የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ብኘወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ “መንግስት የሰብዓዊ መብቶችን የማስከበር ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም!” ሲል ገልጧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በአገሪቱ እየተፈጸ ያለውን የሰብዓዊ መበቶች ጥሰቶች ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት የነበረበት ውድመትና ማፈናቀል እየጨረና ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም ለመግባት የማይችሉበትና በከፍተኛ ስጋት ላይ የሚኖሩበት ሁኔታ በመኖሩ

መንግስትና የሚመለከታቸው አካላቶች አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ህገ ወጥ ድርጊት በሚፈጽሙ ቡድኖች ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ በተለያዩ መግለጫዎች ሲወተውት መቆየቱን አውስቷል።

ነገር ግን ይህ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ የተለያዩ ከፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እንደቀጠሉ ይገኛሉ ብሏል ኢሰመጉ በመግለጫው።

የኦሮሚያ ከልል እና የሲዳማ ክልል በሚዋሰኑባቸው በሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ ሀሌላ ቀበሌ በ25/07/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች የሲዳማ ተወላጅ የነበሩ አንድ የሀገር ሽማግሌ በመገደላቸው በአካባቢው ግጭት ተፈጥሯል ብሏል።

ይህ ግጭት ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ተሰራጭቶ በአጠቃላይ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 5 ሰወች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሷል።

እንዲሁም በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አስታውቋል።

በተጨማሪም በአካባቢው የሚኖሩ የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች አካባቢውን በመልቀቅ እንደተፈናቀሉና ጥቃቱንም የፈጸሙት በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መሆናቸውን ከአካባቢው ሰዎች መረዳቱን ገልጧል።

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን በሰገን ዙሪያ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በተፈረው ግጭት በርካታ ቀበሌዎች እየተቃጠሉና የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሚገኝ የሚያሳይ መረጃዎች ለኢሰ ደርሰዋል።

ለዚህ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ በአስቸኳይ እንዲሰጥ ለሚመለከታቸው የክልል እና የፌደራል መንግስት አካላት ኢሰመጉ በተለያዩ መግለጫዎቹ ቢያሳሰብም ይህ ሆኖ ባለመገኘቱ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና እስከፊነቱ እየጨመረ ቀጥሏል ነው ያለው።

በተጨማሪም መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን አማሮ ልዩ ወረዳ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የተነሱ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 3 የአማሮ ኬሌ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሱት አስታውቋል።

በተዘረዘሩት እና በሌሎች ከግጭቶች ጋር ግንኙነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ኢሰመጉ ተጨማሪ የምርመራ ስራዎችን በማከናወን ሰፋ ያለ ዘገባ
እንደሚያቀርብ አስታውቋል።

በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተነሳው ግጭት የበለጠ ሳይባባስ እና የሚደርሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሳይበራኩቱ የሁለቱም ክልል መንግስታት ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከሁለቱም ወገኖች የሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማሌዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የበኩላቸውን እንዲወጡ ሲል ኢሰመጉ አሳስቧል።

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተነሳውን ግጭት የክልሉ መንግስት በተግባር ትኩረት እየሰጠው ባለሆኑ ኢሰመጉ በድጋሚ ለደቡብ ክልል መንግስት እንዲሁም ለሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያበጁ አሳስቧል።

በዚህም ረገድም በሀገራችን ኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች መፍትሄዎችን በማምጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላላቸው በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ላለው ግጭት መፍትሄ በማምጣቱ ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪ አድርጓል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator