============= /ክፍል ሁለት/ ==============

================ መግቢያ ==============

በክፍል አንድ ላይ “ኦሮሙማ” የሚለው ቃል ምንጩ የኦሮሞ ብሔርተኛ ምሁራን መሆናቸውንና፥ በጥናታዊ ፅሁፎቻቸውና በመፅሐፎቻቸው ጭምር “ኦሮሙማ” ምን ማለት እንደሆነ በዝርዝር መግለፃቸውን፣ theorize ሲያደርጉትም በአምስት ደረጃ ከፍለው መሆኑን በመጥቀስና ከአምስቱ ውስጥ ሁለቱን በማየት ነበር ያቆምነው።

በዛሬው ክፍል-ሁለት ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ ምሁራን የፃፏቸውን ምንጮች መሠረት በማድረግ ቀሪ ሶስት የኦሮሙማ እርከኖችን እንደሚከተለው እንዳስሳለን። መልካም ንባብ።

  1. ህፅበተ-አዕምሮ የመፈፀሚያ ዕውቀቶች ክምችት ኦሮሙማ / Oromummaa as repertoire of knowledge
  • ናዚዎች በጥላቻ የነቀዘ፥ የዘር ንፅህና /racial purification/ ለመፍጠር ሲነሱ፥ አይሁድን ከከሰሱበትና ካወገዙበት ነገር አንዱ፥ “አይሁዶች ሳይንስንም ይሁን የአብርሆት እሳቤዎችን አቆሽሸዋል” የሚል ሲሆን፥ በአይሁድ “የቆሸሸው” knowledge reservoir መንፃት የሚችለው አይሁዳዊያኑን በአካል በማጥፋትና በናዚ ፍላጎት የተሰፋ Nazi-Science ሲፈጠር እንደሆነ በማመን መፃህፍት ከማቃጠል እስከ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል።

=> በዶክተር አሰፋ ጃለታ አገላለፅ “ሶስተኛ ደረጃው ኦሮሙማ” ተብሎ የተገለፀውም፥ ይህንን ናዚያዊ ፍልስፍና መሠረት አድርጎ የተነሳ ሲሆን፥ ናዚ አይሁዶችን በከሰሰበት ውንጀላ ልክ፥ የኦሮሙማ ስመ-ጥር ideologue የሆኑት እነ አሰፋ ጃለታም “ኢትዮጵያ” በሚል ጭምብል ጋርደው አማራን እንዲህ ሲሉ ይከሰሳሉ፦ “The Oromo people have been chained mentally and psychologically by Ethiopian ignorance, evilness, and darkness that must be smashed by the liberation knowledge of critical Oromo studies, which are based on Oromo indigenous knowledge and human-centric critical knowledge of the world.”
በመቀጠልም፥ የህሊናና የስነልቦና እስረኛ አደረገን ከሚሉት “የአማራ ድንቁርና፣ ክፋትና ጨለምተኝነት” ነፃ ለመውጣት፣ እንዲሁም “forces of unfreedom” ሲል ከሚያብጠለጥለው የአማራ እሴት (value) ለመጥራት (purification)፥ መፍትሔው ሶስተኛው የኦሮሙማ አይነት ማለትም ህፅበተ-አዕምሮ የመፈፀሚያ ዕውቀቶች ክምችት ኦሮሙማ / Oromummaa as a repertoire of knowledge/ እንደሆነ እ.አ.አ ከኦገስት 1 እስከ ኦገስት 2, 2015 ዓ.ም፥ በዋሽንግተን ዲሲው የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በተደረገው 29ኛው የኦሮሞ የጥናት ማዕከል አመታዊ ኮንፍረንስ ላይ፥ “THEORIZING OROMUMMAA” በሚል ርዕስ ባቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ገፅ 21 እና ገፅ 22 ላይ በግልፅ ያትታል።

በአጭር ቋንቋ፥ “repertoire of knowledge” በሚል በእነ አሰፋ ጃለታ የተገለፀው “ሶስተኛው እርከን ኦሮሙማ” ማለት ፥ የናዚ ፍልስፍና መሠረት ከሆኑት የBernhard Foerster እና የ Alfred Rosenberg ስራዎች በቀጥታ የተቀዳ ፋሽስታዊ እሳቤ ሲሆን የፈጠራ ተረቶችንና ታሪክን በመከለስ አዲስ ሀገራዊ የፖለቲካና የታሪክ ትርክት በመፍጠር የፖለቲካ የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ እየሰሩበት ይገኛል‼‼‼

  1. ብሔራዊ ፕሮጀክት ኦሮሙማ፦
  • ኦሮሙማን እጅግ አደገኛ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ፥ ከፋሽስታዊ ጠባብ የፖለቲካ አይዲዮሎጂነቱም በላይ፥ አሰፋ ጃለታ በአራተኛ እርከንነት የገለፀው national project መሆኑን ነው።

“ኦሮሙማ” ፥ National project መሆኑ፥ ልክ እንደማንኛውም ፕሮጀክት በየደረጃው መከናወን ያለባቸው
collection of tasks ያሉት ሲሆን በመጨረሻም የእነዚህ ስራዎች ድምር ውጤት የሚያዋልደው distinctive result ይኖረዋል። ይህም ማለት ዛሬ የምናየው በኦሮሚያ የሚፈፀመው የዘር ማጥራት ያልተቋረጠ ዘመቻ፣ አዲስ አበባን የመሰልቀጥ ርብርብ፣ አጎራባች ክልሎችን Oromonized የማድረግ ስራ ሁሉ የፕሮጀክቱ ፍፃሜ የሆነውን ከተቻለ የኦሮሚያ ሪፐብሊክን አለበለዚያም ኦሮሞናይዝድ የተደረገችውን ኢትዮጵያ ለማዋለድ የሚሰሩ collection of tasks ናቸው።

ይህንን ደግሞ የኦሮሞ የጥናት ማዕከል በሚያሳትመው መፅሔት ቅጽ 14, ተራ ቁጥር 1, 2007 ላይ
“Oromo National Political Leadership: Assessing the Past and Mapping the Future”
በሚል ርዕስ ባወጣው ፅሁፍ ውስጥ “The Concept of Oromummaa and Identity Formation in
Contemporary Oromo Society” በሚለው ንዑስ-ርዕስ ስር እንዲህ ሲል በግልጽ ነግሮናል፦

“Oromummaa is a complex and dynamic national and global project. As a national project and the master ideology of the Oromo national movement, Oromummaa enables Oromos to retrieve their cultural memories, assess the consequences of Ethiopian colonialism, give voice to their collective grievances, mobilize diverse cultural resources, interlink Oromo personal, interpersonal and collective (national) relationships, and assists in the development of Oromo-centric political strategies and tactics that can mobilize the nation for collective action empowering the people for liberation.”

  • የአማራ ፖለቲከኛ ነን የሚሉትም ይሁኑ genuinely የሀገሪቱ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ሰዎች ከጥቂቶች በቀር፥ የየዕለት የኦሮሙማው መንግስት የሚያከናውናቸውን collection of tasks የኦሮሙማ-ፕሮጀክት አካልና የፕሮጀክቱ ፍፃሜ ውጤት የኦሮሚያ ሪፐብሊክ አልያም ኦሮሞናይዝድ የሆነች ኢትዮጵያን የመፍጠር አካል አድርጎ የማየቱ ነገር እምብዛም ነው። ይህ አይነቱ myopic interpretation ያተረፈልን ነገር ቢኖር የፋሽስቶቹ force-multiplier መሆንን እና ፕሮጀክታቸውን ያለተግዳሮት ከግብ እንዲያደርሱ በድንቁርና አልያም በሆድ-አደርነት ተባባሪ መሆንን ነው።
  • ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ቢኖር፥ ብዙሃኑ ለፖለቲካ ቅርብ ነኝ የሚለው ህዝብ ኦሮሙማን ፕሮጀክት አድርጎ ከመቀበል ይልቅ ልክ እንደ ዴሞክራሲ፥ ሂደት /Process/ አድርጎ ከማመን አልፎ ቀድመን የነቃነውን “በለውጥ አደናቃፊነት” ለመክሰስ መጋጋጡ ነው። “ኦሮሙማ” Process ቢሆን ኖሮ፥ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ፥ የ Optimization ጉዳይ ስለሚሆን፥ ገንቢ ሃሳብ በማዋጣትና ጊዜ በመስጠት ነገሮችን እንዲሻሻሉ ማድረግ ይቻል ነበር። የሀገሪቱም ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ አዎንታዊ ለውጥ እያሳየ እንጂ እየከፋ ባልሄደ ነበር።

ነገር ግን የኦሮሞ ideologues በጥናታዊ ፅሁፎቻቸው አስረግጠው እንደነገሩን፥ “ኦሮሙማ” Process ሳይሆን distinctive product (የኦሮሚያ ሪፐብሊክን አልያም ኦሮሞናይዝድ የሆነች ኢትዮጵያን) እንዲያዋልድ በቀመር እየተሰራበት ያለ Project ነው‼‼‼

  1. አለማቀፋዊ ተልዕኮ (Global mission) የሰነቀ አለማቀፍ-ኦሮሙማ (Global Orommuma)፦
  • “ግሎባል ኦሮሙማ” ማለት በአጭሩ፥ ፋሽስት ወያኔ የአማራን ህዝብ በሌሎች ለማስጠላት የሚከተለውን መንገድ መከተል ማለት ነው። አሰፋ ጃለታ “ኢትዮጵያ” በሚል ጭምብል ሸፍኖ “ቅኝ-ገዢ” ባለው አማራ ላይ ሌሎችን እንዴት ማነሳሳት እንዳለባቸው “በግሎባል ኦሮሙማ” ትንታኔው ስር እንዲህ ሲል ፅፏል፦ “Using the philosophy of safuu (moral and ethical order), global Oromummaa promotes horizontal and democratic relations among all the various peoples who have been colonized and brutalized by the Ethiopian colonial state.”
  • “ኦሮሙማ” አለማቀፍ ተልዕኮዬ ብሎ የሰነቀው፥ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን “የአማራ ቅኝ-አገዛዝ የፈጠረብን common historical trauma እና አማራ የሚባል common historical enemy አለን” በሚል sentiment በመቀስቀስ አማራን የመነጠል ስራ ነው።
  • “ኦሮሙማ” ጥላቻን ከመስበክና አማራን አሰይጥኖ ትውልድን ከመመረዝ በዘለለ constructive ideology አይደለም። ለዚህም ነው የኦሮሚያ ሪፐብሊክን የመመስረት ዕድል ቢያገኝ እንኳ አማራን Boogyman አድርጎ Global-Oromumma በሚል ለመቀጠል ዕቅድ ያዘጋጀው። ይህ ደግሞ ከጥላቻ በቀር ለወጡበት ህዝብ አንዳችም ነገር sustainably deliver ማድረግ የማይችሉ Pseudo-ideologies መገለጫ ነው። ሁለት ዓለማቀፍ ምሳሌዎችን እንመልከት።

ከሌኒን ሞት በኋላ በስታሊንና በሊዮን ትሮትስኪ (ወይም በትክክለኛ ስሙ ሌቭ ዴቪዶቪች ብሮንስታይን) መካከል ከነበረው ንትርክ መካከል፥ ትሮትስኪ “ኮሚንዝምን በፍጥነት አለማቀፍ ካላደረግነውና በሶቭየት ብቻ እንዲወሰን ካደረግነው ሲስተሙ dead end ላይ ይደርስና እንፈርሳለን” የሚል ሀሳብ ያቀነቅን ነበር። በእርግጥ የኋላ ኋላ ትሮትስኪን ካስገደለው በኋላም ቢሆን ስታሊንም ሀሳቡን ገዝቶታል። የሆነው ሆኖ በሰባ ዓመት ውስጥ የቱንም ያህል አለማቀፍ ቅርፅ ሊያስይዙት ቢሞክሩም ስርዓቱ dead end ላይ ደርሶ ከስርዓትም በላይ ታላቋን ሀገር ለፍርሰት አጋልጧት አልፏል።

በተመሳሳይ በአያቶላህ ክሆሚኒ የተመራው የኢራኑ theocratic fascism ያንን የመሰለ የስንት ሺህ አመታት ስልጣኔና ጥበብ መፍለቂያ የሆነውን ሀገር በ clergy council ተጠርንፎ እንዲያዝ ከማድረጉም በላይ የህልውናው ማስቀጠያ አድርጎ የሚጠቀመው ፀረ-እስራኤል rhetoricን ነው። በእርግጥ ከቃላትም በዘለለ ራሱን የአለማቀፍ የ Shia shrines የበላይ ጠባቂ፣ የኢየሩሳሌም ነፃ አውጪ አድርጎ ከመስበክ አልፎ በሊባነን፣ ጋዛና የመን ሄዝቦላህ፣ ሀማስና የሁቲ ሚሊሻዎችን አደራጅቶ አሰማርቷቸዋል። በዚህም ሳይወሰን የአያቶላህ አርሚ IRGC አካል የሆነውና Quds የሚባለው expeditionary force ዋነኛ ተልዕኮም በመካከለኛው ምስራቅ የእስራኤልን ከፍ ሲልም የአሜሪካንን ጥቅም destabilize ማድረግ ነው። በነገራችን ላይ የዚህ ኃይል አዛዥ የነበረውና በምዕራቡ ዓለም “The Shadow Commander” በመባል የሚታወቀው ቃሲም ሱሌማኒ (ብ.ጄ/ል)፥ ኢራቅ ባግዳድ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምበሲን በQuds Force እንዲወረር በማድረጉ ምክንያት ትዕግስቱ የተሟጠጠው ዶናልድ ትራምፕ “የይሙት-በቃ” Presidential Order ባሳለፈበት በ24 ሰዓት ውስጥ ነበር እ.አ.አ በጄንዋሪ 03, 2020 ዓ.ም ባግዳድ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በ Drone ጥቃት የተገደለው።

=> ለማንኛውም ወደተነሳንበት ጉዳይ ስንመለስ፥ የሠርቶአደሩን አምባገነንነት /Proletariat dictatorship/ በማንበር Utopian society እገነባለሁ ብሎ አለማቀፍ የመደብ ጠላት በመፍጠር የተንቀሳቀሰውም ስሁት-ርዕዮት ይሁን ለ12ኛው ኢማም ዳግም መምጣት መንገድ ጠራጊ ነኝ በሚል ሃይማኖታዊ ጭምብል የሚንቀሳቀሰው Theocratic fascist ቡድን፥ ከጥላቻና ተቃርኖን ከመስበክ የዘለለ ለህዝቡ deliver የሚያደርገው sustainable development የለውም። ሥርዓቶቹም መቆሚያ መሠረታቸው አለማቀፍ ጠላት ፍለጋ መማሰንና ለአንዳች global noble cause የቆሙ አስመስሎ ለህዝባቸው በመስበክ ብቻ ነው።

ኦሮሙማም በመሠረተ ሃሳብ ደረጃ ከእነዚህ ከመከኑ አስተሳሰቦች የተለየ አይደለም፤ ለዚህም ነው ከፅንሰት እስከ ጉልምስና ድረስ lifeblood ሆኖ ያገለግለኛል ብሎ የተማማለበትን የአማራ ጥላቻ በሌሎች ህዝቦች በማስረፅ ለህልውናዬ መቀጠል ዋስትና ይሆነኛል ሲል Global Orommuma የሚል theorization ውስጥ የገባው‼

  • ስለሆነም እኛ “ኦሮሙማ ፋሽስታዊ አመለካከት ነው” ስንል፥ ራሳቸው የኦሮሞ ብሔርተኛ ምሁራን በእርከን ከፋፍለው ካስቀመጡት ውስጥ መርዘኛ ፖለቲካዊ አጀንዳ የያዘውን በክፍል አንድ ላይ በጠቀስነው ዝርዝር መሠረት ከተራ ቁጥር 2-5 ያሉትን፥ ማለትም፦
  • Nationalist Political Ideology Oromumma
  • “Repertoire of Knowledge” Oromumma
  • National Project Oromumma
  • Global Orommuma ታሳቢ በማድረግ እንጂ፥ ሰፊውና ወገናችን የሆነውን የኦሮሞ ህዝብ ማለታችን ፈፅሞ አይደለም‼‼‼

ራሳቸው የኦሮሞ ልሂቃኑ የተጠቀሙበትን ስያሜ፣ ሀተታና ትንተና መሠረት በማድረግ ላይ ብቻ ተመስርተን ነው እያወገዝን የምንገኘው። ከማውገዝም በላይ ይህንን ፋሽስታዊ አመለካከት በጠላትነት እስከመጨረሻውም እንደምንዋጋው ጠላትም ወዳጅም ሊያውቀው ግድ ይላል‼‼‼

====== የኦሮሙማ ፕሮጀክት እና የአዲስ አበባ ስልቀጣ ====
:
:
:
:
:
:
:

========== በክፍል ሶስት ይቀጥላል =========

ዴቭ ዳዊት።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator