የቀድሞ ሰራዊት አባል አስር አለቃ በላይ ከበደ የመርሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው። የኢፕድ ዘጋቢዎች ዛሬ በከተማዋ ሲያገኛቸው ስሜታቸውን የገለጹት በእንባ እና በሳቅ ታጀበው ነው።

የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ታጣቂዎች በመርሳ ያልፈጸሙትን ግፍ ጠይቁኝና ልንገራችሁ፤ እንደ ሰው ቆመው ይሄዳሉ ይናገራሉ እንጂ ድርጊታቸው ፈጽሞ የሰው አይደለም ነው ያለት አስር አለቃ በላይ።

“የአእምሮ ህሙማንን ‘ለተልእኮ የተቀመጡ፣ መረጃ አቀባዮች ሰላዮች ናቸው’ በማለት በከተማው ያሉ የአዕምሮ ህሙማንን በያሉበት አሳደው ገድለዋቸዋል” ነው ያሉት አስር አለቃ በላይ።

አስር አለቃው የተመለከቱትን የወራሪውን ግፍ ዓይናቸው እንባ ሞልቶት ነግረውናል።

አስር አለቃ በላይ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ሲሄዱ ሰይፈ አሰፋ የተባለ ታማሚ ቤተክርስቲያን ደጃፍ ተገድሎ አስከሬኑን መመልከታቸውን ይናገራሉ። “…ለሞቱት ማልቀስ ስለሚያስገድል በልባችን እያለቀስን ምንም የማያውቀውን ምስኪን ስድስት ሆነን ቀበርነው”።

በቅጽል ስሙ “ዘጭ” ብለን የምንጠራው በየበረንዳው የሚያድር፤ ሠውን ሁሉ አጎቴ፣ አክስቴ ከማለት ውጭ የማይሳደብ ከመንገድ የጫት ገረባ ሰብስቦ የሚቅም፣ ተለማምጦ ሲያገኝ የሚበላ ምስኪን የአእምሮ ህመምተኛም ነበር። ይህንንም ምስኪን ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በጭካኔ ገድለውታል” ብለዋል የዓይን እማኙ።

ሌላው የውጫሌ ከተማ ነዋሪው አቶ ካሳው ተሾመ በበኩላቸው፤ “ይገድላሉ ፣ ያሰቃያሉ ሲሉኝ አራት ልቼንና ባለቤቴን ወደ አዲስ አበባ ሸኘኋቸው። ባለቤቴ አብረን መሸሽ አለብን ብትለኝም ንብረቴን ጥዬ አልሄድም ብዬ ቀረሁ” ብለዋል።

“የመንግስት አመራር፣ የብልጽግና ፖርቲ አባልና ደጋፊ ቤትን ምራ አሉኝ በአካባቢው እንደሌሉ ገለጽኩላቸው። ገንዘብም ፈትሸው አጡ። ቤቱን ከማፈራረሳችን በፊት ብር አምጣ በማለት ለአምስት ቀናት አስረው ቀጥቅጠው አሰቃይተውኛል። በዱላ ብዛት አንድ ጆሮዬ መስማት አቁሟል።ገድለነዋል ብለው ነው ጥለውኝ የሄዱት አስተሳሰባቸውና ተግባራቸው የአውሬ ነው” ሲሉም ለዘጋቢዎቻችን ተናግረዋል።

አቶ ካሳው “በብድር የገነባሁትን ሆቴል አውድመውብኝ ባዶ እጄን አስቀርተውኛል። ያም ሆኖ ህይወቴ ስለተረፈ ተመስገን እላለሁ” ሲሉም ነው ያጫወቱን።

የመርሳ ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ እናኑ ገበያው በበኩላቸው፤ ወራሪው ሀይል በከተማዋ በቆየባቸው ወራት ንጹሃንን የአብይ ደጋፊ ናችሁ በማለት መግደሉን፣ በየቤቱ በመዞር ዝርፊያ መፈጸሙን ተናግረዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator