0 0
Read Time:4 Minute, 53 Second

ዶ/ር ጥላሁን
የአማራ ሕዝብ ከሚደርስበት ሰላሳ ዘመን ያለፈ እጅግ ዘግናኝ ግፍ፤ ዘር ማጥፋት፤ጅምላ ጭፍጨፋ ስደት: መፈናቀል ወዘተ.. ከሲአል እስከ ምድር ያሉ የመከራ ጥጎች ሁሉ ተፈራርቀውበታል::
በቅድሚያ ትሕነግ በምትባል እኩይ ቡድን ትግራይ ደደቢት በረሃና ዋሻ እንደ እባብ ካብ ስር ጠንሥሰው በበጠበጡት የአጥፍቶ ማጥፋት መርዝን ሰይጥነው የጥላቻ መርዙንና የመከራ ገፈቱን ሲግቱት ኖሩ::
በየደረሱበት ጎጥ ሁሉ በየአምሳያቸው የቀፈቀፏቸው የእንግዴ ልጆችና ጋሻ ጃግሬዎቹ (ኦነግና፤ኢድሃን(ብአዴን)ን እየፈለፈሉ በአንድ ሕዝብ (አማራ) ላይ ፍጹም ጥላቻ በማስረፅ የሹመታቸውና የኃልውናቸው መነሻም መዳረሻም አድርገው እነሆ በመሰረታት ሀገሩ እንደ ክፋ አውሬ ለሰላስ አመት በተገኘበት ሁሉ እየተሳደደ በጭካኔ እንዲጨፈጨ አደረጉት::
ኢሕአደግ ብለው በመንግሥትነት በጉልበት እራሳቸውን ካሰፈኑበት ጊዜ ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ጭፍጨፋው፤የግፍ ግድያው ማፍናቀሉ፤ ጅምላ ፍጅቱ በኢትዮጵያ አራቱም ማዕዘናት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ተጠናክሮ ይፈጸማል።
• በበድኖ፤ ባሌ፤ ጉራፋርዳ፤ወለጋ፤ አርሲ. ወለጋ፤ በቤንሻንጉል ወዘተ:: https://youtu.be/PA7k2iuGr4U
ይኸ የመከራ ዝናብ በመጨረሻም የሕዝብ የቁጣ ማእበል አስነስቶ ከ27 አመት የሰቆቃ ዘመን በኋላ የተፈጠረውን ለውጥ አሻፈረኝ ብላ ወያኔ እትብቷ ወደተቀበረበት ትግራይ ምድር ተጠቃላ ገብታ ቆየች::
ይሁንና የተካነችበትን አገርና ሕዝብን የማጥፍት ሴራ ሙሉ ጊዜዋን ልምዷን ተጠቅማ እንድታከናውን በምትኳ የሥልጣን ኮርቻ ቋምጦ የተቆናጠጠውን የተረኛውን የኦሕድድን እውቅናና ፈቃድ ያገኘች ይመስላል፤ቀለብ እየተሰፈረላት እንድትጠናከር ጊዜና እድል ተሰጣት:: አዘናጊው የአብይ መንግሥትም ኢትዮጵያ ከፍ ትላለች፤ጨረቃ ላይ ትወጣለች፤አሜሪካን ዘቅዝቃ ታያለች ይለን ጀመር::
ያዞረብንን ‘አዚም’ እንጃ? አፍዞ አደንግዞ አንዴ የቤተ መንግሥት ማስዋብ ሥራ ተጠምጃለሁ ብሎ አንድ እራት እስከ አምስት ሚሊዮን የመሸጥ ማጅኩን ሲያሳየን፤ሌላ ጊዜ በችግኝ ተከላ አገራችንን በደን ሸፍኖ ድንቅዬ አርዊቶችን በጥንት ዘመን የጠፍትን የ ‘ዲያኖሶርስ’ ዝርያ እመልሳለሁ እያለ ሲያነሆልለን ባጀ::

ጭራሽ የአለም መንግሥታትም የአመቱ እውቅ ሰው ብለው ኖቬል ሸልመውልን አረፍት፤ መቸም የተመከረብንን አናውቅ፤ ክብር መስሎን አጨበጨብን መልሶ እጃችንን በቆረጠን ብንልም።
በዚህ ሁሉ መሃል ግን ፍጅቱ ግድያው ማፈናቀሉ በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ ተጠናክሮ ቀጠለ፤ መንግሥትና ወያኔ፤ኦነግ በቅንጅት እንዲሚፈጽሙት በሚያሳብቅ መልኩ።
• ወለጋ፤ናዝሬት፤ሻሸመኔ፤ዝዋይ: አጣዬ…. በይዘትና በስፋት እየስፋ እየከፋ ቀጠለ፤
ፅንፈኞች ሎተሪ ወጣላቸው፤ባንክ ዘርፈው፤ከተማ አውድመው፤ የአማራን ሕዝብ ጨፍጭፈው የሚጠይቃቸው የለም:: እንዲያውም ‘አሸባሪዎቹ’ ከአገሪቱ ሪፐብሊካን ጋርድ ከሚታጠቁት እጅግ ውድና ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቀው ምስኪን አማራውን በጅምላ ምጥአት ያወርዱበት ጀመር፤ይኸ ሁሉ ሲሆን የአብይ መንግሥት ትንፍሽ አይልም እርሱ አበባ ሲተክል፤ ውሃ ሲያጠጣ፤ መንገድ ሲጠርግ፤ፎቶ እየተነሳ ይለጥፍልናል:::
የሚፈፀመው ወንጀል እየሰፍ መጣ፤ሙሉ ከተማ ሲወድም የፌደራል መንግሥትም እንዳልባሌ፤እንዳልሰማ በዝምታ ከማለፍ ጀምሮ በመዋቅሩ ባሉ ባለስልጣናት ጭምር ሲፈጸም ተባባሪ ሆኖ ወይም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፤የአማራ ክልል መንግሥትም ቢብስ እንጅ የተሻለ ነገር አይታይበትም እንዲያውም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በማበር ለአማራሕዝብ ተቆርቁረው ጥያቄ የሚያነሲቱን: በደሉን ግፉን የሚያጋልጡትን በርትቶ ማሳደድና ማዋከብ ዋና ሥራው አድርጎት ቀጠለ ችግሩን ተጋፍጦ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ::
ብርቅዬ ፋኖዎችን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ሄዶ በመግደል እንዲህ ለጭንቅ ቀን የሚሆኑ ጀግኖቻችንን በከንቱ አጣን ጠላት ተሳለቀብን።
በሌላ በኩል ትሕነግ በጥጋቧ ወም በወጠነችው የመከራ ድግስ መሰረት ከፌደራል መንግሥቱ ተነጥላ በአማራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ማዕበል ልታዘንብ ከአቅም በላይ ስትዘጋጅ፤ብሎም አሁን የቀጥታ ወረራና የሂሳብ ማወራረድ ዘመቻ ስትፈጽም የአማራ ክልል መንግሥት ምንም ዝግጅት ሳያደርግ ሕዝቡን አጋፍጦ ጠበቃት።
ለጡት አባታቸው የገቡትን ቃል ኪዳን ማን ያውቃል??
ይባስ ብሎ ትህነግ የአማራ ክልል በየመዋቅር ባሉ ካሃዲ ባለሥልጥናትን ተጠቅማ እንደሆነ አሁን እየተከፈለ ባለው ከፍተኛ መሥዋዕትነትና እልቂት በኋላ ከከፍተኛ የጦር መኮንን እስከ የፓለቲኪኛ ሹመኞች ለወያኔ መረጃ በማቀበለ፤ከኋላው በማስወጋት

በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከተማውን በማስለቀቅ፤ያለምንም ተቃውሞ ከተማ እንዲወረር በማድረግ ሃብት ንብረቱን በማስወደም የአማራ ሕዝብ በችግር እንዲማቅቅ አብረው ተባብረው በማስደብደብ ወገናቸውን ለጠላት እንደ ይሁዳ በጥቅም አሳልፈው ሽጠውታል::
በመጀመሪያ ብልጽግናና ትሕነግ ባላቸው የስልጣን ሽሚያና ፉክክር ባስነሱት አምባጓሮና ከዚያም የሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የሕግ ማስከበር የስምንት ወር ዘመቻ (የመጠፋፋት ውጊያ) በኋላ እልባት ሳያገኝ ለትግራይ ሕዝብ የእፎይታና የጥሞና ጊዜ ደግሞም የእርሻ ጊዜ እንስጠው በሚል ‘ስልታዊ ማፈግፈግ’ ስም ወያኔ የበለጠ ጊዜ አግኝቶ ተደራጅቶ የፈረደበትን የአማራን ሕዝብ በድጋሚ ይፈጅ ዘንድ እንደተፈረደበት ግልጽ እየሆነ የመጣው የሀገሪቱን ከባድ መሳሪያ የታጠቀ የመከላከያ ሰራዊት እንደ ዱቄት በአየር ላይ ትህነግ ተበትናለች በጋንታም መደራጀት አትችልም የተባለችው ትህነግን ሳይከላከልና ሳይመክት በፍጥነት እየሸሸ የአማራን ሕዝብ የበቀል ሰይፏን ታሳርፍበት ዘንድ ‘መንግሥታችንና ሰራዊታችን’ የተናጥል ተኩስ አቁም ላይ ነኝ በማለት እልቂቱን በባይታወርነት ታዝቧል፤ እንዳንንዴም ከጀርባ የአማራን ሕዝብ ወግቷል፤ ተብሎ ይጠረጠራል::
እጅግ ልብ ይሚያደማው ደግሞ አማራ ክልል ስትራቴጅክ ተራሮች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ተክሎ/ አስቅምጦ የሚያስጠብቀው በአማራ ሃይሎች ነበር!! በመጀመሪያ ዙር ትህነግ ወረራ ባሃርዳርና አንዳንድ የአማራ ከተሞች በሮኬት የተመቱት ከነዚህ ቦታዎች በሚተኮሱ ነበር ይባላል፤አሁንም የሰሜን ወሎ ከተሞች ወልድያን ጨምሮ የተደበደቡት ከነዚህ ምስጥራዊ ቦታዎች መሆኑ ተረጋግጧል::
መከራውን ሆን ብለው ያከበዱበት የብአዴን ባንዳ አመራሮች መሆናቸውን የሕዝባዊ ኃይሎች እጅግ አምርረው ተናግረዋል፤አስጠንቅቀዋልም፤
• ልብ ያለው ልብ ይበል! የሚሰማ ይስማ!
• ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መግደል ባንዳ ባንዳውን ነው!! https://www.facebook.com/100040269544694/posts/561065671912413/ ?d=n
ሌላው እጅግ ልብ የሚያደማው የክልሉ መንግሥት ያደረገውን የክተት አዋጅና የአማራ ሕዝብ የህልውና ማዳን ዘመቻ ተጋድሎ ለመፈፀም በሙሉ ጀግንነትና ወኔ ሙል ስልጠና ወስደው ከተመረቁ በኋላ በአመራሩ የተቀነባበረ ሻጥርና ክህደት ባዶ እጃቸውን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ ምሽግ ለሚጠብቃቸው ጠላት አረር ማብረጃና ደመ ከልብ እንዳደረጓቸው ታሪክ ይቅር የማይለው ትልቅ ክህደት በአማራ ሕዝብና ልጆቹ ላይ በብአዴን ጭንጋፍ የእንግዴ ልጆች እንደተፈፀመ የሚቅጥለው መረጃ ይገልጻል::

https://www.facebook.com/100012685426356/posts/127170980326185 5/?d=n
ታዲያ የአማራ ሕዝብ በፌደራሉ ከተሰገሰጉት ባለስልጣናት አቶ ተመስጌን ጥሩነህን እና ከክልሉ ባለስልጣናት ደግሞ እራሻቸው አቶ አገኘሁ ተሻገርን የወያኔ ኤጅንቶች
ናችው! ካማራ አብራክ የተጨነገፉ የእንግዴ ልጆች ናቸውና አናምናቸውም ቢል ይፈረድበታልን!!!!
የአማራ ኃልውና ትግል አስራ ሁለት መርሃ ግብሮች:-

  1. አደረጃጀት፦ ከመንግሥት አደረጃጀት ውጭ የሆነ የአማራ ሕዝባዊ ግብረ ኃይል ማቋቋም፤
    2.ስልጠና-፤ወታደራዊ ስልጠና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሕዝብ እንዲወስድ፤
    3.ዘመቻ፡- የአማራ ሕዝብ ባሉት አደረጃጀቶች ሁሉ የኃልናውን ዘመቻ መቀላቀል፤
    4.ጥበቃ፡- በከተማም ሆነ ገጠር ነዋሪዎች እራሳቸውን አደራጅተው የአካባቢያቸውን ደህንነት ከተለያዩ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው መጠበቅ: ግዳጅ ላይ ያሉ ቤተሰቦችን መንከባከብና ማገዝ፤
  2. ማቋቋም፤-በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን እርዳታ አሰባስቦ ጊዚያው መጠላያና ምግብ ደህንነት ማስጠበቅና ወደ መደበኛ ኃይዎታቸው በቋሚነት መመለስና ማቋቋም
  3. ሴራ ማጋለጥ፤- የአማራን የኃልውና ትግል የሚያደናቅፉትን: ሴራ የሚሰሩትን ማጋለጥ: ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ
  4. ‘ጆኖሳይድ ክስ’፤- የአማራውን የኃልውና ትግልና ተጋድሎ የክልሉና የፌደራል የመንግሥታት ሽፍን ያለውና በታላቅ ሴራ የተወሳሰበ የዘር ማፅዳቱ ተከታታይ እንድሆነ ለአለም አቀፍ ማኃበረሰቡ ማሳወቅና እርዳታና ድጋፍ ማሰባሰብ:
  5. ጣልቃ ገብነትን መቋቋም፤- የክልሉንም ሆነ የፌደራል መንግሥቱን አላስፈላጊ የሆነ ጣልቃ ገብነት መቋቋም
  6. ቅንጅት፤- ሕዝባዊ ኃይሉ ከመንግሥት ወታደራዊ አደረጃጀትና ከአጎራባች ክልሎች (አፋር) አሰላለፍ ጋር መረጃ መለዋወጥ መቀናጀት መደጋገፍ፤
  7. ወራሪውን ወግቶ ማስወጣት፤- ክልሉን በኃይል ወረው የሚገድሉትን: የሚዘርፍትን ከክክልሉ እንዲወጡ ማድርግ ተቀዳሚና ዋና ተግባሩ ማድረግ፤
  8. በሌል ክልል የሚጨፈጨፉ አማሮችን ማገዝ፤- በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚደረገው ጦርነት ባልተናነሰ በተለይ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ክልሎች የሚገኙ አማሮችን እልቂት (ዘር-ማፅዳት) በትኩረት መከታተል ማጋለጥና ታላቅ ጫና ማድረግ::
  9. እርዳታ፤- ከሀገርም ሆነ ከውጭ የሚሰባሰቡት ገንዘብና ቁሳቁሶች በቀጥታ ለሕዝብ ባስቸኳይ እንዲደርስ ማድረግ:
    ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ዶ/ር ጥላሁን!
    ነሐሴ 2013

Pdf View

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator