የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን 16 ወራትን ከፈጀ ጥናቱ በኋላ ትህነግ በርካታ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ከሌሎች አካባቢዎች የታፈኑ አማራዎችን ያስርበትና በጅምላ ይቀብርበት የነበረውን “ገሃነም” የተባለ ቦታ አጋልጧል። 

አካባቢው በተራሮች የተከበበና ሰዎች በብዛት የማይሄዱበት በመሆኑ እንዲሁም በትህነግ አፈና ምክንያት ወንጀሉ ሳይጋለጥ ቆይቷል። ይሁንና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምር ቡድን ካጋለጠው በኋላ በርካታ አካላት ወንጀሉን ለማጋለጥ እየሰሩ ይገኛሉ። 

ከእነዚህ መካከል Getty Images የተሰኘ እውቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ይገኝበታል። በፎቶ ግራፍ ጋዜጠኝነት የታወቀው ይህ ተቋም “ገሃነም” ወደተሰኘው የትህነግ የሰቆቃ እስር ቤት በማቅናት በርካታ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። ተቋሙ በገፁ በለቀቃቸው ምስሎቹ አርጅተው የፈረሱትን የእስር ቤት ክፍሎች፣ የጅምላ መቃብሮች፣ በተለያዩ የጅምላ መቃብሮችና ዋሻዎች ተቀብረው የነበሩ የንፁሃን አፅሞች እንዲሁም ከሞት የተረፉ ነገር ግን ጭካኔው አሁንም ድረስ በአካላቸው ላይ በጉልህ የሚታዩ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አድርጓል።

በጥሻ የተሸፈኑት እስር ቤቶችና የጅምላ መቃብሮች፣ የንፁሃን አፅም የሞላባቸው የዋሻ እስር ቤቶች፣ ከምስሎቹ ማስተዋል እንደሚቻለው የራስ ቅላቸው ተመትቶ የፈራረሱ የንፁሃን አፅሞችና በሕይወት የተረፉት ንፁሃን ምልክቶች በሙሉ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ላይ የተፈፀመው የዘር ፍጅት ወንጀል ማሳያ ቋሚ ምስክሮች ናቸው።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator