የሚቆጨኝ ቢደፍሩኝ ነበር በጥይት መቱኝ ብዬ አላማርርም እንኳንም በእነሱ እጅ አልተነካሁ (አልተደፈርኩ) – ራሷን መስዋዕት ያደረገችው የወልዲያዋ ታዳጊ
ከተወለደችበት ወለጋ ጉትን ኦነግ ሸኔን ሸሽታ ወልዲያ የመጣችው ታዳጊ የሸኔን ጥቃት በመፍራት ከቤተሰብ ተለይታ ከወለጋ በ2009 ተፈናቅላ ወደ ወሎ በመምጣት በወልዲያ ጎዳናዎች ላይ ብስኩትና ቦንቦሊኖ እየጠበሰች ስትኖር ሕወሓት ወልዲያን ሲቆጣጠር ከጓደኞቿ ጋር በመሆን በተቀመጠችበት ምሽት ላይ ወደተከራየችው ቤት የሽብር ቡድኑ ጀሌዎች ይገባሉ። አብረዋት የነበሩ አዳጊ ወንዶችን አንድ ቤት ውስጥ በመቆለፍ ሁለት ሴት ጓደኞቿን አስገድደው ይደፍራሉ፡፡ ሀብታም ራሷን ለማዳን ስትሞክር በጥይት ጭኗ ላይ በተደጋጋሚ እንደመቷት ገልፃለች፡፡ የሁለት ሽብር ቡድኖችን ግፍ የተጋፈጠችው አዳጊዋ ሀብታም- በወልዲያ