የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ( ፋኖ ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ!

ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል ( ፋኖ ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠው ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው:_

ከዛሬ ሃምሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ አማራው በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ካለው በጎ አስተዋፅኦ በተቃራኒ በስሁት የታሪክ
ትንተና እና የፈጠራ ትርክት ላይ የተመሰረተ የስም ማጠልሽት ፕሮፖጋንዳ ተሰርቶበታል።

በህወሃት-ኢህአዴግ መሪነት ለሃያ ሰባት ዓመታት መዋቅራዊ ቅርፅ እና ህገ-መንግስታዊ መሰረት ያገኘው ይህ ፀረ-አማራ ፕሮጀክት አማራው በማንነቱ ላይ ለተመሠረተ ጥቃት እንዲጋለጥ አድርጎታል።

በዚህም ምክንያት በህዝባችን ላይ ያልተቋረጠ ጅምላ ግድያ፣ የዘር ማጥፋት እና ማፈናቀል
ተካሂዷል። እየተካሄደም ነው።

በተለይም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ክልሎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የዘር ማጥፋት
ተፈጽሞበታል፤ እየተፈጸመበትም ነው።

እንዲሁም አማራ ክልል በሚባለው ግዛት ውስጥም በከሚሴ፣ በጎንደር፣ በሸዋሮቢትና በአጣየ ለተመሳሳይ ጥቃት እንዲጋለጥ ከመደረጉም በላይ አጣዬና ሸዋሮቢትን ጨምሮ የአማራ ከተሞች እንዲወድሙ ተደርገዋል።

ከጥቂት አመታት በፊት በከፍተኛ ሕዝባዊ ትግልና መስዋእትነት ከማዕከላዊ የመንግስት ሥልጣን የተወገደው ሕወሃት እንደገና
አንሰራርቶ በቂ ዝግጅት እና ትጥቅ በሌለው በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ባደረገው ወረራ ሰሜን ወሎን፣ ደቡብ ወሎን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ሰሜን ጎንደርን እና ሰሜን ሸዋን ለማውደምና ለመዝረፍ በቅቷል።

ወራሪው ኃይል የጅምላ ጭፍጨፋ ከማካሄዱም በላይ በእናቶቻችን ፣ በእህቶቻችን እና በልጆቻችን ላይ የመድፈር ተግባር ፈፅሟል።

ቤተ-እምነቶችን ደፍሯል፤ ብዙ የታሪክ ቦታዎችን እንዳልነበሩ ለማድረግ ችሏል።

በቅርቡ የአማራ ክልል አስተዳደር ወራሪው ያደረሰውን ውድመት አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ዩንቨርስቲዎችን ጨምሮ
በትምህርት ተቋማት ላይ፣ በዋና ዋና ሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች ላይ እንዲሁም ሌሎች የእምነትና የልማት ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት የክልሉን ኢኮኖሚ ለበርካታ ዓመታት ወደኋላ እንደመለሰው ማመን ይቻላል።

ይህንን የአማራ መከራ ለመቀልበስ ግንባር ቀደም በመሆን ከወራሪው ጋር በመፋለም ከፍተኛ መስዋእትነት በየቀኑ በመክፈል ላይ ላሉት የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ዛሬም እንደትናንትናው ከፍተኛ አድናቆት ያለን መሆኑን እንገልፃለን።

ትናንት ደብረሲና ደርሶ የነበረው የሕወሃት ወራሪ ኃይል በወገን ጦር ተጋድሎ ዛሬ ወደመጣበት እየተመለሰ ቢሆንም፤ ገና ያልተለቀቁ
በጎንደርና በወሎ ያሉ የአማራው አጽመ እርስቶች አሉ።

በወያኔ የተተከለው የአፓርታይድ ሥርአት እስካልተወገረ፣ በተለይም
የወያኔ የጥፋትና ጥላቻ ድርጅት ከኢትዮጵያ ምድር ሙሉ በሙሉ እስካልጠፋ ድርስ የአማራ ሕዝብ ሌላ አውዳሚና ህልውናውን
አደጋ ላይ የሚጥል ተደጋጋሚ ወረራ እና ፖለቲካዊ ክህደት እንደማይፈፅልምበት ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም።

ይልቁንም በግራም በቀኝም ካሉ ጠላቶቻችን ባህሪ መረዳት የሚቻለው ህዝባችን ዛሬም ከአደጋ የፀዳ የፖለቲካ አየር ለመተነፈስ የሚችልበት ግዜ ያልደረሰ ስለመሆኑ ብቻ ነው።

ስለሆነም አማራው ከምንጊዜውም በበለጠ ጠንክሮ ከመደራጀት እና ከመሰልጠን እንዲሁም ከትንሽ እስከትልቅ ድረስ የጠላቶቻችንን ቀመር በጥልቀት እየመረመረ እንደ ህዝብ ለመኖር፣ እንደ ሀገር ለመቀጠል
እራስን ከማዘጋጀት ውጭ የተሻለ አማራጭ የለውም።

በዚህ ጦርነት ውስጥ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ያለውን የፋኖ ገድል ስንመለከት መደራጀት እና መሰልጠን የህዝባችንን ህልውና
በማስከበር ረገድ ያለውን የማይተካ ሚና በአግባቡ መገንዘብ እንችላለን።

ይህ ኃይል የስንቅ፣ የትጥቅና የትራንስፖርት ችግር
ቢኖርበትም በዚህ ጦርነት በሁሉም አውደ ውጊያወች ከአማራው ሕዝብ ጠላት ጋር ተናንቋል፤ እየተናነቀም ይገኛል።

ፋኖ በባዶ እግሩ፣ በባዶ ሆዱ፣ ያለበቂ አልባሳት፣ ያለበቂ ትጥቅ፣ አጋዥ ሕክምና ሳይኖረው፣ በራሱ ወጭ ሥራውን፣ ቤተሰቡን ትቶ ለወገኑ
እየተዋደቀ ያለ የነፃነታችን ቀንዲል ነው።

ስለሆነም ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበትን የአማራውን ህልውና ለማስከበር ቆመናል የሚሉ በውጭ ሀገር ያሉ ድርጅቶችን ጨምሮ
አቅሙ እና ፍላጎቱ ያለን ሁሉ ይህንን ኃይል በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብ እና በሞራል የመደገፍ የውዴታ ግዴታ አለብን።

ይህን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ ለመተግበር ይቻል ዘንድ ተጠሪነቱ አገርቤት ላለው ለዋናው ድርጅት ለአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የሆነ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

በዚህም መሠረት ኮሚቴው የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ / Amhara Popular Force (Fano) Foreign Affairs Committee
2 [email protected] Phone: +1 301 264 5673

የአማራ ህዝባዊ ኃይል የውጭ ግንኙነት እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች የሚመራ አካል ለማቋቋም የተጠራ
ጠቅላላ ምክር ቤት ታህሣሥ 3 ቀን 2014 ዓ.ም (December 12, 2021) የምስረታ ጉባኤዉን አድርጎ 13 የስራ አስፈፃሚ
አባላትን መርጧል።

የሰባት የሥራ ዘርፍ መሪዎችን እና አባላትን ያካተተው ይህ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለታላቅ አላማ ታላቅ
ሀላፊነትን ተቀብሎ ስራ ጀምሯል።

በሥራ አስፈጻሚ አጀንዳ ቀራጭነት የአማራውን የህልውና ትግል በእውቀትና በፖሊሲ
ዝግጅቶች የሚያግዝ ምሁራን የተሰባሰቡበት የጥናት እና አማካሪ ቦርድ ቀደም ብሎ ተቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ በቀጣይነትም
እራሱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ወስኗል።

በተጨማሪም የፋይናንስ እና የሚዲያ ቅስቀሳ ኮሚቴውዎችም በሥራ
አስፈጻሚው ስር ተካትተው እንዲቀጥሉ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የውጭ ጉዳይ ኮሚቴውም በተዋረድ መዋቅር ዘርግቶ መሥራት እንዲችል በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካ በስፋት የማደራጀት ሥራ በእቅድ ያከናወናል።

ስለዚህ በውጭው ዓለም የምትኖሩ የአማራ ወገኖቻችን እና የትግላችን ደጋፊዎች በየውጭ ጉዳይ ኮሚቴው በየእርከኑ ለሚፈጥራቸው አካላት በአባልነት እንድትሳተፉ፣ በገንዘብ፣ በእውቀት እና በሞራል ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ጎን
እንድትቆሙ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

ከአማራ ህዝባዊ ኃይል ( ፋኖ ) ጎን በመሰለፍ የአማራን ህልውና እናረጋግጣለን!!!

አማራ በረጅሙ ያሸንፋል!!!
ታህሣሥ 16 ቀን 2014 ዓ/ም
ሰሜን አሜሪካ

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator