መጋቢት 20/2014 በሶስት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ የመጡ የተደራጁ ኦነጎች እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በአሞራ ቤት ቀበሌ ልዩ ስሙ አውራ ጎዳና በተባለ አካባቢ
ላይ ጥቃቱን ማድረሳቸው ተገልጧል።

ጥቃቱ ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን የገለጹት የምንጃር ነዋሪዎች ሁሉም ነቅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

ጥቃቱን ለማድረስም የመንግስት አንቡላስ፣ አንድ አይሱዙና አንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ጥቅም ላይ መዋሉ ተገልጧል።

መጋቢት 20/2014 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከናዝሬት ወደ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መግቢያ በኩል ቡና ሲጠጡ በነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ አነጣጥሮ በመተኮስ አንዱን ሲገድሉ ሌላኛውንም በከባድ አቁስለዋል።

በመቀጠልም በአስፓልት ግራ እና ቀኙን በሴቶችና በህጻናት ላይ ጭምር በመተኮስ አደጋ አድርሰዋል፤ የቆሰሉ ሴቶችና ህጻናት መኖራቸው ተሰምቷል።

በዚህም አቶ መለሰ ከበደ የተባሉ የመከላከያ ምልስ እና የህልውና ዘመቻውም ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ጀግና ተሰውተዋል።

ጥቃቱ የተከፈተበት የምንጃር አርሶ አደርም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት በሰጠው የአጸፋ ምላሽ ወረራ እና ጥቃት የፈጸሙትን ማስቀረት መቻሉ ተነግሯል።

ይህ አካሄድ ለመስፋትና ለመንሰራፋት የያዙት ፍላጎትና እቅዳቸው አካል ስለመሆኑም ተነግሯል።

አሚማ ያነጋገራቸው አቶ ታደሰ ቦሰት በጥቃቱ የሰው ህይወት መጥፋቱንና 4 መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ጥቃቱ ከወትሮው በተለዬ እና በቡድን መሳሪያ እና በተሽከርካሪ ጭምር የታገዘ መሆኑን የገለጹት አቶ ታደሰ አሁንም አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ አስታውቀዋል።

የሚመለከታቸው የክልል መንግስት አካላት ቁጭ ብለው በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ላለው ትንኮሳ እና ጥቃትን ለማስቆም ከልብ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator