0
0
Read Time:38 Second
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
በደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ አሪ ወረዳ የአማሮች ቤቶች እየተመረጡ ተቃጥለዋል።
ቃጠሎና ዘረፋው ከ18 ቀናት በፊት የጀመረ ሲሆን ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን በወረዳው ከቶልታ ቀበሌ ተፈናቅለው በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የተጠለሉ አማሮች ተናግረዋል።
በጅንካ የሚገኙ የአማሮች የንግድ መደብሮች ማለትም የጣቃ ልብስ ሱቆችና ሆቴሎች ተዘርፈዋል፤ ተቃጥለዋልም።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ፣ ከ150 በላይ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በርካታ ኗሪዎችም ተፈናቅለዋል።
በአካባቢው የፖሊስ አባላት ቢኖሩም ሕዝቡን ከጥቃት አልተከላከሉም።
ጥቃቱን እየፈፀሙ ያሉት ራሳቸውን ‘ሸከን’ ብለው የሚጠሩ የአሪ ብሔረሰብ ጥቂት ወጣቶች መሆናቸውንም ያነጋገርናቸው ተጎጅዎች ተናግረዋል።
ከጥቃቱ ጀርባ የአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበትም ጠቁመዋል። ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ጠመንጃ፣ በገሚስ ደግሞ ጦር እና ጩቤ የታጠቁ ናቸው።
በአካባቢው ካለው ኗሪ መካከል ከፍተኛ ቁጥር ከሚሸፍኑት መካከል አማሮች ይገኙበታል ያለው ባልደራስ ነው።
About Post Author
Admin
Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF.
ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።