ByAdmin

Apr 17, 2022

አቻምየለህ ታምሩ

የኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ባልሆኑና ኦሮሞ አይመስሉም በሚሏቸው ግፏአን ላይ የጅምላ ፍጅትና የዘር ማጥፋት እያካሄዱ የፈጸሙት የዘር ማጥፋትና የጅምላ ፍጅት በዓለም ላይ እንዳይታወቅባቸው የጩኸቴን ቀሙኝ እሪታ ከጣራው በላይ ማሰማትና በዱልዱም ያረዷቸውን ግፉአን መወንጀል ጥርሳቸውን የነቀሉበትና የተካኑበት “የፖለቲካ ብልጠታቸው” ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወረሪውና ዘር አጥፊው ሉባ የሚባለው የኦሮሞ የገዢ ብቻ ናቸው። ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከወረረበት ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስከ ዛሬ ድረስ ከ28 በላይ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ነገዶች በኦሮሞ ወረራ፣ ጦርነትና ስልቀጣ ጠፍተዋል። እውነታው ይኼ ቢሆንም ቅሉ የኦሮሞ ብሔርተኞች ግን የተቀሩት የኢትዮጵያ ነገዶች በኦሮሞ ወረራ ተውጠው ከመጥፋት የታደጉትን በወራሪነትና በዘር አጥፊነት ይከሳሉ። ይኼን የሚያደርጉት ቀጣዩ ወረራቸው መከላከል እንዳይገጥመው ከወዲሁ መንገድ ለመጥረግ ነው።

ጭሰኛነትና ባርነት የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚኮሩበት ገዳ የሚባለው የወረራ ሥርዓታቸው በጥንት የኢትዮጵያ ነገዶች ላይ የተከላቸው ሥርዓተ ማኅበራት ናቸው። በኦሮሞ በራሱ አባባል መሰረት ኦሮምኛ ከሚናገረው አስር ሰው ውስጥ ዘጠኙ ኦሮሞ በወረራ ይዞ ባርያ ያደረገው ገርባና ጰለታ ነው። ጰለታ ማለት ኦሮሞ ገርባ ያደረገው ወይንም በሞጋሳና ሜዴቻ ማንነቱን ወደ ኦሮሞ የቀየረው ሰው ልጅ ማለት ነው። ኦሮሞ ኢትዮጵያን ሲወርር በኃይል አስገብሮ ጭሰኛና ባሪያ ያደረጋቸውን ነባር ነገዶች ከመሬታቸው ከነቀለ በኋላ «ገርባ» ይላቸዋል። ባጭሩ ገርባዎች የኦሮሞ ጭሰኞች ናቸው። ገርባ የሚለው የኦሮምኛ ቃል የአማርኛ ፍቺው ባርያ ወይንም አገልጋይ ማለት ነው።

ከአስሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ መካከል ትክክለኛ ኦሮሞ ያልሆነው ዘጠኙ የጥንት ማንነታቸውን በኃይል እንዲያጡ ተደርጎ ኦሮምኛ እንዲናገሩ የተደዱት ገዳ የሚባለው የወረራ ሥርዓት ተቋማዊ ያደረገው የገርባ ሥርዓት ነው። በገዳ አደረጃጀት መሰረት ኦሮሞ ሳይሆን ማንነቱ በኦሮሞ የተቀየረበት የኦሮሞ ባሪያ ነው። ኦሮሞ ያስገበራቸው ነባር ነገዶች ገርባ እያለ እንደሚጠራቸውና ጭሰኛ አድርጓቸው እንደኖረ ማወቅ የሚሻ በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ጥርሱን የነቀለው አሌክሳንድሮ ትሪውልዚ “Boorana and Gabaro among the Macha Oromo in Western Ethiopia” በሚል ያሳተመውን ምርምር ያንብብ።

አባ ማሲያስ የሚባሉ እ.ኤ.አ. ከ1846 ዓ.ም. – 1880 ዓ.ም. የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኦሮሞ በወረራ በያዛቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ላይ ሐዋርያ አድርጋ የሾመቻቸው ካርዲናል በኢትዮጵያ የአገልግሎት ዘመናቸው መጨረሻ አካባቢ ወደሮም በጣሊያንኛ ቋንቋ በጻፉት አንድ ደብዳቤያቸው በወንጌል አገልግሎት ለዓመታት እየተዘዋወርኹ አስተማርኹት ስለሚሉት ሕዝብ ሲጽፉ “ቢያንስ አንድ ባሪያ የማያሳድር የኦሮሞ ቤተሰብ ማግኘት አይቻልም” በማለት ነበር የገለጹት።

የኦሮሙማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነው በላኤ ሰብ ዐቢይ አሕመድ እንደ ሮል ሞዴሉ የሚቆጥረው የጅማው ገዢ አባ ጅፋር አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ድኆችን ወደ ዘሮቹ አገር ወደ ሳውዲ አረቢያ በባርነት ጭቡ አድርጎ የሸጠ በምስራቅ አፍሪካ ወደ የማይገኝነት የባሪያ ከበርቴ ነበር። ዛሬ በጅማ ከተማ ውስጥ ቁሞ የሚገኘው የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሞች፣ ካፋዎች፣ ኢናርያዎች፣ ጋፋቶች፣ ወዘተ ይፈነገሉበት የነበር የባሪያ ንግድ ማዕከል ነበር።

በአ ባጅፋርና ገዳ በሚባለው ከ28 በላይ የኢትዮጵያ የጥንት ነገዶችን ባጠፋበት የገርባ ሥርዓት የሚኮሩት ነውር ጌጡዎቹ የኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የባርያ ንግድን በአዋጅ ያገዱትንና በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ባሪያ ሲሸጥ የተገኘ ቢኖር በሞት እንዲቀጣ ሕግ የደነገጉትን፤ ኦሮሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶች ላይ የተከለው የባርነት ሥርዓት እንዲያከትም ያደረጉትንና ኦሮሞ ባሪያ አድርጎ ሲሸጣቸው የኖራቸውን ጰለታዎችና ገርባዎችን ከኦሮሞ የባርነት ሥርዓት ያላቀቁትን ዳግማዊ ዐጤ ምኒልክ ሲያሰየጥኑ ይውላሉ።

ምን ይኼ ብቻ! ከባሮ ቱምሳ እስከ ሐጫሉ ሁንዴሳ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ርስ በርስ በተገዳደሉ ቁጥር በአማራ እየተመካኘ በአማራ ላይ የዘር ፍጅት ሲካሂዱ የኖሩት ርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ አማራ እንደገደላቸው በማስመሰል ከጣራው በላይ በማስጮህ ነው።

ኦነጋውያን የትግል አባት አድርገው የሚቆጥሩትን ባሮ ቱምሳን የገደለው አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ ወይም በጫካ ስሙ ጃራ አባገዳ በመባል የሚታወቀው የእስላማዊ ኦሮሚያ ሪፐብሊክ ግንባር መሪ የነበረው ጨካኝ አውሬ ነው። “ኦሮሞ ከፖለቲካ ስልጣን ተገልሏል” ብሎ ኢስላማዊ ኦሮምያን ለመፍጠር ጫካ የገባው ጃራ አባገዳ ወይም አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛና ሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ገዢ የነበሩት የፊታውራሪ ኢብራሂም ሀሚድ ልጅ ነው።

ባሮ ቱምሳን ጃራ አባገዳ እንደገደለው ታሪኩን የነገረን መረራ ጉዲና ነው። መረራ ጉዲና ይህን ታሪክ የነገረን በጦብያ መጽሔት በጥር 1988 ዓ.ም. «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይሆንም» በሚል ርዕስ ባሳተመው ሁለት ክፍል ጽሑፉ ነው።

ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የኦሮሞ ብሔርተኛት አባት የሚለው ዳኛ አሰፋ ዱላ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ የተገደለው በኦሮሞው በጃራ መስፍን በጥይት ተጠዛጥዘው ሲሆን ርስ በርሳቸው ተገዳደሉበት የጠባቸው ምክንያትም በመካከላቸው የተፈጠረው ቁርሾ ነው። ኦነጋውያን ግን ለኦሮሞ ወጣቶች ያስተማሩት ዳኛ አሰፋ ዱላን አማራ እንደገደለው አድረገው ነው።

ኦነግ የኦሮሞ ትግል አባት ያደረገውን ጀኔራል ታደሰ ብሩን የመሬት ላራሹን አዋጅ ተቃወመ ብለው የገደሉትም ኦሮሞዎች ናቸው። መጋቢት 5 ቀን 1967 ዓ.ም. አዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣው ሪፖርት ማንበብ እንደሚቻለው ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከነ ጭስኞቻቸውና ከኮሎኔል ኃይሉ ረጋሳ ጋር ከሸፈቱበት አስሶ የያዛቸው የኦሮሞ ነገድ ተወላጁ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ገለቱ ሻለቃ ተስፋዬ [ኋላ ሌተናት ጀኔራል] የኢትዮጵያ 11ኛው መከላከያ ሚንስትር ሲሆን ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበር።

ጀኔራል ታደሰ ብሩ እንደሸፈቱ እጃቸው እንዲያዙ አልያም እምቢ ካሉ እንዲደመሰሱ ትዕዛዝ የሰጠው የደርጉ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት የወለጋው ኦሮሞ ኮሎኔል ተካ ቱሉ ነበሩ። ጀኔራል ታደሰ ተይዘው ልዩ የጦር ፍርድ በቀረቡ ጊዜ የልዩ የጦር ፍድር ቤቱ አቃቢ ሕግ ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የነበሩ ሲሆኑ ዳኛው ደግሞ ኦሮሞው ሻለቃ በቀለ ነዲ ነበሩ። መረራ ጉዲናም ቀደም ሲል በጠቀስሁት ጽሑፉ ጀኔራል ታደሰ ብሩ በኦሮሞ እንደተገደሉና ጀኔራሉ እንዲገደሉ ሴራውን ያቀነባበረው ባሮ ቱምሳ እንደሆነ ጽፏል። ኃይሌ ፊዳ የሚመራው መኢሶንም ጀኔራል ታደሰ ብሩ ሲገደሉ ፊውዳሉ ታደሰ ብሩ እንደተገደለና የተወሰደውን አብዮታዊ እርምጃም እንደሚደግፍ በልሳኑ መግለጫ አውጥቷል።

በሌላ አነጋገር ጀኔራል ታደሰ ብሩ የተረሸኑት ከሸፈቱበት ተይዘው እንዲመቱ ወይም እንዲረሸኑ ኦሮሞው ኮሎኔል ተካ ቱሉ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት ኦሮሞው ጀኔራል ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ባካሄዱት ኦፕሬሽን ሲሆን፤ ጦር ፍርድ ቤት የቀረቡትና የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ደግሞ ኦሮሞው ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ አቃቢ ሕግ በነበሩበትና ኦሮሞው ሻለቃ በቀለ ዳኛ ሆነው በተሰየሙበት የልዩ ጦር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ነው። ይህን በጀኔራል ታደሰ ብሩ ላይ የተላለፈው የግፍ ፍርድ በኦሮሞው በኃይሌ ፊዳ ድርጅት በመኢሶን ተደግፎ ነበር። ኦነጋውያን እንደ ትግል ጀማሪያቸው የሚያዩትን የመኢሶኑን ኃይሌ ፊዳንም አብዮታዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የወሰኑትም [የወሰኑበት ሰነድ በእጄ ገብቷል] ኦሮሞዎቹ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን፣ ደበላ ዲንሳና ተካ ቱሉ ናቸው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ሐውልት የቆመለትን የጡት ቆረጣ ታሪክ ሳይቀር የነገድ ስም ይሰጠው ከተባለ የኦሮሞ እንጂ የሌላ የማንም ባሕል አይደለም። ለዚህ ደግሞ ማስረጃው ራሳቸው ኦሮሞዎች ናቸው። ኦሮሞው ዶክተር ታደሰ በሪሶ በ1980 ዓ.ም. “Traditional warfare among the Guji of Southern Ethiopia” በሚል በጻፈው የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ወረቀቱ ገጽ 31 ላይ የአርሲ ኦሮሞ ጡት የመቁረጥ ባሕል እንደነበረው ጽፏል። የኦሮሞን ጡት የቆረጠው ኦነግ መሆኑን ደግሞ የማይሞተውን የታሪክ ምስክርነት የሰጠን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበረው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ነው። ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚል በተረከውና የሕይዎት ታሪኩን ባቀረበበት መጽሐፉ ገጽ 50 ላይ ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሴት ወታደሮችን ማለትም የሴት ኦሮሞ ወታደሮች ጡት ይቆርጥ እንደነበር ባይኑ ያየውን ታሪክ ነግሮናል። ነጋሶ ኦነግ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት የቆረጠበትን ታሪክ የኦነግ አምበል የነበረው አባ ቢያ አባ ጆቢር አባ ጅፋር ሳይቀር በሽግግር መንግሥት ተብዮው ምክር ቤት ፊት ቀርቦ እንዳረጋገጠና የሰጠውም ምስክርነት በምክር ቤቱ ላይበራሪ ውስጥ በምስልና በድምጽ ተመርጆ እንደሚገኝ ነግሮናል።

ከሶስት ዓመታት በፊት በጃዋር መሐመድ የሚመራው ሁለተኛው “መንግሥት” በቡራዩ፣ በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በናዝሬት፣ በሐረር፣ ወዘተ ባካሄደው የዘር ፍጅት የአማራ፣ የጋሞ፣ የዎላይታና ኦሮሞ አትመስሉም የተባሉ የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሴቶች ጡት ተቆርጧል። የተደራጁ ቄሮዎች የፈጸሙት የዚህ ዘግናኝ ወንጀል ማስረጃ በፎቶና በተንቀሳቃሽ ምስል ተደራጅቶ በማኅደራችን ይገኛል።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ይህንን ሁሉ ዘግናኝ ወንጀል ኦሮሞ ባልሆኑና ኦሮሞ አይመስሉም በሚሏቸው ላይ እየፈጸሙ ወንጀላቸውን ለመደበቅ ግን እነሱ የፈጸሙትን አለማቀፍ ወንጀል ሌላ የፈጸመው አድርገው በመፍጠር የግፉአንን ጩኸት ቀምተው ያላዝናሉ።

ከሰሞኑ የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ አማራ ክልል በሚባለው ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሸንኮራ ወረዳ የምትገኘውን አውራ ጎዳና ከተማን እንደ ኤፌሶን ለማውደም የግፍ ወረራ ፈጽሞ የጅምላ ፍጅት ፈጽሟል። ይህንን ተከትሎ ወራሪው የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ የኦሮሞ ብሔርተኞች ለዘመናት ሲከተሉት በኖሩት “የፖለቲካ ጥበብ” ተክኖ ራሱ ወረራ ፈጽሞና ንጹሐንን የአማራ ገበሬዎችን ቤት ለቤት እየዞረ መጨፍጨፉ ሳያንሰው ቤት ለቤት እየዞረ የፈጃቸውን ንጹሐን ተጠያቂ በማድረግና ጭራሹኑ አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ ዘልቆ የሚገኘውን የአውራ ጎዳና ከተማና አካባቢውን ኦሮምያ የሚባለው ክልል አካል አድርጎ መግለጫ አወጣ።

ልብ በሉ! የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ ቤት ለቤት እየዞረ የጨፈጨፋቸውን ግፉአንን “ጽንፈኛ አማሮች” እያለ ያወገዘውና አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ የሚገኘው የምንጃር አውራ ጎዳና ከተማና አካባቢው ኦሮምያ ክልል የሚባለው ውስጥ እንዳልሆነ ጠፍቶት አይደለም፤ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ እንዲህ ስለሆነ ነው። ቀደም ሲል እንዳልነው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ እነሱ የፈጽሙትን ወይም ሊፈጽሙ ያሰቡትን ዘግናኝ ወንጀል ሌላ በነሱ ላይ የፈጸመው አድርገው ጩኸት የመቀማት የካበተ ልምድ ያላቸው ናቸው። በምንጃርም ከሰሞኑ ያደረጉት ይህንኑ ነው።

በኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ ማፈርና ነውር የሚባል ለሰው ልጆች የተሰጡ ጸጋዎች ስለሌሉ ሌላውን “ጽንፈኛ” ብለው ሲከሱ ሰው ምን ይለናል አይሉም። በምድር ላይ የተፈጠረ ጽንፈኛና አሸባሪ ሁሉ ቢሰበሰብ እንደ ኦሮሞ ብሔርተኞች ጽንፈኛ፤ ድኆችን በማንነታቸው ብቻ መጥላትን ፖለቲካው ያደረገ አረመኔ ፍጥረት አይገኝም። የኦሮሞ ብሔርተኞች ግን እነሱ የሚያደርጉትን፤ ወይም እነሱ የሆኑትን ለሌሎች በመስጠት የግፉአኑን ለቅሶ እየቀሙ ከጣራው በላይ እሪ ማለትን ስለተካኑበት በልጆች የመማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የጽንፈኛ ተምሳሌት ተደርገው ሊቀርቡ የሚገባቸው እነሱ የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሔርተኞች በዱልዱም የሚገግዟቸውን ምስኪን የአማራ ገበሬዎች ጩኸት ቀምተው አፈር ገፊዎችን በጽንፈኛነት ይከሷቸዋል።

የኦሮሞ ብሔርተኞች የግፉአንን ጩኸት እየቀሙ እሪታቸውን ከጣራው በላይ የሚያሰሙት ስለሁለት ነገር ነው፤ አንድም ሌሎችን የሚከስሱበትን ወንጀል ወረራ አካሂደው ፈጽመውታል፤ አልያም የዘር ማጥፋት ወንጀሎች (Genocide)፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (Crimes against Humanity)፣ የጦር ወንጀሎች (War Crimes)፣ የወረራ ወንጀሎች (Crime of aggression)፣ በሰላም ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (Crime against Peace)፣ ወታደራዊ ወንጀሎችና ዘግናኝ የመብት ጥሰቶችን ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ናቸው።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ወንጀል እየሰሩ የሚያሰሟቸው እነዚህ የጩኸቴን ቀሙኝ ውንጀላዎች ኦሮሞ ባልሆኑና ኦሮሞ አይመስሉም በሚሏቸው ላይ ሲያካሂዱ የኖሩትን የጅምላ ፍጅትና እልቂት ሲፈጽሙ ለዘመናት ሲከተሏቸው የኖሯቸው ስልቶቻቸው ናቸው። ኦሮሞ ባልሆኑና ኦሮሞ አይመስሉም በሚሏቸው ላይ እስካሁን ያካሄዷቸውን የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ የጭካኔ ተግባሮችን፣ የጦርና የወረራ ወንጀሎችን በሴቶች፣ ሕጻናት፣ አቅመ ደካሞችና ባጠቃላይ በንጹሐን ላይ እየፈጸሙ በንጹሐን የጅምላ ፍጅትና ጭፍጨፋ ክብረ ወሰን ሲቀዳጁ የኖሩት እንዲህ የግፉዓንን ጩኸት እየቀሙ እነሱ በሰሩት ወንጀል ግፉአኑን እየከሰሱ ነው!

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator