−−−//−−−
ከደባርቅ እስከ ወራቤ የተቀነባበረው የሽብርተኞች በኢትዮጵያ ላይ እሳት የመለኮስ የጥፋት ውጥን…
(ሪፖርታዥ)
በሮቤል ፍቃዱ እና ቤተልሔም ግርማቸው
በሳምንቱ መጀመሪያ በጎንደር ከተማ የተከሰተው የፀጥታ ችግር የከተማው ነዋሪዎችን ጨምሮ ብዙዎችን የጉዳዩ ተከታታዮች ግራ ያጋባ ጉዳይ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ችግሩን ለመፍጠር ጊዜ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ የነ አህመዲን ጀበል ክንፍ የሆነው አክራሪ ቡድን በጎንደር ከተማ እንዳለ የሚታወቅ ቢሆንም ግጭቱ ከተፈጠረ በኋላ የነበረውን ትርምስና ተኩስ በማን እና በማን እንደሆነ ለተወሰኑ ሠዓታት አይታወቅም ነበር፡፡
ማኀበረሰቡ መረጃ ሲያገኝ የነበረው ከማህበራዊ ሚዲያ ስለነበር፣ በማህበራዊ ሚዲያው የነአህመዲን ጀበል ቡድን የበላይነት ይዞ ሐሰተኛ መልዕክቶችን ያሰራጭ የነበረ በመሆኑ ለጊዜውም ቢሆን እውነታው ተጋርዶ ውዥንብር ተፈጥሮ ነበር፡፡
ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ እንዲሉ ባለፉት አምስት ተከታታይ ቀናት በጎንደር የሆነው እውነታ የሚከተለውን ይመስላል፡-
ቅድመ-ግጭት የነበሩ የግጭት መደላድላዊ እንቅስቃሴዎች፡-
በጎንደር ከተማ ለሐሙስ ሚያዚያ 20/2014 በቴዎድሮስ አደባባይ የአፍጥር ፕሮግራም መዘጋጀቱን የሚገልጽ ማስታወቂያ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ሰነበተ፡፡ ጥያቄው የቀረበለት የከተማ አስተዳደሩም ከተማዋ በአሸባሪው ወያኔ እና ቅጠረኛው የቅማንት ኮሚቴ የጥቃት ኢላማ ውስጥ የገባች በመሆኑ፣ ካለባት የፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የአፍጠር ፕሮግራሙ ቀበሌ 17 በሚገኘው በአብዮት አደባባይ እንዲሆን ምላሽ ይሰጣል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመነጋገር ሰኞ ሚያዚያ 17/2014 በከንቲባ ቢሮ የተገኙ የአፍጥር ፕሮግራሙ አስተባባሪ ነን ካሉት ውስጥ፣ ግማሾቹ የቀረበውን ምላሽ አሳማኝነት
1
በሮቤል ፍቃዱ እና ቤተልሔም ግርማቸው
አምነው ሲቀበሉ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ቴዎድሮስ አደባባይ ካላፈጠርን ከተማው ላይ ችግር ይፈጠራል በሚል ማስፈራሪያ አዘል ምላሽ ሰጡ፡፡
ለጎንደሩ የአፍጥር ፕሮግራም ‹27 ረመዳም› በሚል ጁሀር መሀመድ ሀጎስ በሚባል ጎንደር ከተማ በሚኖር የትግሬ ሙስሊም የአድራሻ ስልክ ቁጥሩ 0918 77 41 56 በሚል ፎርም የተሞላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ተከፍቶ ገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ አስቀድሞ ተጀምሯል፡፡
እንደመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ፣ ሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ ከንቲባ ቢሮ በነበረው ውይይት፣ ስብሰባውን እያቋረጡ በመውጣት ስልክ አውርተው የሚመለሱ ሰዎች የነበሩ ሲሆን፤ በወቅቱ የሰጡት ምላሽ ‹ከታላላቆቻችን ጋር እየተመካከርን ነው› የሚል ነበር፡
፡ እነዚህ ሰዎች በውይይቱ መጨረሻ የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ አንቀበልም ብለው የወጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሁሉም የአክራሪው ውሃቢይዝም አስተምህሮ ተከታዮች ከመሆናቸው አኳያ በወቅቱ ስብሰባውን እያቋረጡ ወጥተው ስልክ ያወሩ የነበሩት ከነአህመዲን ጀበል እና ከነሙጅብ ቃሲም ጋር ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የአፍጥር ፕሮግራሙ በአብዮት አደባባይ እንዲሆን መወሰኑን የተቀበሉት ከክርሲያኑ ጋር በአብሮነት የሚያምኑ የነባሩ እስልምና እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡
ከከንቲባ ቢሮ በእምቢተኝነት የወጡት የአክራሪው ቡድን አባላት፣ ቢሮ ላይ በተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት የተነሳ ከክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር ተከባብረን እንኑር በሚል ጽኑ አቋማቸው የሚታወቁትን ሐጅ አደምን ከመስጅድ ሲወጡ ጠብቀው ደብድበዋቸዋል፡፡ ጉዳዩ በሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተይዞ ይገኛል፡፡ ይህ ድብደባ ከዋናው ግጭት አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተፈጠረ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ …
አሁን ብዙ ዝግጅት ወደተደረገበት የግጭት ሴራ ማስፈጸሚያ ቀን ደርሰናል፡፡ ለቀኑም ምክንያት ይፈለግለት ነበር፡፡ ጥሩ አጋጣሚም ተገኘለት፡፡…
ማክሰኞ፤ ሚያዚያ 18/2014
ማክሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ ታዋቂ የሆኑት ሸህ ከማል ለጋስ በፈጣሪ ጥሪ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ቀብራቸው ከሰዓት
በኋላ 7:00 ላይ በሸህ ኤሊያስ መካነ መቃብር ለማከናወን በርካታ ሙስሊም ክርስቲያን በአንድ ላይ ተጉዟል፡፡
በዕለቱ የቀብር ቦታ መረጣ ላይ የሟች ቤተሰቦች የተሳተፉ ቢሆንም፤ አጋጣሚውን የብጥብጥ ማስነሻ ማድረግ የፈለጉ ሰዎች ለቀብር የሚሆን ድንጋይ ፍለጋ በሚል ታላላቆቹ የእምነቱ አባቶች ሳይፈቅዱ በአቅራቢያው ወደሚገኘው መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመሻገር ድንጋይ ማንሳት ይጀምራሉ፡፡
ከእነዚህ ግጭት ፈላጊ ወጣቶች ውስጥ ስድስቱ ከአዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፤ ከሟች ጋር ምንም አይነት ዝምድና እንደሌላቸው የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ በእነዚህ ስድስት ወጣቶች መሪነት አጥር አልባውን ወሰን አልፈው ወደቤተክርስቲኑ ሲዘለቁ፣ በወቅቱ በአቅራቢያው የነበሩ የቤተክርስቲያኑ ሰዎች ድንበር ተሻግረው እንደገቡ በመናገር እንዲወጡ ቢማጸኑም ቀድሞውኑ ግጭት ለመፍጠር አስበው የነበሩት ወጣቶች አካላዊ ፍልሚያ ውስጥ ይገባሉ፡፡ እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ
2
በክርስቲያኖች ዘንድ በሚወደዱት ሸህ ከማል ለጋስ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ በርካታ ክርስቲያኖች የሚገኙ በመሆኑ ታስቦበት የተቀነባበረ ግጭት ነበር፡፡
በዚህ መካከል የቦምብ ፍንዳታ ይሰማል፡፡ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ጉዳይ ቢሆንም ቦንቡ የፈነዳው ከወርዋሪው እጅ ላይ መሆኑን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በዚህ የቦንብ ፍንዳታ ስድስት ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደሆስፒታል በአንቡላስ በሚላኩበት ቅጽበት፣ ቀብር ላይ የነበሩ ወጣቶችን በስሜት በማነሳሳት ቅዳሜ ገበያ ወደተባለ የከተማው የንግድ ማዕከል
አላህ አክበር! በሚል ድምጽ አጅበው ይዘው መጡ፡፡ በዚህ ቅጽበት ቅዳሜ ገበያ ላይ አንዲት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ እናት አንገቷን በገጀራ ተመታት ትወድቃለች፡፡ ይህ ክስተት የጎንደር አርማጊዲዮኑ ማስጀመሪያ እንዲሆን ተፈልጎ የተፈጠረ ስለመሆኑ ኋላ ላይ ማመሳከሪያ ማስረጃዎች ታይተዋል፡፡
አጠቃላይ የአመጽ፣ የግጭትና የብጥብጥ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን በሚያሳብቅ መልኩ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከቅዳሜ ገበያ ወደ አራዳ፤ ከአራዳ ወደፒያሳ የአመጽ ጥሪና ሰልፎች ተዛመቱ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያው ‹ፋኖ የጎንደር ሙስሊሞችን አጠቃ› በሚል ሐሰተኛ መረጃ እንዲሰራጭ ሲደረግ፤ ግጭቱን ወደመሀል ከተማ ለማስገባት ያለሙ ጥቂት እስልምናን የማይወክሉ አክራሪ ወጣቶች ከፊት እየመሩ እስከቴዎድሮስ አደባባይ አደረሱት፡፡
ከዚህ በኋላ በነበረው ክስተት በከተማው ውስጥ የክርሲቲያን የሙስሊም ሳይባል የንብረት ዘረፋ ተጀመረ፡፡ ፒያሳ ላይ የነበረውን ሁኔታ ቋራ ሆቴል ላይ ሆነው የሚቀርጹ የዛውያ ቴሌቭዥን ወኪሎች (የመረጃ ምንጮች) በአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አድማ ብተና ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እዚህ ላይ ግጭቱ በመንግሥት ይፈለግ እንደነበር የሚያሳየው ነገር፣ በርካታ ቤቶች ሲዘረፉ የጸጥታ ኃይሉ ከማስጣል ይልቅ በስልካቸው ካሜራ ትዕይንቱን የሚቀርጹ ሰዎችን እየተከታተለ ይለቅም ነበር፡፡
ቅዳሜ ገበያ የተባለው የከተማው ትልቁ የገበያ ማዕከል አቅራቢያ ላይ በገጀራ አንገቷን ተመትታ የተጣለችው እናት አስከሬን በአካባቢው በፈጠረው ቁጣ አካባቢው ወደአመጽ በመቀየሩ ፒያሳ ላይ ከነበረው ግርግር በከፋ ሁኔታ ቅዳሜ ገበያና አራዳ ላይ የከፋ ሁኔታ ተፈጥረ፡፡
ከንግድ ህንጻዎችና ከመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጥይት በየአቅጣጫው መተኮስ ሲጀምር የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቂና አፋጣኝ ምላሽ አልሰጡም ነበር፡፡ ማክሰኞ ማምሻውን በነበረው ግጭት 12 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7 ሙስሊም፤ 5 ክርስቲያኖች መሆናቸውን ዘግይቶም ቢሆን ከጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል የተገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡ በማክሰኞ ዕለቱ ግጭት ብቻ 92 ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተው ህክምና አግንተዋል፡፡
ጎንደር ከተማ ውስጥ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎበት በተፈጠረው ግጭት፣ መሬት ላይ የነበረው እውነታ ይህ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያው ፋኖን ታርጌት ያደረገ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት በስፋት ታይቷል፡፡ በዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሂደት ውስጥ የኦህዴድ ብልጽግና ሰዎች እጅ እንዳለበት ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ፋኖን የመምታት ፍላጎት የነበረ ቢሆንም ፋኖ በስፍራው በለመኖሩ የታሰበው ሳይሳካ ለሊቱ ተጋመሰ፤ ማክሰኞ ለዕረቡ ዕለቱን አስረከበ፡፡
3
ዕረቡ፤ ሚያዚያ 19/2014
በተጠና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በተቀነባበረ ሁኔታ የተፈጠረው ግጭት ለጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን ለመላ ኢትዮጵያውያን አስደንጋጭና አሳዛኝ ክስተት ነበር፡፡ በማግስቱ ዕረቡ የውሃቢይዝም አስተምህሮ በሚከተሉት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አብሮነት አደጋ ላይ በሚጥሉ የኦሮሞ ጽንፈኛ በሆኑት በነ አህመዲን ጀበል እና ካሚል ሸምሱ የሚመራ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በስፋት ታየ፡፡ በዕለቱ በአዲስ አበባ አንዋር መስጅድ፣ በተጨማሪም ቤተል አካባቢ በሚገኙ ሁለት መስጅዶች ፋኖን የሚወነጅል፣ የአማራ ሕዝብን ከአንድ ኃይማኖት ጋር አያይዞ የሚያጥላላ ፖለቲካዊ መልዕክቶች እንዲተላፉ ተደረገ፡፡
ከጉዳዩ ጋር አንዳችም ግንኙነት በሌለው ሁኔታ ‹አጼዎችን የፈለገ መቃብር ይወረድ› የሚል የተለመደው የኦነጋዊያን ዝማሬ የሆነው የፀረ-ምኒልክ እርግማን አዘል መልዕክት በጩኽት ተራገበ፡፡ እነዚህ አክራሪ ኃይሎች በጎንደሩ ጥቃት 41 ሙስሊሞች
ተገድለዋል፤ ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ በሐሰት መወንጀላቸውን ቀጠሉበት፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ኢምባሲዎች ስለጉዳዩ የተሳሳቱ መረጃዎችን ሪፖርት ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ በዚህ ተሳክቶላቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኢምባሲ 21 ሙስሊሞች በመገደላቸው አዝኛለሁ በሚል የተሳሳተ መረጃ የያዘ መግለጫ ሊያወጣ ችሏል፡፡
ዕረቡ ዕለት በነበረው የመረጃ ግርግር የኦነግ ብሔርተኞቹ እነ አህመዲን ጀበል ተሳክቶላቸው በርካታ ተቋማትን ለጊዜውም ቢሆን አሳስተው ነበር፡፡ በዚህም የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 21 ሙስሊሞች ተገድለዋል የሚል መግለጫ ሲያወጣ፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በበኩሉ 33 ሙስሊሞች መገደላቸውን ገልፆ፤ ሴቶች ተደፍረዋል የሚል ሐሰተኛ ውንጀላም በመግለጫው ይዞ ወጥቷል፡፡
በአጠቃላይ በቀውስ ላይ ቀውስ ለመፍጠር ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ታላላቅ ተቋማትንና ኢምባሲዎችን ሳይቀር በማሳሳት ላይ ተጠምዶ የዋለው የነ አህመዲን ጀበል ቡድን፣ ዕረቡ በነበረው ውሎ የግብጽ ሚዲያዎችን ጨምሮ ለዓረቡ ዓለም ሚዲያዎች ሐሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ውሏል፡፡
ዕረቡ ቀኑን ሙሉ ጎንደር ከተማ ከአንጻራዊ እንቅስቃሴዋ ተገትታ የዋለች ሲሆን፤ ከፒያሳ ጀምሮ ዋነኞቹ የከተማው የንግድ ማዕከላት አራዳ እና ቅዳሜ ገበያ ተዘግተው ውለዋል፡፡ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ልዩ የወንጀል መርማሪ ቡድን ዕረቡ ረፋድ ከባህርዳር ወደጎንደር ከተማ የገቡ ሲሆን፤ ከሠዓት በኋላ ስለቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ሲነጋገሩ ቢውሉም በሆስፒታል ጉብኝታቸው ያገኙት አስከሬን ብዛት 7 የሙስሊም፤ 5 የክርስቲያን በድምሩ 12 ብቻ ነበር፡፡
ከቁጥር ጋር በተያያዘ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱ የተደረሰበት የነ አህመዲን ጀበል ቡድን ቀጣይ ዕቅድ ለሐሙስ የተያዘውን የቀብር ሥነ-ሥርዓት የዳግማዊ ግጭት መነሻ ለማድረግ ከወዲሁ አልሞ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ቀኑን ሙሉ የዋለው የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ማምሻውን ቀለሙን ቀይሮ ለበቀል እጃችሁን አንሱ የሚል የድምጽ ሪከርድ በመቅረጽ ማሰራጨት ተጀመረ፡፡ በኦዲዩ ሪከርዱ ላይ ‹‹… ጎረቤቶቻችሁን እንኳ ቢሆኑ እርምጃ ውሰዱባቸው፤ ይህ የበቀል ጊዜ ነው…›› የሚል አስደንጋጭ መልዕክት በቴሌግራም ቡድኖችና በማህበራዊ ሚዲያው ሲሰራጭ አመሸ፡፡ ‹አማራ ክልል የካፊሮች
4
(ኢ-አማኞች) መገኛ በመሆኑ ክልሉ መፍረስ አለበት› የሚል ግልጽ የፖለቲካ ፍላጎት የተንጸባረቀባቸው መልዕክቶችም አብረው ሲሰራጩ አምሽቷል፡፡
ሐሙስ፤ ሚያዚያ 20/2014
ዕለተ ሐሙስ በግጭቱ ሕይወታቸው ያለፈ ወገኖች የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው የሚፈጸምበት ቀን በመሆኑ ከጥዋቱ 2:00 ጀምሮ
የሰባት ሙስሊም ሟች ወገኖቻችን አስከሬን ከሆስፒታል ወደቀብር ቦታ መጓዝ ጀመረ፡፡
ግጭቱን በመላ ጎንደር ብሎም በአማራ ክልልና በሌሎች ክልሎች የማዛመት የጥፋት ዕቅድ ቀድሞውን የተዘጋጀ በመሆኑ ጎንደር ከተማ ላይ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ለቀብር በወጡበት ሰዓት፣ በደባርቅ ከተማ ጎጥ ማርያም በምትባል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ መጋዝንና ከፊል የቆሎ (የአብነት) ተማሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ ሰው ሰራሽ የእሳት አደጋ ይደርሳል፡፡
እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ይህ እሳት የተለኮሰው በአንድ የእስልምና እምነት በሚከተል ወጣት ሲሆን፤ የእሳት ቃጠሎው በተነሳበት ቅጽበት ሰው ለማጥፋት መሰባሰቡን ተከትሎ አደጋውን ያደረሰው ወጣት በቁጥጥር ስር ውሎ በደቦ ፍርድ እዛው ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ይህን ክስተት ተከትሎ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ወጣቶች ደባርቅ ከተማ ላይ የሚገኝን አንድ መስጅድ አቃጥለዋል፡፡ በከተማው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል በሌሎች የእምነት ቦታዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ በሚል ለጥበቃ በተሰማሩበት ቅጽበት ከመስጅድ በተተኮሰ ጥይት ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተመትተው ወዲውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ አንድ የልዩ ኃይል አባል በጽኑ ቆስሏል፡፡ ከዚህ በኋላ የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ በመውሰድና በቁጥጥር ስር በማዋል ከተማዋን በፍጥነት ማረጋጋት ችሏል፡፡
ይህ አሳዛኝ ክስተት ከጠዋቱ ከ2:50-3:40 ባለው ጊዜ የተከናወነ ሲሆን፤ በዚህ አንድ ሠዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በማህበራዊ ሚደያው ‹‹በደባርቅ ከተማ ሙስሊሞች እየተጨፈጨፉ ይገኛል›› የሚል መረጃ መሰራጨት ጀምሯል፡፡ ይህ መረጃ በርካታ ተከታይ ባላቸው የጎንደር ተወላጅ በሆኑት እነ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን የተሰራጨ በመሆኑ፣ ጎንደር ከተማ ላይ ለቀብር የወጡ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወጣቶችን በስሜት ወደጥፋት ለመግፋት የተጠመደ ፈንጅ ነበር፡፡
በዕለቱ ቀብሩ የሚከናወነው አዲስ አለም ተብሎ በሚጠራው የሸኽ ኤልያስ መካነ-መቃብር ሲሆን፤ በቀብር ጉዞ ላይ የደባርቁ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ እንዲሰራጭ ከመደረጉም በላይ ጎንደር ከተማ ውስጥ ጥቃት ለማድረስ ቀድሞ የተደራጀው ቡድን በተመረጡ ህንጻዎች ላይ የቡድን የጦር መሳሪያ በመጥመድ መተኮስ ጀመረ፡፡
ይህ ድርጊት ዓላማው አንድና አንድ ነበር፤ ይሄውም የተከፈተውን የተኩስ እሩምታ ተከትሎ ቀብሩን ለማስተጓጎልና ለቀብር የወጡ በርካታ ወጣቶች ወደአመጽ እንዲገቡ ለማድረግ ታስቦ ነበር፡፡ ይሁንና ጎንደር ከተማ ውስጥ በሕዝብ ጩኽት በርካታ የጸጥታ ኃይል እንዲገባ ተደርጎ የነበረ በመሆኑ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ምንም አይነት ግርግር ሳይፈጠር ቀብሩ ከቀኑ 8:30 ላይ ተጠናቀቀ፡፡
5
በዚህ ሂደት ውስጥ፣ መሀል ከተማው ቀበሌ 09 ባዕታ ማርያም ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኝ አንድ ህንፃ ውስጥ ብሬን እና ስናይፐር የጠመዱ አልሞ ተኳሾች ከ 4:00 ጀምሮ አካባቢውን በተኩስ መናጥ ጀምረዋል፡፡ በልዩ ኃይል እና በሀገር መከላከያ ሰራዊት ከበባ ውስጥ የገቡት እነዚህ የእስልምናን እምነት የማይወክሉ አክራሪ ኃይሎች ከህንፃው ላይ ሆነው በመተኮስ ሦስት ሕግ አስከባሪ የጸጥታ አባላትን ሲገድሉ፤ ስድስቱን አቁስለዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል ለቀብር የወጣው በአስር ሺህዎች የሚገመት አብዛኛው ወጣት ከቀብር መልስ ወደቤቱ ተጠቃሎ እስከሚገባ ድረስ በመሀል ከተማው ህንጻ ላይ ሆነው የሚተኩሱ አክራሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ
አለመፈለጉን የምንጮቻችን መረጃ ያመላክታል፡፡ እንደምንጮቹ መረጃ፣ ይህ የሆነበት ምክንያት የቀብር ሥነ-ሥርዓቱን በሰላም ለማከናወን እንዲሁም ለቀብር የወጣው ሕዝብ በስሜት ወደአመጽ እንዳይገባ መታገስ አስፈላጊ በመሆኑ ነበር፡፡
ለቀብር የወጣው ሕዝብ ወደየቤቱ መግባት ከጀመረ በኋላ በከተማው ሕግ የማስከበር እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የሚገልጹት ምንጮቻችን፣ በጎንደር ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ብቻ ከ 7 ህንፃዎች ላይ ብሬል ጠምደው መከላከያን እና ልዩ ኃይሉ ላይ ሲተኩሱ የነበሩ አሸባሪዎች ላይ ሕግ የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህ ሕግ የማስከበር ስራ የጸጥታ ኃይሉ ከአሸባሪዎቹ ጋር ከሦስት ሰዓት በላይ የፈጀ ውጊያ አድርገዋል።
ዋነኛው የጦሩ መሪ አብዱ አዱኛ አደም የተባለው ግለሰብ ቀበሌ 12 አባጃሌ ተክለ ኃይማኖት ጀርባ ከሚገኘው የውሃቢያዎች መስጅድ ውስጥ ሆኖ ወደሰላማዊው ሰው እና ወደጸጥታ ኃይሎች ሲተኩስ ካመሸ በኋላ ምሽቱን ቆስሎ ተያዟል፡፡ በዕለቱ
በከተማው ውስጥ የነበረውን የሽብር ጥቃት በስልክ ሆኖ ሲመራው፣ ሲዋጋና ሲያዋጋ የዋለው አብዱ አዱኛ አደም የተባለው የውሃቢያ ታጣቂዎች መሪ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ሌሎቹ የሽብር ቡድኑ አባላት መሪ በማጣታቸው በሂደት እጃቸውን እንደሰጡ የምንጮቻችን መረጃ ያመለክታል፡፡
አብዱ አዱኛ የተባለው የውሃቢያ ታጣቂዎች መሪ በማግስቱ ግልኮሱን ነቅሎ ጺሙን ተላጭቶና ፒጃማ ቀይሮ ከሆስፒታል ሊያመልጥ ሲል መውጫ በሩ ላይ በነበረ ፍተሸ የተሳፈረበት መኪና ውስጥ ከተባባሪ ግብረ አብሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ በአሁኑ ሰዓት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል፡፡
ምንጮቻችን እንዳረጋገጡት ከቀብር መልስ ሀሙስ ሚያዚያ 20/2014 በነበረው ሕግ የማስከበር እርምጃ በጎንደር ከተማ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በኤግዚቭትነት የተያዙ የጦር መሳሪያዎች ብዛትና አይነት የሚከተለውን ይመስላል፡-
➢ 4 ብሬል
➢ 4 ባለእግር መትረጊስ
➢ 6 ስናይፐር
➢ ከ 40 በላይ ክላሽ
➢ ቁጥሩ ያልታወቀ ቦንብ እና በርካታ የጥይት ካዝናዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
6
እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ፣ አብዛኞቹ ይዋጉበት የነበረውን ከባድ መሣሪያ ደብቀው እጅ ሲሰጡ ክላሽ ብቻ ይዘው ወጥተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በነበረው ግርግር በሱዳን መተማ በኩል የጦር መሣሪያ በኮንቴነር ያስገቡ እና ለአክራሪው ኃይል እንዳስታጠቁ የሚጠረጠሩት አህመድ ሀምዛ እና የኮንትሮባንድ አጋሮቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ባደረጉት የጋራ አሰሳ ለተማረኩ ውሃቢያዎች ያስታጠቃቸው እሱ እንደሆነ ጠቁመው አስይዘውታል።
በአራዳ ክ/ከተማ በተለምዶ ቻይና ግቢ ተብሎ በሚጠራው አንድ ግቢ ብቻ 35 የውሃቢያ አክራሪዎች (25 የታጠቀ፣ 10 ጀሌ እና ገጀራ የያዘ) ኃይል በሕግ አስከባሪው ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ሀሙስ ከሰዓት በኋላ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ሁለት ምድብ የነበረው ሲሆን፤ አክራሪ የውሃቢያው ኃይል ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጋር በግልጽ ውጊያ የገጠመ ሲሆን፤ አክራሪው ኃይል በተኩስ ልውውጡ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ሲያደር ታይቷል፡፡
ሀሙስ ዕለት ይህ ሁሉ ክስተት በጎንደር ከተማ ሲከናወን በሌላኛው የሀገሪቱ ክፍል የኃይማኖት ጦርነት ለመክፈት ተፈልጎ ነበር፡ ፡ በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን፤ ወራቤ ከተማ ውስጥ ሦስት የፕሮቴስታንት የአምልኮ ቤቶችን እና አንድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ደርሷል፡፡ የጎራጌ ተወላጅ የሆኑ ቀሳውስት ተገድለዋል፡፡ በንብረት ላይም ወድመት ተፈጽሟል፡፡ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት ተከፍቶ የአንድ ክርስቲያን ሕይወት አልፏል፡፡
በኢትዮጵያ የኃይማኖት ጦርነት ለመቀስቀስ ታልሞ እየተሰራ ለመሆኑ የሚያመላከክተው የነገሮችን ሁኔታ ቀጣጥለን (ፈረንጆቹ the dots concept… በሚሉት መልኩ) ማስተዋል ከቻልን ብቻ ነው፡፡
ይሄውም የሀሙስ ዕለት ድራማዊ ትዕይንቶችን ብቻ ብንመለከት በጎንደር ከተማ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ሐዘንተኞች ለቀብር በወጡበት ሰዓት ደባርቅ ላይ ሙስሊሞች እየተጨፈጨፉ ነው የሚል መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭ፤ ቀብሩ በመከናወን ላይ እያለ በመሀል ጎንደር ከተማ በህንጻዎች ላይ የተደራጁ አሸባሪዎች የተኩስ እሩምታ መክፈት ጀመሩ፤ ከሰዓት በኋላ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተከፈተ… ጥቃቱ በወራቤ
ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ በሚገኙ የክርስትና እምነታ ተከታዮች ላይ ተደገመ፡፡ …ይህ ተራ መገጣጠም ሳይሆን በዕቅድ የተመራ፤ በኃይማኖት ጉዳይ ለሺህ ዘመናት ተከባብሮ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደኃይማኖት ጦርነት የመግፋት የጥፋት ፍላጎት እንዳለ በግልጽ ታይቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዳሜ ሚያዚያ 22/2014 በጎንደሩ ግጭት ሕይወታቸው ካለፉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ውስጥ የሁለቱ አስከሬን ከምህላ በኋላ በአደባባይ ኢየሱስ ተቀብሯል። 3ኛው አስከሬን ወደ ወገራ-እንቃሽ ኪዳነ ምህረት የተባለ አካባቢ ተሸኝቷል። ቀሪዎቹን ሁለት አስከሬኖች መንግሥት ቤተሰቦቻቸው ካልመጡ በሚል ይህ ሪፖርታዥ እስከተጠናቀረበት እሁድ ምሽት ድረስ ሊሰጥ አልቻለም።
7
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ከ375 በላይ ሰዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ አልሞ ተኳሾች ከአዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ እንዲሁም ከስልጤ ዞን የመጡ ሆነው ተገንተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች የአክራሪው ኃይል ክንፍ አባል መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በሕግ ማስከበር ሂደት ውስጥ እርምጃ የተወሰደባቸው አክራሪ ታጣቂ ኃይሎች በመኖራቸው የሟቾችና የቁስለኞች ቁጥር እንደሚጨምር ይገመታል፡፡
የሪፖርታዡ ማጠቃለያ
በጎንደር ከተማ ቀብርን ምክንያት በማድረግ ማክሰኞ ሚያዚያ 18/2014 ከሰዓት በኋላ በተቀነባበረ መልኩ የተነሳው ግጭት
ከመፈጠሩ ቀድሞ (ረፋድ ላይ) ከተማዋን ለቀው የወጡ የአክራሪው ኃይል ሰዎች እንዳሉ መረጃዎች ወጥተዋል። በዚህ መረጃ
መሰረት የጎንደር ከተማ የውሃቢይዝም አደራጅ የሆነውና ዋነኛ የገቢ ምንጩ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ግብይትና ዝውውር (black
market and money loundary) የሆነው ሐጂ እስማኤል አንደኛው ሲሆን፤ ሌሎች ከእርሱ ጋር ከተማውን ለቀው የወጡት
ደግሞ ከ10 ቀናት በላይ ጎንደር ከተማ ሰንብተው ግጭቱን አመቻችተው የወጡ ከአዲስ አበባ የመጡ ሰዎች ይገኙበታል፡፡
ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ መንግሥት በቅርቡ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ተጠርጣሪ ሽብርተኞች ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የታወቀ ነገር የለም፡፡
Pdf view