በምስራቅ ጎጃም ዞን የጁቤ ከተማ ኗሪ የሆነው ፋኖ አበባው እጁን ለመንግስት እንዲሰጥ ለማስገደድ በፎቶው ላይ የሚታየውን ህፃን ልጁን የመንግስት የፀጥታ ሃይል ይዞታል ::

በሰሞኑ የብልፅግና እመቃ ጎጃም ውስጥ የመንግስትን ህገወጥ እስር በመቃወም እጅ አንሰጥም ስላሉ በመያዣነት የተፍላጊ ሚስቶች ፣ ወላጆች ፣ ወንድም እና እህቶች ተይዘው ታስረዋል :: ዛሬ ደግሞ ህፃን ልጅ ::

ይሄን ግፍ ነው የምንቃወመው ::

ፋኖ መቶ አለቃ አበበ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት ስለ ሴቶች እና ስለህፃናት መብት መከበር ብዙ የሚወተውተው መንግስት እናትና ልጅ ባልሽ ፋኖ ነው ባልሽን ካላመጣሽ በሚል የመሐይም አስተሳሰብ አስሮ እያሰቃያቸው ይገኛል ብለዋል። በባሶሊበን ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡ 4 ቀን ሆኗቸዋል።ይኸው ይመራል ያስተዳድራል የተባለ መንግስት ህፃን አስሮ ያሰቃያል። የአማራ ህዝብ ይህንን ጉድ ማወቅ አለበት ብለዋል።

የአማራ ተወላጆች የመንግስት ሰራተኞች እየታፈኑ መሆኑ ታወቀ

ኦህዴድ ብልፅግና በአማራ ሕዝብ ላይ የጀመረው ማሳደድ የውክልና ጦርነት በአዲስ አበባ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በላይና በታችኛዉ መዋቅር የሚገኙ በሙያቸው ተቀጥረው የሚሰሩ የአማራ ተወላጆችን በማንነታቸዉ ብቻ እያሰሩ መሆኑ መረጃ ደርሶኛል።

በዋናነት በክልሉ የተጀመረዉ ሕዝባዊ ንቅናቄዉ ወደ አዲስ አበባ ይገባል በሚል በተረኞች መነፅር የተፈራ ሲሆን የአማራ ፋኖን ይደግፋሉ የተለየ ተቃዉሞ በመንግስት ላይ ያነሳሉ የሚሉትን በመለየት አንገት ለማስደፋት አማራን ማሰር መጀመራቸው ታውቋል።

የታሳሪዎች ዝርዝር እንደደረሰን እናሳውቃለን።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator