0 0
Read Time:3 Minute, 15 Second

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው መንግስታዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠይቅ ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ፤ በሰልፉ ላይ የተገኙት የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋም “ኑ አብረን እንታገል!” ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በእስራኤል ቴላቪቭ እና በጀርመን በርሊን ግንቦት 26/2014 በድምቀት የተካሄደው በአማራ ላይ የተከፈተውን መንግስታዊ ጥቃት የሚያወግዘው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 27/2014 በተመሳሳይ በዋሽንግተን ዲሲም በተሳካ መልኩ ተካሂዷል።

በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ግልጽ ጥቃት የተወገዘበት ነው።

በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ህዝብ ላይ የቀጠለውን መንግስታዊ ሽብር፣ አፈና፣እስር፣ወከባ፣ እንግልትና መሳደድን የተቃወሙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ይህን የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የዲሲ ግብረ ኃይል፣የተለያዩ የአማራ አደረጃጀቶች፣ ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ እና ሌሎች በወገናችን ላይ የሚሰራው ግፍ መቆም አለበት ብለው የሚያምኑ በአረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቃችን የደመቁ እና ሰንደቁን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈውበታል።

የሰልፉ ዋነኛ አላማም በፋኖዎችና በባልደራስ አባላት፣ በጋዜጠኞች፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በፖለቲከኞች፣ በአክቲቪስቶችና በሌሎች ንጹሃን ወገኖች ላይ የሚደርሰውን እስር ለመቃወም መሆኑ ተገልጧል።

በአማራ ላይ በመንግስት እየተፈጸመ ያለውን ግድያ፣አፈናን፣እስርና ማሳደድን፣ እንዲሁም ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረገውን ዘመቻ ለመቃወም ጭምር ስለመሆኑ ቀደም ሲል ተጠቅሷል።

በህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኙት የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋም “ኑ አብረን እንታገል!” ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

ሰልፈኞች በከፍተኛ ድምቀትና ሞራል አቀባበል ያደረጉላቸው አቶ እስክንድር ነጋ ትግላችን ግቡን ሲመታ በኤምባሲው ላይ በተሰቀለው ኮኮብ ባለው የወያኔ ሰንደቅ አላማ ቦታ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ቀዩን ትክክለኛ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ከፍ አድርገን እንሰቅላለን ብለዋል።

የሌሎች ሀገራት ኤምባሲ ማንነታቸውን በራሳቸው ቋንቋ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲጽፉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን በእንግሊዝኛ ብቻ የጻፈ መሆኑን ለሰልፈኞች በማመላከት አውግዘዋል፤ ይህም በትግል እንደሚስተካከል አስታውቀዋል።

“ፋኖዎች ጀግኖች ናቸው!” ያሉት አቶ እስክንድር ከተከፈተባቸው መንግስታዊ ጥቃት ራሳቸውን መከላከላቸውም ተፈጥሮአዊ መብታቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል።

“ለምነን እስረኞችን አናስፈታም፤ ታግለን እናስፈታለን፤ መብታችንንም እናስከብራለን እንጅ!” ሲሉ ለኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በከፍተኛ ሁለንተናዊ ችግር ላይ ባለች ኢትዮጵያ ውስጥ በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ቤተ መንግስት ለመገንባት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመቃወም ቤተ መንግስቱን ለማንሳት ያስገደዳቸው የያዙት የተሳሳተ የፖለቲካ እሳቤያቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው ሰልፍ ፋኖ ተወድሷል፤ በአንጻሩ የአብይ አገዛዝ በፋኖ፣ በአጠቃላይ በአማራ እና በአፋር ብሎም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ክህደት
የፈጸመ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

በሰልፉ ላይ ከተላለፉት አበይት መልዕክቶች መካከልም:_

1) የዘር ፌደራሊዝም ሀገር ሲያፈርስ እንጅ ሲገነባ አይተን አናውቅም!

2) የባልደራስ አመራሮችና አባላት አሁን ይፈቱ!

ሁሉም በግፍ የታሰሩ ፋኖዎች፣ ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ይፈቱ!

ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ፣ መዓዛ መሀመድ፣ መስከረም አበራ፣ ሰለሞን ሹምዬ፣ ጀኔራል ተፈራ ማሞ እና ሌሎችም ይፈቱ!

3) ንብረቱን ሽጦ ሀገርን የታደገ ፋኖን መግደል፣ማሳደድ፣ማሰር እና ማፈን ይቁም!

ፋኖ የሀገር እና የወገን መከታ እንጅ ስጋት ሆኖ አያውቅም!

ፋኖነት ወረራን እምቢኝ ማለት ነው!
ፋኖነት ሀገርን ከወራሪ ማስከበር ነው!
ፋኖነት ጭቆናን መጥላት ነው!
ፋኖነት ራስን መከላከል ነው!
ፋኖነት አሸባሪነት አይደለም!
ፋኖ ለፍትህ፣ለእኩልነትና ለሰብአዊነት የቆመ ነው!
ፋኖ ህዝብንና ሀገርን ከአሸባሪዎች ከትሕነግ እና ከኦነግ ጥቃት የታደገ ነው!

ፋኖ የሀገር ዘብ ነው!
ፋኖ ትጥቅ አይፈታም!

እኔ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነኝ!
እኔ ፋኖ ነኝ!
ፋኖን እንደግፋለን!

4) የአማራን ደም ማፍሰስ በቃ!
የአማራ ህጻናትን ማረድ በቃ!
የአማራ እናቶችን ማጨናገፍ በቃ!

ንጹሃን የአማራ ዜጎችን መግደል፣ማፈን፣ማሰር፣ማሳደድና ማፈናቀል በቃ!

የአማራን እና የአፋርን ደም ማፍሰስ ይብቃ!

በአማራ ላይ ተደጋጋሞ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ህወሓትንና ኦነግን እናወግዛለን!

በአማራ ላይ የሚፈጸመው ፍጅት በመንግስት፣ በህገ መንግስትና በመዋቅር የተደገፈ ነው!

የአማራ አንገቱ አንድ ነው!
አማራነት ወንጀል አይደለም!

5) ቢመችሽም ባይመችሽም ሸገር ፊንፊኔ አይሆንልሽም!

እኔም አዲስ አበቤ ነኝ!

በአዲስ አበባ ቅርሶችና ታሪክ እየጠፋ ነው!

በኢትዮጵያዊነት ላይ የተከፈተውን ጥቃት እንቃወማለን!

6) በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የተፈጸመውን ድብደባ እናወግዛለን!

7) ድርድሩ የጥቃት ሰለባ የሆኑትን አማራንና አፋርን ካላካተተ ተቀባይነት አይኖረውም!

በወልቃይት፣ጠገዴ፣በራያ እና በሌሎች አጽመ እርስቶች ላይ ከበስተጀርባ የሚደረግ ድርድርን አንቀበልም!

😎 ወላይታን ማሳደድ እና መጨፍጨፍ ይቁም!

9) ትናንት ህወሓት የፈጸመውን ግፍ ያወገዘ ሁሉ ዛሬም የኦህዴድ ብልጽግና በአማራ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ወጥቶ ማውገዝ አለበት!

10) አማራ በአብይ አገዛዝ ተክዷል!

ብልጽግና፣ብአዴን፣ አብይ ገዳይ ነው!

አብይ አሁኑኑ ከስልጣኑ ይውረድ!

መንግስት መሩ የአማራን ዘር ማጥፋት ይቁም!

የኦሮሙማ መስፋትና መንሰራፋትን እንቃወማለን!

“ዴ በል እንዴ! በአማራ ጉዳይ አያገባነም እንዴ? በአፋር ጉዳይ አያገባንም እንዴ?
በአዲስ አበባ ጉዳይ አያገባንም እንዴ?

ግጥም አድርጎ ያገባናል!” የሚሉ እና ሌሎች በርካታ መልዕክቶች ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በእንግሊዝኛም ተላልፈዋል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator