0 0
Read Time:1 Minute, 27 Second

ወገኖቻችን በወሎ፣በጎንደር እና በሸዋ በአሸባሪዎች ጥምረት ሕልቆ መሳፍርት ጥቃት እየተፈጸባቸው መሆኑን የሚጠቅሱት የጦር መኮንኖቹ “አላጠፋንም፤ አጥፍተንም ከሆነ ዘምተን ህዝባችን እንድንክሰው ይፈቀድልን” በሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመንግስት እያቀረቡ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሰሚ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረው በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት ታስረው 2 ዓመት ከ6 ወራት በላይ ያስቆጠሩ የጦር መኮንኖች፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና የአዴኃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደ ምስክር የማሰማት ሂደቱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀላቸውም።

አቃቢ ህግ 133 ምስክር አቀርባለሁ ብሎ 84 ካስመሰከረ በኋላ በተከሳሾች በኩል የመከላከያ ምስክር ማሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፤ እስካሁን ከ50 በላይ ምስክሮችን አሰምተዋል፤ የተወሰኑ ይቀራሉ።

ህዳር 16 ቀን 2014 ፍ/ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር የማሰማት ሂደቱ ይቀጥላል ሲሉ በመሃል አቃቢ ህግ ለዘመቻ ህልውና ስምሪት በመደረጉ ባለሙያ ስለሌለ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተከሳሾችም ሆነ የተከሳሽ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ደንበኞች ለረዥም ጊዜ የታሰሩ መሆናቸውን በመጥቀስ የአቃቢ ህግን ጥያቄ ተቃውመውታል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የአቃቢ ህግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ህዳር 23 ቀን 2013 ቀሪ የመከላከያ ምስክሮች እንዲሰሙ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷል።

በተከሳሾች በኩል ለዘመቻ ህልውናው በመሳተፍ የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚፈልጉ በመግለጽ ፈጣን ፍትህ እንዲሰጣቸው፤ ያ ካልሆነ ደግሞ መንግስት እጁን አስገብቶ በመፍታት እንዲዘምቱ ቢያደርግ መልካም ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

አሚማ አጠቃላይ ሂደቱን በተመለከተ ከጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታሰሩ 512 ቀናት ያስቆጠሩት እነ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ቀለብ ስዩምና አስካለ ደምሌ ህዳር 16 ቀን 2014 በነበራቸው ቀጠሮ አለመቅረባቸውን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል።

የፌደራል ማ/ቤቶች አስተዳደር በጸጥታ ችግር ምክንያት በሸዋሮቢት ማ/ቤት የነበሩ እስረኞችን ወደ ዝዋይ እያዘዋወርኩ በመሆኑ የአጃቢ እጥረት ስላጋጠመኝ ለማቅረብ አልቻልኩም እስካደራጅ ድረስ ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱን የተከሳሽ ጠበቆች የመከራከሪያ ፍሬ ነገሮችን በመጥቀስ ተቃውመውታል።

ዳኛም የማ/ቤት አስተዳደር እነ እስክንድር ነጋን በቀጠሮአቸው ለምን እንዳላቀረበ ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማለት ለህዳር 17 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጧል።

ከሁለቱ ጠበቆች ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator