ዴቭ ዳዊት

ጃዋር መሐመድና ሙጅብ አሚኖ በፈፀሙት ያለመናበብ “ስህተት” የተጋለጠው ሴራ‼

  • ፖለቲካል-ኢስላምና ኦሮሙማ ጋብቻ ፈፅመው በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጀው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ውለው አድረዋል።

አህመዲን ጀበልን፣ ሙጅብ አሚኖንና ቀሪ የአልቃራዳዊ ደቀመዛሙርትን ከፊት አሰልፎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሃይማኖትን ጭምብል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ቡድን የሚፈጥረውን ግጭት ቀስቃሽ የጥፋት ተግባር፥ ለፖለቲካ ፍጆታ capitalize የሚያደርገው የጃዋርና መረራ ድርጅት የሆነው ኦፌኮ ነው።

ይህ ጥምረት፥ በፍኖተሠላም መስጊድ የማቃጠል ዕቅድ ነበረው‼‼ አማራን ለማሳጣት በኦፌኮ የተዘጋጀው መግለጫ ይህንን በፍኖተሠላም ሊፈፀም የነበረን የጥፋት ዕቅድ ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ቢሆንም፥ ጋሪው ከፈረሱ ቀድሞባቸው ሊጋለጡ ችለዋል።

መግለጫው ላይ “በፍኖተሰላም መስጊድ ተቃጥሏል” የሚለው ዐረፍተነገር በድንገት አልያም በስህተት የገባ ሳይሆን፥ መግለጫው በጀበሉና ሙጅብ ክንፍ ሊፈፀም የነበረውን ዕቅድ ታሳቢ አድርጎ ቀደም ብሎ የተዘጋጀና ድርጊቱ አለመፈፀሙን ቢያውቁም መግለጫውን edit ሳያደርጉ ያወጡት ነው።

የኦሮሙማ ሰዎች እንዲህ አይነት ድራማ ሲሰሩ እንደሚዝረከረኩ ደግሞ አብይ አህመድ የብል(ፅ)ግና አመራር ምርጫ ላይ ብአዴናዊው ደመቀ መኮንንን በካልቾ ሊያባርረው አስቦ የመምረጫ አይፓዶቹ ላይ የደመቀን ስም ሳያስገባ ያልተጠቆመን የደቡብ ሰው አስገብቶ ረስቶት ኖሮ በመጨረሻም በአባዱላና ግርማ ብሩ ምክር ደመቀን ሲያስቀጥለው አይፓዶቹ ላይ የገባውን ዴታ edit ባለማድረጉ የውስጥ ሽኩቻቸው እንደተጋለጠ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የኦፌኮም “የፍኖተሠላም መስጊድ ተቃጥሏል” የበሬ ወለደ ሪፖርት፥ ፈረሱ ከጋሪው በመቅደሙ የመጣ እንጂ በድንገት አልያም በስህተት የተፃፈ አይደለም‼‼‼

ዴቭ ዳዊት።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator