ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ አስኮ አካባቢ በወገን ድጋፍ ቤት ለመከራየት የበቁት አማራዎች ምስጋና አቀረቡ፤ እኛም ዜጎች ነንና መንግስት የት ወደቃችሁ በማለት ድጋፍ ሊያደርግልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ አስኮ አካባቢ በወገን ድጋፍ ቤት ለመከራየት የበቁት አማራዎች ከህዳር 7 ቀን 2014 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ሜዳ ላይ ሆነው ጸሀይ፣ ብርድና ቁር ሲፈራረቅባቸው እንደነበር አውስተዋል።

ከጥቅምት 24 ቀን 2014 ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ከጎቡሰዮ እና ስቡስሬ ሲፈናቀሉ የደረሰባቸውን ዘርፈ ብዙ በደል አስከፊ መሆኑን አውስተዋል።

ከህዳር 29 ቀን 2014 ጀምሮ በጉለሌ ክ/ከታማ ወረዳ 15 በወጣቶች ማዕከል ለአንድ ሳምንት በአስኮ ነዋሪዎችና በወጣቶች የሰብአዊ ድጋፍ ሲደረግላቸው እንደነበር ጠቅሰው የአዲስ አበባን ህዝብ አመስግነዋል።

ህዳር 23 ቀን 2014 ያሉበትን ሁኔታ ለማየት በሚል ከጎናቸው ካልተለዩት መካከል ባንችአየሁ ክንዴ እና ጽየረዳ ቀለመ ወርቅ ከተባሉ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በአስኮ ተገኝቶ ተመልክቷል።

የደረሰባቸውን በደል፣ አሁን ያሉበትን ሁኔታና ለወደፊቱ ያላቸውን ተስፋም ተጋርቷል፤ በጎ ፈቃደኛ ባንችአየሁ ክንዴ በበኩሏ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በተቻለ መጠን ተደጋግፈውና ተቻችለው እንዲኖሩ መክራለች።

አሚማ እንደተመለከተው 47 ከሚሆኑት ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ የወገንን እርዳታ በእጅጉ የሚሹ ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ናቸው።

ከአስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታና መጠለያ በተጨማሪ ህክምና፣ ትምህርትና ስራም ይፈልጋሉ።

በእለቱም ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ከአማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ ጋር በመነጋገር 30 ሽህ ብር ገቢ በማድረጓ እህል፣ ምጣድና አስፈላጊ የመመገቢያ እቃዎችን በመግዛት ሂደት ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል።

ያሬድ የሚባል በጎ ፈቃደኛ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ በተለይም በአረብ ሀገር ያሉ ወንድም እና እህቶች፣ የአማራ ኢመርጀንሲ ፈንድን፣ በጎ ፈቃደኛ የሆኑትን እነ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድን፣ ባንችአየሁ ክንዴ፣ ጽየረዳ ቀለመ ወርቅ፣ ደራሲና መ/ር አስማማው አጥናፉን እንዲሁም በአጠቃላይ ከጎናቸው ያልተለዩ ወገኖችን በሙሉ አመስግነዋል።

የወገን ድጋፍ እንዲቀጥል ያሳሰቡት ተጎጅዎቹ በዋናነት ግን መንግስት እኛም ዜጎች ነንና አስቸኳይ የሆነ የሰብአዊ እርዳታ የምናገኝበትን መንገድ እንዲሁም መጠለያ እንዲያመቻችልን እንጠይቃለን ብለዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator