሸባሪው ኦነግ እና ኦህዴድ-ብልፅግና በጋራ ለ5 ዓመታት አማራን ሲያሸብሩና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአብይ አህመድ መሪነት እና ሴራ በመቶ ሺዎች ተጨፍጭፈው ፤ ሚሊዮኖችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለው፤ በአገራቸው ስደተኛ ያደረገው የብልፅግና መንግሥት አንድም ለጥያቄና ለፍርድ ሳይቀርብ፤ ከሚሊየን ህዝብ በላይ ያለቀበትንና በትሪሌዮን ብር የሚገመት ተቋማት፤ የአማራ ቤት እና ንብረቱ የወደመበት ጦርነትን ግልፅነት በጎደለው መልኩ ተጣላን፤ ታረቅን አበቃ በማለት በአብይ አህመድና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ማን አለብኝነት ዛሬም የዚህን ህዝብ ደም እንደ ውኃ ያፈሰሱ የዘመናችን ፋሽሽቶችን ለፍርድ በማቅረብ ህዝብ የሰጣችሁን አደራ እንድትወጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን አጥብቀን እንጠይቃለን።  

የአማራ ህዝብ እንደሚታወቀው በመዋቅራዊ ጥቃት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ከጀመረ ከሰላሳ ሁለት አመታት በላይ አስቆጥሯል። ዛሬም መደመር በተባለ የመንግሥት መዋቅር ለ5 አመታት በወለጋ፣ መተከል፣ ሸዋ ፣ ጉራ-ፈርዳ እና በመላው ኢትዮጵያ የመንግሥት ታጣቂዎች የኦሮሞ ልዩ ሃይል ፣ ኦነግ-ሼኔ፣ ኦህዴድ-ብልፅግና ተጣምረው ዘር ማጥፋት እየፈጸሙ ነው። የወልቃይትና ራያ ጥያቄ ባልተመለሰበት፣ የአማራ ህዝብ ከምንጊዜውም በከፋ ሁኔታ አዲስ አበባን ጨምሮ የህልውና አደጋ ተጋርጦበት፤ ህዝባችን በተረኞች እየተገደለ፣ እየተፈናቀለ; ቤት ንብረቱን እየተነጠቀ ባለበት በዚህ ሰዓት በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚባለው ክልሉን የሚመራው የአማራ ብልፅግና በክልሉ ውስጥ ከአማራ ጠላቶች ጋር በማበር ሁሉም አማራ ትጥቁን ፈትቶ ለበለጠ ጥቃት እንዲጋለጥ በማድረግ ማንነቱን አሳይቷል።  የኦነግ እና የህውኃት ኃይል ትጥቁን እያጠናከረና እያዘመነ ባለበት ሁኔታ የአማራ ልዩ ኃይልን ብቻ ማስፈታት እና መበተን ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለውና ከጠላቶቻችን ለይተን የማናየው ስለሆነ የወረዳ እና የቀበሌ የብአዴን አመራር ተወካዮች ከህዝብ ጎን እንድትቆም የመጨረሻ የሆነው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

  1. የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ በማስፈታት እና መለዮ አስለብሶ በምሽት በመላክ ከ65 በላይ ልዩ ኃይል ትዛዛችሁን ተቀብሎ በባዶ እጁ የተንቀሳቀሰውን ምስኪን የአገር ጀግና አስረሽነህ፤ በአስከሬናቸው ላይ የቀለድህ ምርኮኛው ነጋዴ ብርሃኑ ጁላ ሽፍታው ፋኖ ወንድሙን ገደለ ልትለን ሲዳዳህ መስማት ያማል! እንደ እናንተ የእናት ጡት ነካሾች ምስክር ሳያስፈልግ እውነቱ ወጥቷል። በየቦታው የምትገኘው መከላከያ ውስጥ ያለህ የአማራ ልጅ አማራ በመሆንህ ብቻ በየቦታው ከጀርባህ እየተመታህ የወደቅኸው፣ አሰልፈው የረሸኑህ ፣ ዛሬም ለዚሁ እያዘጋጁህ ዝም ብለህ የምትሞትበት ምክንያት የለም እና የእራስህን መንገድ አዘጋጅተህ የህልውና ትግሉን ተቀላቀል። ለአገሩ ለድንበሩ ዘብ ለመቆም ቃለ መሃላውን ፈፅሞ ወደ ስራ የተሰማራውና በሴራ ያስጨፈጨፋችሁት የአማራና የደቡብ ልጆች ደም ዛሬም ይጮሃል። ስለዚህ በየቦታው በዚህ አይነት ሁኔታ ወጥተው የቀሩ ቤተሰቦች ስም ዝርዝር በመሰብሰብ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እንድታዘጋጁ ለመላው ህዝባችን ጥሪ እናቀርባለን።
  • በአዲስ አበባ በህገወጥ አሰራር በግፍና በተረኝነት በማንነታቸው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና ልጆቻቸው የተበተኑባቸው፤ ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቁ ዜጎቻችን ለሞቱት ፍትህ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው የሞራል ካሣ ይቅርታና እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ድጋፍ ተደርጎ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ አስፈላጊው ጥበቃና ዋስትናም እንዲሰጣቸው፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፤ የአፍሪካ መዲና፤ በማንነት ከመጣ ደግሞ ባለቤት ያላት፤ ማንኛውም ሕዝብ በጋራ የሚኖርባት ከተማችንን ከቀማኞች ለመጠበቅ ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ቅርሱንና ከተማውን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።    
  • የአማራ እሴት በሆነው “ሽምግልና” ስም አታሎ በማምጣት ውንብድና የተፈፀመበት ጀግናው አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሤ እና ባልደረቦቹ እንዲሁም ከ35,000 በላይ በግፍ የታሰሩ ፋኖዎች እና ወጣቶች ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ ፣ የአማራ ልሂቃን፣ ማህበራዊ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ አማራነት ወንጀል የሆነባቸው የመንግስት ሠራተኞች የመናገር መብታቸውን በመግፈፍ እንደ ወንጀለኛ በማፈን፤ ማሰር መግደል ማፈናቀል እንዲሁም ንፁሃንን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
  • የአማራን ባለሀብት በማንነቱ ፈርጆ ይህ ተረኛውና ዘራፊው ከመጣ ጊዜ ጀምሮ የገበታ እራት፤ የፓርክ ሥራ እና ኦሮሚያን እናልማ በሚል አጀንዳ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለ5 ዓመታት ኪሳቸውን እና ባንካቸውን አጥቦ ሲጨርስ ያለውን እቃ ለመውረስ የ140 የአማራ ባለሀብቶችን አካውንት ዘግቶ ህዝብን እያስጨነቀና እያመሠ ይገኛል።
  • የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና እና ህወሃት ወንጀለኛ እና አሸባሪነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ አጋር ድርጅቶች መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል፡፡ በህወሃት እና በኦህዴድ መካከል ያለው ልዩነት የሥልጣን ክፍፍል እንጅ በህገ መንግሥታቸው እንዳልሆነ ይታወቃል። እነዚህ አማራ ጠላቴ ነው ብለው የፈጠራ ትርክት ይዘው የመጡ የኢትዮጵያ ነቀርሳዎች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በማፍረስ፣ እምነቶቻችንን በማርከስ አገራችንን አፍርሰው ህዝባችንን አገር የለሽ እያደረገ ያለውን ፅንፈኛ የመንጋ ስብስብ ህዝቡ እንደ ሁልጊዜው በጋራ አምርሮ እንዲታገላቸው ጥሪ እናደርጋለን።
  • አማራ የጀግንነት አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብ ቢሆንም ላለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት በአገር በቀል አሸባሪው መንግሥት ታርዷል፣ ንብረቱ ወድሞበታል ፣ ከኢኮኖሚው፣ ከፖለቲካ ሥልጣን ተገፍቷል። ከመኖሪያው ተፈናቅሎ ፣ የሚመገበው፣ የሚለብሰውን ተነጥቆ በስቃይ ላይ በሚገኝበት ሰዓት የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት ወደለየለት ዘር ማጥፋት ዘመቻውን በአማረኛ ተናጋሪ የኦሮሙማው አራጅ የመከላከያን መለዮ በማልበስ በክልሉ ህዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጆ በከባድ መሣሪያ ህዝብን እየጨፈጨፈ አገራችንን መውጫ ወደሌለው ችግር ውስጥ እያስገባ መሆኑን መላው ህዝባችን ተገንዝቦ አቋም ሊይዝና በቃ እንዲለው ጥሪ እናደርጋለን።
  • በወለጋ የሚኖረው አማራ በገዛ አገሩ የመኖር መብቱ ተገፎ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ አይነት በሺዎች የሚገደሉበት አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪው የንፁሃን እልቂት የቀጠለው መንግሥት ለኦነግ-ሸኔ ሙሉ የትጥቅ አቅርቦት እና መዋቅራዊ ሽፋን ስለሚሰጥ ነው። እርጉዞችን ፣ ህፃናቶችን፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን በመጨፍጨፍ የሚገነባ አዲስ አገር የለም። በመሆኑም መንግሥታዊ ፋሽሽትነት እና ጭፍጨፋን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአስቸኳይ እንዲያስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 
  • የአማራ ህዝብ ልዩ ኃይል እንደ ተቋም በተግባር ተፈትሾ በተሟላ ብቃት ኢትዮጵያን ከውርደት የታደገ ኃይል ነው። የአማራ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ የተቋቋመው በአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ተወስኖ እንደመሆኑ መጠን፤ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ሳይመክርበት እና ህዝብ ሳያውቀው የኦሮሙማው አራጅ የመከላከያን መለዮ በመልበስ ያደረገውን ወረራና የክልሉን ህዝብ ሉዓላዊነት የተጋፋ የህግ ጥሰት ተቀባይነት የለውም በማለት ክልሉን አስተዳድራለሁ የሚለው ብአዴን በአስቸኳይ እርምት ወስዶ ያስገባውን ህገ ወጥ ኃይል እንዲያስወጣና ከአማራ ህዝብ ጋር እንዲማከር እንጠይቃለን።
  • የሃይማኖት አባቶች እና የሽምግልና ወጉን የያዛችሁ የአማራ አባቶች ወንድሞች! ወጉን ማዕረጉን መያዛችሁና ማስቀጠላችሁን ብናከብርም ካለቦታው ሲሆን ግን ባህልና እሴታችንን እያዋረዳችሁና እያጠፋችሁብን ነው። በዚህ አይነት አካሄድ እንደማይቀጥል ከአክብሮት ጋር እየጠየቅን ከአለፈው ብዙ ጀግኖቻችንን ካሳጣን ስህተት ተምራችሁ ከቻላችሁ በአገሩ ተሳዳጅና ተጨፍጫፊ ከሆነው ወገናችሁ ጐን ቁሙ ካልሆነ ለጠላት መጠቀሚያና ተላላኪ ከመሆን ተቆጠቡ እያልን በጥቅም የተገዛችሁ ከዚህ ተግባራችሁ እምንድትታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
  1. በአብይ አህመድ የሚመራው ብልፅግና አቶ ግርማ የሽጥላን ገድሎ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው ፋኖ እና ልዩ ኃይላችን ላይ እጅ በመቀሰርና አማራ ክልልን የጦርነት አውድማ በማድረግ ህዝብን እያሰቃዬ፤ እያሳደደ፤ እያሰረና እየገደለ ነው። ተባባሪውና ምስለኔው ብልፅግና ካድሬ የአገውና የቅማንት ሸንጎ ኦሮሙማውን እየመራ እና መንገዱን እያመቻቼ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግና አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ይህን በህዝባችን ላይ የተደገሰውን ፓለቲካዊ አሻጥር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለማስፈፅም የምትንቀሳቀሱ የዞን፤ የወረዳ፤ የቀበሌ አስተዳደርና ሚሊሻ በወንድሞችህና በንፁሃን ደም መታጠብህን አቁምህ ከአርቆ አሳቢው ህዝብህ ጎን እንድትቆም በጥብቅ እናሳውቃለን። 

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! አንተ ሰላም እንድታድር ጐረቤትህ ሰላም ይደር እንደተባለው አማራ እስከዛሬ ብቻውን ታርዶ፣ ተጨፍጭፎ ፣ በር ተዘግቶ መላ ቤተሰቡ በእሣት ሲጋይ፤ የሰውነት ክብሩን ተነጥቆ ለአፈር ሳይበቃ የትም ሲጣል፣ የቤቴ በር ካልተንኳኳ ብለህ ዝም ያልኸው የአገራችን ህዝብ ሆይ ዛሬ አማራ የመጨረሻው የህልውና ትግል ውስጥ ገብቷል እና አገራችን ወደማይሆን አቅጣጫ ከመሄዷ በፊት በህዝባዊ አመፅ የህልውና ትግሉን እንድትቀላቀል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ይህ የተረኛ መንግሥት አገር የመምራት እና የማስተዳደር ብቃት ስለሌለው፤ ህዝብ አገሩን ለማዳን የሚያምንባቸው አቅምና ብቃት ያላቸውን ሰዎች አሰባስቦ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት እንዲዘጋጅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 

አማራ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ይጎናፀፋል!     

ድል ለአማራ ህዝብ! 

PDF View

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
100 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator