አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ ከባህር ዳር አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ከመድረሷ ታፈነች።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው የአክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል ከባህር ዳር አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ከመድረሷ መታፈኗን ገልጸዋል።
ባለቤቷ አቶ ፍጹም እንደሚሉት ቢሌ አየር ማረፊያ ከመድረሷ ለጥያቄ እንፈልጋለን ያሉ አካላት ወደ ቢሮ ሲወስዷት የተመለከተ የዐይን እማኝ ደውሎ እንደነገራቸው አስታውቀዋል።
በሞባይሉ ፎቶ ለማስቀረት ያደረገውን ሙከራ የተመለከቱ መንግስታዊ አፋኞችም ስልኩን ተቀብለው ያነሳውን ፎቶው እንዳጠፉበት ተነግሯል።
አቶ ፍጹም የ7 ወር ህጻን ቤታ ጥላ የታፈነች ባለቤቴን አድራሻ ንገሩኝ ሲሉ ተማጽነዋል።
በተያያዘ ከሰሞኑ ከአሁን ቀደም ለብልበው በተሰኘው የሙዚቃ ስራዬ በተሳሳተ መልኩ የማይገባቸውን ሰዎች በማወደሴ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለት የለቀቀውን ስራ ከዩቱብ ማውረዱን የገለጸው ድምጻዊ ዳኜ ዋለም መታፈኑ እየተነገረ ነው።