ባህር ዳር ላይ ታፍኖ ለቀናት ደብዛው እንዲጠፋ የተደረገው አሸናፊ አካሉ፣ በተወካዩ በኩል
አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ አቅርቧል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 10 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ
ባህር ዳር ላይ ታፍኖ ለቀናት ደብዛው እንዲጠፋ የተደረገው አሸናፊ አካሉ፣ በተወካዩ በኩል
አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለባህር ዳር ከፍተኛ እና ለወረዳ ፍ/ቤት የቀረበለት መሆኑ ታውቋል።
አቤቱታው የቀረበው በታላቅ ወንድሙ መምህር ሳሙኤል አካሉ በኩል ሲሆን የተጠየቀው ዳኝነትም አሸናፊ አካሉ:_
1) ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተገዶ የታሰረ እና
2) ያለበትም የማይታወቅ፣
3) እስከ አሁን ድረስ ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ በወንጀል መጠርጠሩም ይሁን ክስ ያለበት ስለመሆኑ ያልተነገረው እንዲሁም
4) ከቤተሰብ ጋርም ሳይገናኝ ከህግ ውጭ በህግ ስም ታግቶ ስለሚገኝ አካሉ ነጻ እንዲወጣ የሚጠይቅ ነው።
ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለባህር ዳር ወረዳ ፍ/ቤት የቀረበው አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ እና ተያያዥ ጉዳዮች በተናጠል የተመላከቱበት ከስር ተያይዟል።
1)
ቀን 10/05/2015 ዓ.ም
ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት፣
ለባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ባህር ዳር
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 177 መሰረት የቀረበ አካል ነጻ ይውጣልኝ አቤቱታ ነው የቀረበ
አመልካች…….አሸናፊ አካሉ አበራ
ተጠሪ………..የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን
ሀ. ከሳሽ የህግ ችሎታ አለኝ
ለ.ክሱን የማቀርበው በተወካይ ነው
ሐ.ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጠን አለው
የአቤቱታው ዝርዝር:_
አመልካች በቀን 07/05/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከሚገኘው ቤቱ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን አባለት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተገዶ የታሰረ እና ያለበትም የማይታወቅ ሲሆን እስከ አሁን ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ በወንጀል መጠርጠሩም ይሁን ክስ ያለበት ስለመሆኑ ሳይነገረው ከቤተሰብ ጋርም ሳይገናኝ ተገዶ ታስሮ ይገኛል ስለሆነም ተጠሪ ከህግ ውጭ አመልካችን አግቶኝ የሚገኝ ስለሆነ አካሌ ነጻ እንዲወጣልኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 177 መሰረት እጠይቃለሁ፡፡
የምንጠይቀው ዳኝነት:_
ከህግ አግባብ ውጭ ታስሬ የምገኝ በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 177 አካሌ ነጻ እንዲወጣልኝ እጠይቃለሁ።
የቀረበው አቤቱታ በአውነት የቀተበ ለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 መሰረት አረጋግጣለሁ፡፡
አመልካች አሸናፊ አካሉ አበራ
2)
ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት፣
ለባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ባህር ዳር
አመልካች…….አሸናፊ አካሉ አበራ
ተጠሪ………..የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 223 መሰረት የቀረበ
የማስረጃ ዝርዝር
የሰው ማስረጃ ዝርዝር
1.መላክ አዘንጋው አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 14
- ሰላም መኩ ›› ›› ››
- ምናለ አዘንጋው ›› ››
የቀረበው የማስረጃ ዝርዝር በእውነት ቀረበ ለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 መሰረት አረጋግጣለሁ
3)
ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት፣
ለባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ባህር ዳር
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 205 መሰረት የቀረበ ቃለ መሃላ
አመልካች…….አሸናፊ አካሉ አበራ
ተጠሪ………..የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን መካከል ባለው የአካል ነጻ ይውጣልኝ አቤቱታ
አመልካች በተጠሪ ያለ ምንም የወንጀል ምርመራ ተገዶ የታሰረ ስለመሆኑ ያቀረብነው ማመልከቻ በእውነት ቀረበ ለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 205 በቃለ መሃላ እናረጋጣለን፡፡
አመልካች አሸናፊ አካሉ አበራ