የኦሮሚያ ክልል መንግስት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የአማራዎች አዝመራ በጽንፈኞች ሲዘረፍ በዝምታ እየተመለከተ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታዎች እየተነሱበት ነው።

ለሚነሱበት ቅሬታዎችም አይደንቀውም፤ አንዳች ተገቢ ምላሽ እየሰጠ አይደለም፤ ሰብአዊ እርዳታም አያቀርብም ይላሉ ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ቦኒያ ቦሼ ወረዳ የተፈናቀሉ አማራዎች።

“የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአማራ ላይ የለየለት ጥላቻ ባይኖረው ኖሮ
በተለያዩ አካባቢዎች ዓመቱን ሁሉ የደከምንበት ሰብል አብሮ መኖርን በሚጠየፉ ስራ ጠሎች በጉልበት ተቀምተን ሲከፋፈሉት በዝምታ አይመለከትም ነበር” የሚሉት ተጎጅዎቹ በክልሉ መንግስት ገለልተኝነት ላይ ተስፋ ቆርጠዋል።

እንዲያውም ይህ ሁሉ ስቃይ፣ ግድያ እና መፈናቀል በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ብቻ ሳይሆን በክልሉ መንግስት ይሁንታ እና ትብብር እንደሚፈጸም ብዙ ማሳያዎች ያነሳሉ።

ስንቅ እና ትጥቅ የሚያቀብሉ፣ በጅምላ ስንገደል፣ ስንፈናቀል፣ ስንቆስል፣ ህክምና ተቋም ጠፍቶና መንገድ ተዘግቶ ታግተን ስንሞት፣ በረሃብ ጠኔ ስንሰቃይ፣ አዝመራችን፣ ሙሉ ሀብት ንብረታችን፣ የሀገር ሀብት የሆኑ ባንኮቻችን ሲዘረፉ እያዩ እንዳላዩ የሚያልፉት፣ በወንጀሉ ቀጥታ የሚተባበሩት በርካታ የመንግስት አካላትን ለማስተካከል፣ በህግ ለመጠየቅ ያልፈቀደው የክልሉ መንግስት ከድርጊቱ ፈጻሚዎች በምን ይለያል ሲሉም ይጠይቃሉ።

“ቢሮው ክዶናል” የሚሉት ነዋሪዎች ህዳር 10 ቀን 2014 በዋማ ቦኒያ ቦሼ ወረዳ ቢሎ ከተማ የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ አባላት እና በዝርፊያ ተባባሪዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘበኛን በመግደል ባንኩን ሲዘርፉ ለመከላከል አልቻለም ሲሉም ይወቅሳሉ።

እስካሁን የሽብር ቡድኑና በመንግስት መዋቅር የተሰገሰጉ ተባባሪዎቹ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በትንሹ ከ24 በላይ ባንኮችን መዝረፋቸው ቢታወቅም “መንግስት ምን ሰራ? ምን አለ? ታዲያ ይህ የመንግስት አካሄድ ምንን ያመለክታል?” ሲሉም ይጠይቃሉ።

አሁንም የሚቆረቆር ወገን እና የፌደራል መንግስት ካለ ቢያንስ በርሃብ ከምንሰቃይ እና ተረጅም ከምንሆን ዓመቱን ሁሉ የደከምንበት ሰብል በጸጥታ አካል ታጅበን እንዲሰበሰብ ሊያደርግ ይገባዋል ነው ያሉት።

ከቦኒያ ቦሼ ወረዳ ህዳር 1 ቀን 2014 ከሚኖሩበት ቀዬ አማራዊ ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ አዝመራቸውን፣ሀብት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው በግፍ የተፈናቀሉ ተጎጅ “መከላከያም ሆነ ምን እኛን ቢያደራጅና ቢያስታጥቀን አብረን ብንሄድ ተረጅ ሆነን ከምንቀር ብዙ የምናስቀረው አዝመራ አለ፤ አንድ አባዎራ እኮ 400 እና 500 ድረስ ኩንታል በቆሎ የሚያወጣ ነው” በማለት ይናገራሉ።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator