አቻምየለህ ታምሩ

እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን፤ ይልቁንም ታላላቅ የግዕዝ ሊቃውንት የሆኑት እነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌና ከሣቴ ብርሀን ተሰማ የጻፏቸውን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ዋቢ በማድረግ እሬቻ ቃሉ አማርኛ መሆኑን በትናንትናው እለት የጻፍሁት ጽሑፍ ብዙ የኦሮሞ ብሔርተኛ ዶክተርና ፕሮፈሰሮች ጥንቢራቸው እስኪዞር ድረስ በጥላቻ እስንዲሰክሩ፣ ጺማቸውን እየነጩ ጨጓራቸው እንዲቃጠልና ነርቫቸው እንዲነካ ያደረገ ይመስለኛል። አንድ ሰው በጥላቻ የሚሰክረው፣ በንዴት ጨጓራው የሚቃጠለውና ነርቩ ተነክቶ ለስድብ የሚጋበዘው እውነት ሳይኖረው ሲቀና በጥሞና የሚያቀርበው ሀቅ ሲያጣ ብቻ ነው።

እውነት ያለው ሰው ለተነሳው ተጠየቅ አለኝ የሚለውን በማስረጃ የተደገፈና አመክንዮ ያለውን መከራከሪያውን ይዞ ይመጣል እንጂ እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን መጻፌ ለኦሮሞ ጥላቻ ያለኝ አድርጎ ሊያቀርበው። የአገራችን ብሔርተኞች የሚፈጥሩትን ዝባዝንኬ ተረት ለሚተችባቸው ሰው የሚሰጡት ብቸኛ መለስ ለዚህ ነገድ፣ ለዚያ ጎሳ ጥላቻ ስላለህ ነው የሚል አፍ ማዘጊያ ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች ግን ይህ አፍ ማዘጊያ ዘዴያቸው የተባነነበት መሆኑን ስለማያውቁ የተባነነበት ያረጀ ጩኸታቸው ደጋግመው ያሰሙናል። የኦሮሞ ያልሆነው የኦሮሞ አለመሆኑ መነገሩ የኦሮሞ ጥላቻ የሚሆነው በኦሮሞ ብሔርተኞች ጭንቅላት ካሰብን ብቻ ነው። የአረብና የላቲን ፊደል የአረብና የላቲን እንጂ አማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ ወዘተ ፊደል አለመሆኑን መናገር ጥላቻ የሚሆነው በኦሮሞ ብሔርተኞች እሳቤ ብቻ ነው።

አሁንም እንደግመዋለን፤ እሬቻ የኦሮሞ ነው የሚል ቢኖር ቃሉ ኦሮምኛ፤ ባሕሉም የቀዳሚው ኦሮሞ የቦረና መሆኑን በማስረጃ ሊያቀርብ ግድ ይለዋል። ትክክለኛው ኦሮሞ ቦረና ስለሆነ የቦረና ያልሆነ የኦሮሞ አይደለም። ቦረና የማያከብረው፣ ቦረና የማይከበር የገርባ እንጂ የኦሮሞ አይደለም። ይህ ኦሮሞን ከመጥላት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። የአማራ ያልሆነ የአማራ አይደለም መባሉ ጥላቻ እንደማይሆን ሁሉ የኦሮሞ ያልሆነውም የኦሮሞ አይደለም መባሉ ጥላቻ ሊሆን አይችልም። የኦሮሞ አይደለም የተባለውን እሬቻን ቃሉ ኦሮምኛ መሆኑን፤ ባሕሉም ኦሮሞ የእርሻ ስራን በወረራቸው አካባቢዎች ካገኛቸው ነገዶች ከመማሩ በፊት በዘላልነት ዘመኑ ያከብረው እንደነበር ማሳየት እንጂ የኦሮሞ ጥላቻ ነው በማለት ብቻ እሬቻን ኦሮምኛና የኦሮሞ ማድረግ አይቻልም።

አሁንም እንናገራለን! እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ፤ በዓሉንም ከሁሉ በፊት እሬቻን ሊያከብሩት የሚገባቸው ገርባዎች ሳይሆኑ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ቦረናዎች መሆን ነበረባቸው። ያልተበረዘው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና የማያከብረው በዓል የኦሮሞ በዓል አይደለም። ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና እሬቻ “የገርባ በዓል” እያለ ነው የሚጠራው። በኦሮሞ ጥናት ጥርሳቸውን የነቀሉት እነ ኸርበርት ሌዊስ ሸዋ ውስጥ የሚከበረው እሬቻ ቦረና ውስጥ እንደማይታወቅ ነው የነገሩን።

ባጭሩ እሬቻ የገርባ እንጂ የኦሮሞ ባሕል አለመሆኑን ለማወቅ ቃሉ አማርኛ እንጂ ኦሮምኛ አለመሆኑን፤ ባሕሉም በእርሻ የሚተዳደሩ አራሾች በዓል እንጂ የከብት አርቢዎች በዓል አለመሆኑን፤ በዓሉ ኦሮሞ የእርሻ ስራን ከመልመዱ ዘመና በፊት ዛሬ በሚከበርበት በደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ በአማሮች ሲከበር የኖረ በዓል መሆኑን፤ ገርባው እንጂ ያልተበረዘውና ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ቃሉንም ሆነ በዓሉን የማያውቀው መሆኑን፤ ይልቁንም እሬቻ ሲከበር የኖረው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ከሚኖርበት 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው።

ቦረና የማያከብረውን በዓል ገርባው የኦሮሞ ነው ብሎ ማክበሩ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ገርባው ኦሮሞ አለመሆኑን ብቻ ነው። እሬቻ የኦሮሞ ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ ይሆን ነበር፤ በዓሉም በገርባው ምድር ሳይሆን ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነ ቦረና በሚኖርበት በቦረና ምድር እንጂ ቦረና ከሚኖርበት አካባቢ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ገርባ እንጂ ቦረና በማይኖርበት ምድር በሸዋ ውስጥ አይከበርም ነበር።

ዛሬ የማወሳችሁ ሌለኛው ታሪክ እሬቻ ብቻ ሳይሆን ገዳም የኦሮሞ ሥርዓት አለመሆኑን የሚያሳይ ነው። የገዳ ሥርዓት የባንቱ የወረራ ሥርዓት ነው። ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን የወረሰው ከባንቱ ነው። ይህን ታሪክ የሚነግረን በኦሮሞ ጥናት ግንባር ቀደሙ ተመራማሪ፣ የኦሮሞ ብሔርተኛ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮች ሁሉ እሱን ሳይጠቅሱ አንድ የጻፉት ታሪክ የማይገኝላቸው ፕሮፌሰር ኢኔርኮ ቸሩሉ ነው። ፕሮፌሰር ኢኔርኮ ቸሩሊ ይህን ታሪክ የሚነግረን እ.ኤ.አ. በ1543 ዓ.ም. በአርብኛ ቋንቋ የተጻፈውን ቱህፋት አል ሙዘንጂን ተርጎሙ ባዘጋጀው መጽሐፍ ውስጥ ነው።

ፕሮፈሰር ቸርሉ የተረጎመው ቱህፋት አል ሙዘንጂ የተጻፈውን የአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ*ን ከመጻፉ አስርት ዓመታት በፊት ሲሆን መጽሐፍ የአካባቢው ቀደምት ታሪክ የተመዘገበበት በጥንት ጊዜ የተጻፈ የሰነድ ማስረጃ ነው። በዚህ ቸሩሊ እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. በጣሊያንኛ ቋንቋ አርሞ ባሳተመው [ታሪኩን ዣን ዶሬስ እ.ኤ.አ. በ1971 ዓ.ም. ወደ ዘፈረንሳይኛ ተርጉሞታል] መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው ታሪክ እንዲህ ይላል፤

“ዛሬ ሱማሊያ በሚባለው ምድር ሱማሌ ጋን ተካ። መጀርቲን በሚባለው አካባቢ አንድ መዘክር ወይም የጥንት መጽሐፍ ይገኛ። ይህም ሰነድ ዑባያ በተባለ አካባቢ በሱማሊኛ Galka’yo (ጋል ካ አዮ) የተባለ ቦታ እንዳለ ይጠቅሳል። የቦታው ትርጉም “ጋሎች የለቀቁት [ቦታ]” ማለት ነው… ከሰሜን ምስራቅ የመጣ የጋ* ሕዝብ ከመቶ ዓመት በላይ ከዘለቀ ትግል በኋላ ባንቱን ከማዕከላዊ ሱማሊያ አስወጣ። ብዙውን ወደ ራሱ አዋህዷል። የገዳ ሥርዓትን የወረሰው ከባንቱ ነው። ሶማሌ ጋላን ወግቶ ከሱማሌ አስወጣ። ጋ [ከባንቱ በወረሰው] የገዳ ሥርዓት በመጠቀም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ከፍተኛ መሬቶች ወረረ”

[ምንጭ፡ Enerico Cerulli, Somalia I (1957); Somalia II (1959), Rome (Italian Version), Jean Doeresse: A Short Hisrory of the horn of Africa, Holland(Translated from the French Version: Histoire Sommaire de la Corne Orientale de l’Afrique (1971) P.138]

ፕሬሰፈር ቸሩሊ ካዘጋጀው ከዚህ የታሪክ መጽሐፍ እንደምናነበው ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ የወረሰው እንጂ የራሱ ሥርዓት አይደለም። ባጭሩ የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ አይደለም። ይህን ታሪክ እኔ የፈጠርሁት ተረት ተረት አይደለም። ይህ ታሪክ እኔ ከመታሰቤ ከአምስት መቶ አመታት በፊት በ1543 ዓ.ም. የተመዘገበ የጥንት ታሪክ ነው። ታሪኩም የተጻፈው በአረብኛ ቋንቋ በዘመኑ የተዋጣለት የታሪክ መዝጋቢ ነው። የመጽሐፉም ርዕስ ቱህፋት አል ሙዘንጂ ይባላል። የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ ሥርዓት እንዳልሆነ የነገረንን ይህን ቱህፋት አል ሙዘንጂ መጽሐፍ መሞገት እንጂ እኔን ይህን ታሪክ አንብቤ ያገኘሁትን እውነት ያጋራሁትን ሰው የተመዘገበውን እውነት ከላይበራሪ ወደ መድረክ በማምጣቴ የኦሮሞ ጥላቻ እንዳለብኝ መቀስቀሱ ርባና የለውም። በግልባጩ ኦሮሞ እውነት ሲነገር አይወድም ብሎ እንደመናቅም ይቆጠራል።

በመሆኑም የገዳ ሥርዓት ኦሮሞ ከባንቱ የወረሰው እንጂ የኦሮሞ ባለመሆኑ በዩኔስኮ ጭምር መመዝገብ ያለበት በባለቤቱ በባንቱ ሕዝብ ስም እንጂ ሥርዓቱን ከባንቱ በወረሰው በኦሮሞ ስም መሆን የለበትም። የባንቱን ሥርዓት ኦሮሞ ሊወርስ ይችላል። ሆኖም ግን የባንቱን ሥርዓት የኦሮሞ ሥርዓት አድርጎ ማስመዝገብ ስርቆት ነው። የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ ሥርዓት አለመሆኑን የሚያስረዳ የጥንት ሰነድ ከላይበራሪ ወደ መድረክ በማምጣቴ የሚቆጣ፣ የኦሮሞ ጥላቻ እንዳለብኝ የሚቀሰቅስ ግዝብተኛ ቢኖር የሌባ ዐይነ ደረቅ ብቻ ነው። ጎበዝ ነኝ፤ አውቃለሁ የሚል የኦሮሞ ብሔርተኛ የታሪክ ምሁር ቢኖር የገዳ ሥርዓት ኦሮሞ ከባንቱ የወረሰው አለመሆኑን የሚያስረዳ እ.ኤ.አ. በ1543 ዓ.ም. እንደተጻፈው ቱህፋት አል ሙዘንጂ አይነት የታሪክ ማስረጃ በማቅረብ ይሞግት። ከዚህ ውጭ እውነት ስለተነገረ ኦሮሞና አማራ የሚጣላ፤ አገር የሚፈርስ አድርጎ የሚያቀርብ ቢኖር ሕዝብን እውነትን የማይሻ አድርጎ የሚንቅ ግብዝ ብቻ ነው።

ባጭሩ እሬቻ የገርባ፤ የገዳ ሥርዓትም የባንቱ እንጂ የኦሮሞ አይደሉም! ይህን የማይቀበል ቢኖር እሬቻ ኦሮምኛ ኦሮምኛ መሆኑን፤ ገርባ ብቻ ሳይሆን ቦረናም የሚያከብረው በዓል መሆኑን፤ የገዳ ሥርዓትንም ኦሮሞ ከባንቱ በፊት ይጠቀምበት እንደነበር በማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ እንደወረሰው በተጨማሪ ለማወቅ አሁን ስንተኛው ገዳ በስልጣን ላይ እንደሆነ ማየት ይቻላል። ከአራት አመት በፊት የቦረናን አባገዳነት ድል ባለ ድግስ የተረከበው አባ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ነው። [ምንጭ፡ https://www.opride.com/2017/03/08/meet-kura-jarso-new-borana-abba-gadaa/] አባገዳ ኩራ ጃርሶ የቦረና 71ኛው አባ ገዳ ነው። የአንዱ አባ ገዳ ዘመን 8 ዓመት ስለሆነ 71 አባ ገዳ ማለት የመጀመሪያው አባ ገዳ ሥልጣን የያዘው ከ568 ዓመታት በፊት የተሾመ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ይህ ማለት የመጀመሪያው አባገዳ የተሾመው በ1446 ዓ.ም. ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ከ1446 ዓ.ም. በፊት ኦሮሞ በገዳ ሥርዓት አይነታደርም ነበር ማለት ነው። ይህ ማለት ኦሮሞ የገዳን ሥርዓት ከባንቱ ወርሶ በገዳ ሥርዓት መመራት የጀመረው በ1446 ዓ.ም. አካባቢ ነው ማለት ነው። ኦሮሞ ከ1446 ዓ.ም. በፊት በገዳ ሥርዓት በፊት ይተዳደር ነበር የሚል ካለው አሁን በስልጣን ላይ ያለውን 71ኛውን የቦረና አባገዳ እየካደ ነው ማለት ነው።

ከታች የታተሙት ሁለት ገጾች ከላይ በትርጉም ያቀረብሁትን ታሪክ የሚያሳዩ ናቸው። የመጀመሪያው ገጽ ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ እንደወረሰው የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት ይኖርበት የነበረው ጋል ካ ዮ የት እንደሚገኝ የሚያሳይ የካርታ ማስረጃ ነው። ሁለቱም ከተጠቀሰው ዶሴ በተመለከተው ገጽ የሚገኙ ናቸው።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator