0 0
Read Time:1 Minute, 16 Second

በኢትዮጵያ ህዝብ እየተፈጸመ ያለውን እልቂት በአጽንኦት የተመለከተው እናት ፓርቲ “ሀገር ሰላም የምታገኘው ስንት ንጹሓን ዜጎች የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ ነው?” ሲል መንግስትን ጠይቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ60ዎቹ ጀምሮ በተጣባት የእኛና የእነሱ የፖለቲካ ትርክት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ
መተኪያ የሌላቸው ውድ ልጆቿን ሕይወት ገብራለች ዛሬም ድረስ እየገበረች ትገኛለች ብሏል እናት ፓርቲ በመግለጫው።

እንደ ሀገር ክፋት እየተጣባን እኛም እየተለማመድነው እንደምንገኝ መስካሪ አያሻንም ያለው እናት ፓርቲ ባሳለፍናቸው ጥቂት ቀናት በአፋር እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በተላላክ እና መዲና መካከል፣
በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በጉጂና በቡርጂ መካከል እንዲሁም በቤኒሻንጉል ክልል ካማሺ
ዞን በለውጂጋንፎይ እና በፓዊ በተከሰተ ግጭት ብዙዎች ለሕልፈት ተዳርገዋል ብሏል፡፡

መንግስትን አወዳሽ ሚዲያዎች
“ተደመሰሰ” ቢሉንም በኹሉም አካባቢ የተዳፈነ እሳት እንጂ የጠፋ ወይም ሊያጠፋው የፈለገ እንደሌለ ድርጉቶቹ
ማሳያዎች ስለመሆናቸው ገልጧል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች የዋለ ያደረ፣ አንዳንዱም ጭሱን ዐይቶ በቀላሉ በአካባቢው ወግና ባህል
መፈታት የሚችሉ ችግሮች ተጋነው ሰውን በግፍ እስከማገዳደል ደርሰዋል ነው ያለው፡፡

እንደቤኒሻንጉል ያሉ አካባቢዎች
ደግሞ በመሠረታዊነት የውጭም የውስጥም ተጻራሪ እጆች ያሉበት በመሆኑ እያንዳንዷ የምትወሰድ
የመፍትሔ አማራጭ ጥንቃቄ መሻቷ አያጠያይቅም ሲል እናት ፓርቲ አክሏል፡፡

አኹን አኹን ደግሞ ከክልሉ በአንጻራዊነት ሰላም ወደነበሩ
አንዳንድ አካባቢች መዛመቱ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን ጠቁሟል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ሰሚ
ካለ አጥፊዎች በአስቸኳይ በሕግ እንዲጠየቁ አብክረን እንጠይቃለን ብሏል፡፡

ለመጠፋፋት አዙሪቱ በዋነኛነት የእኛና የእነርሱ የፖለቲካ ትርክት ቀማሪዎችና አራማጆች፣ የሕዝብን
ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ሓላፊነት የወደቀበት መንግስት የየድርሻቸውን ሓላፊነት እንደሚወስዱ በመግለጫው አመላክቷል።

ይሁን እንጂ የገባንበት የመጠፋፋት ጎዳና በዚህ ዓይነት መልኩ መቋጫ እንደማያገኝ እሙን በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፋፋዮችን፣ ጎሰኞችንና ጎጠኞችን በቃ ሊል፣ በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካና መገለጫውን፣ የእንዲህ ያለው
አጀንዳ ተሸካሚዎችን ተው በቃችሁን በማለት በአንድ ድምጽ እንዲነሳ፣ ወዲህም ራሱን እያደራጀ አካባቢውን
እንዲጠብቅ ሲል እናት ፓርቲ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም በተለያዩ አካባቢዎች ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ከልብ የመነጨ ሀዘናችንን እየገለጽን ለሟች ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን ብሏል፡፡

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator