ለኦረሞ ሰጠናችሁ እንሄዳለን የተባለው ደርሶ ፣ የዐማራ ሞት ምንም ስሜት የማይሰጣቸውን ዛሬም በመንግስት መዋቅር ቁንጮ ላይ ሆነው ስናይ በራሳችን ድክመት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። የራሳችን ድክመት ማለት ለዓመታት በዐማራው ላይ የተካሄደው የዘር ጭፍጨፋ ሊቆም ይገባል ብለን በአንድ ላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ መነሳት አለመቻላችን ነው። የማማ. ባልደረቦች ” አብን የጠራው ሰልፍ ውጤት ነበረው ወይ ” ? በሚል ውይይት አድርገናል ። ሰልፉ በእገታ እንዳይካሄድ ቢደረግም ውጤታማነቱ ብአዴንን እና የማዕከላዊ መንግስትን እራቁቱን የቆመ ነው። ምክንያቱም በያንዳንዱ ዐማራ አምሮ እና ልብ ውስጥ ብልፅግና ኢህአዴግ ኦሮሞን የምትመስል ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በግልፅ እንዲቀመጥ የሚያደርግ ስለሆነ ። ማማ የውይይት መድረክ የዐማራውን ህዝብ ወደ ከፍታ ማምጣት እና እራሱንም ፣ አገሩንም ከአጥፊዎች መከላከል የሚችልበት ቁመና ኖሮት ኢትዮጵያን ሰላም ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ እንዲሰለፍ አስተዋጽዖ ማድረግ ነው ። የማማ ውይይት ይደርሶ ዘንድ ሸር ሊክ ወይም ተከታይ የሚለውን ይጫኑ ። ተሳታፊ ይሆኑዘድ የሁልጊዜ ግብዣችን ነው።