0 0
Read Time:3 Minute, 0 Second

ዛሬ ማለዳ በአባ ሳሙኤል እስር ቤት

ዛሬ ለሦስተኛ ቀን በአባ ሳሙኤል እስር ቤት ማለዳው የተከፈተው በግፍ የታሰሩት ወጣቶችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ የከረረ ፀብ ነበር፡፡ የፀቡ መነሻ፣ ዛሬ በአራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በእነ ወግደረስ ጤናው የክስ መዝገብ እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ 17 ወጣቶች ለብሰውት የነበረው የአፄ ምኒልክ ምስል ያለው ቲሸርት ነበር፡፡ እንደሚታወሰው ሐሙስ እና አርብ፣ ቢኒያም ታደሰ፣ ሳሙኤል ዲሚትሪ፣ አስጨናቂ ተስፋዬ፣ ዳኛቸው ጉዳታ (ቻቻ)፣ ዘካሪያስ ቶራ የአድዋን ቲሸርት በመልበሳቸው ፍ/ቤት እንዳይቀርቡ ተከልክለው ነበር፡፡
ዛሬ ደግሞ፣ የጓዳኞቻቸውን አርአያ በመከተል በእነ ወግደረስ ጤናው የክስ መዝገብ የተካተቱ 17 ወጣቶች ወደ ፍ/ቤት ለመሄድ አውቶብስ ላይ ሊሳፈሩ ሲሉ የአደዋ ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው የፖሊስን ቁጣ ቀስቅሰዋል፡፡ እንዲያወልቁም ታዘዋል፡፡ እነሱም እምቢ ብለዋል፤ በየትኛው ህግ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ እንደወትሮውም ፖሊስ፣ “ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ “ቲሸርቱን አድርጋችሁ ፍ/ቤት መቅረብ አትችሉም” ተብለውም ፍ/ቤት የመቅረብ መብታቸውን ተገፈዋል፡፡
ይባስ ብሎም፣ እቃቸውን በሙሉ በፌስታል ጠቅልለው እንዲይዙ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው በአውቶብስ ላይ ከተጫኑ በኋላ ከአባ ሳሙኤል ጊቢ ወጥተዋል፡፡ የት እንደሚሄዱ አያውቁም ነበር፡፡ በግምት ከአንድ ሰዓት ጉዞ በኋላ ግን ጊዮርጊስ የሚገኘውና ከፍ/ቤቱ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጊቢ ውስጥ እንዲያርፉ ተደርጓል፡፡ ግን እዚያም ብዙ አልቆዮም፡፡ ችሎቱ ከተጀመረ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ፣ እንደገና በአውቶብስ በፍጥነት ወደ አባ ሳሙኤል እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ አልተፈለገም፡፡ ብዙዎቹ ከአዲስ አበባ ውጭ ወደ አለ እስር ቤት የሚሄዱ መስሏቸው ነበር፡፡
ፖሊስ በፍ/ቤት ያቀረበው የፈጠራ ምክንያት
የዛሬው ዕለት ቅዳሜ ቢሆንም፣ የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጡ
ፍ/ቤቶች ግማሽ ቀን ስለሚሰሩ፣ የዕለቱን ጉዳዮች ለመመልከት ዳኛዋ በወንበራቸው ላይ የተገኙት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ነበር፡፡ ከሁለት ሰዓት ተኩል ቆይታ በኋላ በመጀመሪያ የዳኛቸው ጉደታ (ቻቻ) እና ዘካሪያስ ቶራ ጉዳይ፣ ከዚያም የእነ ወግደረስ ጤናው ጉዳይ በሌሉበት ታይቷል፡፡
ተከሳሾቹ ለምን ፍ/ቤት እንዳልቀረቡ የተጠየቀው ፖሊስ በሰጠው ምላሽ፣ ተከሳሾቹ በእስርም ላይ ሆነው የአመፅ እና የአድማ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ፣ ፍ/ቤት አንቀርብም ብለው አሻፈረኝ ማለታቸውን፣ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ በፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጭመር ተለምነው እምቢ ብለዋል በማለት ነጭ ውሸት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም፣ መጀመሪያ ላይ ሲያዙ የተጠረጠሩት ባለስልጣናትን በመሳደብ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በመሞከር ቢሆንም፣ አሁን ግን የምርመራው ውጤት የሚያሳየው፣ ወንጀሉ ከባድ መሆኑንና በሽብርም የሚያስጠረጥራቸው ፍንጭ በመገኘቱ ጉዳዩ ወደ ፌድራል ፖሊስ ሊመራ እንደሚችል ገልጿል፡፡ ዋስትና እንዳይሰጣቸውም ጠይቋል፡፡ ይህ ማለት፣ ፍ/ቤቱ የዋስትና መብት ቢያከብርላቸው እንኳን፣ በፌድራል ፖሊስ ደረጃ አዲስ የሽብር ክስ ፋይል ተከፍቶባቸው በእስር ሊቆዩ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

የጠበቆቹ ምላሽ

ጠበቆቹ ለፍ/ቤቱ በሰጡት ምላሽ፣ ተከሳሾቹ ፍ/ቤት አንቀርብም ብለዋል የተባለው ፈፀሞ ሀሰት መሆኑን፣ በለበሱት ልብስ ሳቢያ ፍ/ቤት እንዳይቀርቡ መከልከላቸውን፣ ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ከአባ ሳሙኤል ተጭነው በፍ/ቤቱ አቅራቢያ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኙ እንደነበር፣ ፍ/ቤት እንዳይቀርቡ ተብሎ ችሎቱ በሂደት ላይ እያለ ተጭነው ወደ አባ ሳሙኤል መመለሳቸውን፣ ፖሊስ ከዚህ በፊት በከተማ ደረጃ ክስ መስርቶ ዋስትና ሲፈቀድ በፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አዲስ ፋይል መክፈቱን፣ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ዋስትና ሲፈቀድ፣ በፌድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለሦስተኛ ጊዜ በሽብር ሽፋን አዲስ ፋይል እከፍታለሁ ማለቱ ተከሳሾቹን በሰበብ አስባቡ ለማንገላታት ፍላጎት እንዳለ ማሳያ መሆኑን በመግለፅ፣ የተከሳሾቹን የዋስትና መብት ተከብሮ በነፃ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

የፍ/ቤቱ ብይን

ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ከአዳመጠ በኋላ፣ ተከሳሾቹ የፈለጉትን ልብስ የመልበስ መብት ያላቸው በመሆኑ፣ በሚቀጥለው ቀጠሮ የፈለጉትን ለብሰው ተከሳሾቹን ፖሊስ ፍ/ቤት እንዲያቀርብ፣ ጉዳዩን በበላይነት የሚመሩት የፖሊስ ኃላፊ በችሎት ተገኝተው ማብራሪያ እንዲሰጡ ለመጋቢት 27/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የሴት እስረኞች ዋስትና መፈቀድ

በአፈሳው ከተካተቱት ወጣት ሰቶች መካከል፣ በመአዛ ታደሰ የክስ መዝገብ የተካተቱት፣ ማህሌት እሸቱ፣ ሶስና ፈቃዱ እና ሊዲያ አበበ ፍ/ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፣ ፖሊስ በእነሱም ላይ ተመሳሳይ ክስ ካቀረበ በኋላ ዋስትናቸው እንዳይፈቀድ ተቃውሟል፡፡ ሆኖም፣ ፍ/ቤቱ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ለመስጠት በቂ ምክንያት አላገኘሁም በማለት እያንዳንዳቸው ሦስት ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ አዟል፡፡ ተከሳሾቹ ግን አሁንም እስር ቤት ሲሆኑ፣ ፖሊስ ይግባኝ ካልጠየቀ ሰኞ ዕለት ከእስር ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም፣ ሐሙስ ዕለት በተመሳሳይ ጉዳይ ክስ የተመሰረተባቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች በሰባት ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ከተወሰነ በኋላ፣ ፖሊስ ይግባኝ በማለቱ ተጨማሪ የአስር ቀን የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

Via Balderas

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator