ሰበር ዜና!

አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የጥምቀት በዓል በሚያከብሩ ወጣቶች ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ወጣት ሲገደል፣ ሌሎች 4 ወጣቶች ቆስለዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

ጥር 12 ቀን 2015 ዓ/ም

አዲስ አበባ ሸዋ

አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የጥምቀት በዓልን ሲያከብሩ በነበሩ ወጣቶች ላይ ከአካባቢው ፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ቢላል ታዴ የተባለ ወጣት ህይወት ሲያልፍ፣ ሌሎች 4 ወጣቶች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

የዐይን እማኞች እንደሚሉት ጥር 12/2015 ከቀኑ 8:30 ገደማ ጫካው ተክለ ሀይማኖትን ለማስገባት እየጨፈሩ፣ እያጀቡ ባሉበት ባርያው የሚባል መይሳው ካሳ የሚል ቲሸርት የለበሰን አስጨፋሪ ሊያስሩት ፓትሮል ላይ ሲጭኑት በብዙ ወጣቶች ዘንድ ቁጣ ተቀስቅሷል።

አስጨፋሪውን አፍነው ለመውሰድ ያደረጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ ከወጣቶች ተቃውሞ የገጠመው ፖሊስም ጥይት መተኮስን መርጧል።

ይህን ተከትሎም ድንጋይ ውርዋሮ መቀጠሉን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የተናገሩት ምንጮች እንደሚሉት አንድ ትውልዱ ምስራቅ ጎጃም ማቻክል የሆነ የታክሲ ረዳት መሆኑ የተነገረለት ቢላል ታዴ ህይወቱ ሲያልፍ፣ በከባድ የቆሰለው ባዬ የተባለ ትውልዱ ምዕራብ ጎጃም የሆነ ወጣትን ጨምሮ 4 ወጣቶች ቆስለው ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስደዋል።

አሁን ላይ ቡልቡላ እንዳለ በፌፈራል ፖሊስ እና በአድማ ብተና ከበባ ስር ሆኗል፤ የሰፈሩን ወጣት በጅምላ በማፈስ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ በማጎር ላይ ይገኛሉ ሲሉ ሁኔታው ያሳሰባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator