ግንቦት 28/2014
መግቢያ፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች፣ በተፎካካሪ ፓ ርቲ አባላ ትና አመራሮቸ፣ በማሕበረሰብ አንቂዎችና በተለያዩ
የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በተደጋጋሚ እስራት እየተፈጸመ ይገኛል። ኢሰመጉምይህንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ሚያዚያ 29 ቀን
2014 ዓ.ም፣ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም እና ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች መንግስት የእርምት
እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲወተውት ቆይቷል፡፡ በጋዜጠኞች ላይ እየተፈጸመ ያ ለው እስር በአብዛኛው የህግ አግባብን ያልተከተለ፣ አስገድዶ
የመሰወር (enforced disappearance) ባህሪ ያለው ሲሆን ለአብነት ያህልም የፍትህ መጽሄት ማኔጂነግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ
ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ፣ 7 በሚሆኑ የአሻራ እና የንስር ዩቲዩብ ሚዲያ ጋዜጠኞች፣ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ፣ ጋዜጠኛ
ሰለሞን ሹምዬ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ቲና በላይ፣ አቶ አሸናፊ አካሉ እና መስከረም አበራ ላይ የተፈጸሙት እስራቶች ይገኙበታል። እነዚህን
በተለያዩ ጋዜጠኞች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ እስራቶች እና እገታዎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን፣ የመናገር መብትን፣የፕሬስ ነጻነትን
የሚጋፉ እና የሚገድቡ በመሆናቸው መንግስት ከእነዚህ ድርጊቶች እንዲቆጠብ ኢሰመጉ ሲወተውት ቆይቷል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፡
ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም የታሰረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በታሰረበት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በፖሊሶች ድብደባ እንደተፈጸመበት
በዚህም ድብደባ በአይኑ እና በጎድን አጥንቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት፣ ምንም እንኳን የፖሊስ ጣቢያው ሀኪም በውጪ እንዲታከም የጻፉለት
ቢሆንም ሊታከም እንዳልቻለ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች እንዲሁም በመርማሪዎቹ ጋዜጠኛ ተመስገንን በማነጋገር ለመረዳት የቻለ
ሲሆን። ሆኖም የኢሰመጉ መርማሪ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በታሰረበት ፖሊስ ጣቢያ ለመጎብኘት ሙከራ ባደረገበት ወቅት ተጨማሪ
መረጃዎችን መሰብሰብ እንዳይችል የፖሊስ ጣቢያው ፖሊሶች ለመተባበር ፈቃደኞች አልነበሩም።
ተያያዥ የህግ ግዴታዎች፡
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል-ኪዳንም (ICCPR) በአንቅጽ 10(1) ላይ ሁሉም ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች በሰብአዊነትና
የሰውን ተፈጥሮአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ ይያዛሉ ሲል ይደነግጋል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) አንቀጽ 5፣የሲቪልና
የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል-ኪዳንም (ICCPR) አንቅጽ 7 ማንም ሰው ጭካኔ ወይም ስቃይ አይደርስበትም ወይም ከሰብአዊነት
ውጪ የሆነየሚያዋርድ ተግባር ወይም ቅጣት አይፈጸምበትም ሲሉ ይደነግጋሉ። ። የአፍሪካ ቻርተር በሰዎች እና ህዝቦች መብቶች (ACHPR)
አንቀጽ 5 ባርነት፣ የባሪያ ንግድ፣ ማሰቃየት፣ ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የተከለከለ
መሆኑን ይደነግጋል።
በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 18 ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ
ወይም ቅጣት የመጠበ ቅ መብት አለው ሲል ይደነግጋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር
720/2011 በአንቀጽ 24 ላይ የፖሊስ ተግባራትን በመፈጸም ረገድ ኢሰብዓዊ ወይም ክብርን የሚነካ አያያዝ ወይም ድርጊት መፈጸም
የተከለከለ ነው ሲል ይደነግጋል። የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 96/2003 የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ
የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ በአንቀጽ 14 በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 24 ላይ የተጠቀሰው በእዚህ
ደንብ ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል።
በተጨማሪም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 424 ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የመያዝ ፣ የመጠበቅ፣ የመቆጣጠር፣ የማጀብ ወይም
የመመርመር ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ የተጠረጠረን፣ የተያዘን፣ በምስክርነት የቀረበን፣ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የተጠራን፣ ተይዞ
በማረፊያ ቤት ወይም በእስር ቤት የተቀመጠን ወይም የእስራት ቅጣት በመፈጸም ላይ የሚገኝን ሰው ላይ አግባብነት የሌለው ወይም
ከሰብዓዊ ርህራሄ ውጭ የሆነ ወይም ለ ሰው ልጅ ክብር ወይም ከተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት ተቃራኒ የሆነ ድርጊት የፈጸመበት እንደሆነ፣
በተለይም ድብደባ፣ የጭካኔ ተግባር ወይም የአካል ወይም የመንፈስ ስቃይ ያደረሰበት እንደሆነ በቀላል እስራት፣ ወይም በመቀጮ ወይም
ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአስር አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል ሲል ይደነግጋል
የኢሰመጉ ጥሪ፡
• መንግስት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዲሁም በእስር ላይ ለሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞች ህጋዊ አካሄዶችን በመከተል ፈጣን ፍትህ እንዲሰጥ፣
• ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአስቸኳይ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ እንዲ ደረግ፣
• በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ድብደባ የፈጸሙ የፖሊስ አባላትን በአስቸኳይ በህግ ተጠያቂ በማድረግ በሌሎች እስረኞች ላይም መሰል
ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ አስተማሪ ቅጣትን በማሳልፍ እርምጃ እንዲወስድ፣
• ፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ያሏቸውን መብቶች በአግባቡ እንዲያከብሩ እንዲሁም የእስረኞች ሁኔታን መከታተል ይችሉ ዘንድ
ለሰብዓዊ መብት ተቋማት ተባባሪ እንዲሆኑ ኢሰመጉ ጥሪውን ያቀርባል።
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ