አሳዛኝ ዜና!

በዲጋ ወረዳ ጅርማ ቀበሌ በግፍ ከተገደለች ሶስት ቀን ከሞላት እናቷ ጋር ወድቃ በሕይወት የተገኘችው የ2 ዓመት ህጻን ልጅ አባትም ታረዱ።

የአማራው የደም መሬት እየሆነ ባለው ኦሮሚያ ክልል የአማራው ጉዳይ ሲታሰብ ዜጎችን በእኩልነት አይቶ የህግ የበላይነትን በማስከበር መብት፣ሰላም፣ ደህንነትና ልማቱን ሊያረጋግጥለት የሚችል አካል ገና አልተገኘለትም።

በተለይም ከወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን
በዲጋ ወረዳ ጅርማ ቀበሌ በአማራዎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተጠቃሽ ነው።

በጅርማ ቀበሌ በግፍ ከተገደለች ሶስት ቀን ከሞላት እናቷ ከወ/ሮ መልካምአየሁ(ታምሬ) አስከሬን ስር ወድቃ በሕይወት የተገኘችው የ2 ዓመት ህጻን ሁላገር ተካ ሞገስ ሁኔታን መስማት ብዙዎችን አሳዝኗል።

ህጻን ሁላገር ተካ ከአንገቷ እና ከትክሻዋ ላይ በስለት ከወጓት በኋላ ሞታለች ብለው ጥለዋት ሄደው እንደሚሆን ተገልጧል።

ዘግይቶም ቢሆን መከላከያ በጅርማ ቀበሌ ተገኝቶ ከእናቷ አስከሬን ለይቶ ያነሳት ህጻኗም ያለበቂ ህክምና በዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ ትገኛለች።

ጥቃቱን ተከትሎ ከቤተሰብ ተለያይተው በሌላ አቅጣጫ ሸሽተው የነበሩት የህጻኗ አባት አቶ ተካ ሞገስም ከልጆቻቸው ጋር ለመገናኘት ጓጉተዋል።

በመሆኑም ህዳር 10 ቀን 2014 ከጅርማ ቀበሌ መንደር 42 ተነስተው
የድንጋይ ክሰል በሚያመላልስ የጭነት መኪና ተሳፍረው ጉዞ ጀምረዋል።

ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር አብረው የተሳፈሩት አቶ ተካ ልጆቻቸውና ብዙ ሽህ ተፈናቃዮች ወዳሉበት ወደ አርጆ ጉደቱ እየተጓዙ፣ ሰባተኛ በተባለ አካባቢ ሲደርሱ ነበር አራጆቹ የጠበቋቸው።

በወቅቱም አቶ ተካ ሞገስን ከኦሮሞዎቹ ለይተው ከመኪና በማስወረድ ወደ ጫካ ወስደው በአሰቃቂ መልኩ ያረዷቸው መሆኑን ከተፈናቃይ ወገኖች ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

በቀናት ልዩነት ባል እና ሚስት በስለት ደጋግማ የተወጋች የሁለት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ሌሎች ልጆቻቸውን በወጉ ሳይሰናበቱ በግፍ በመገደላቸው ላይመለሱ አሸልበዋል።

ህዳር 2 ቀን 2014 ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቹ በአማራ ላይ በደመ ነፍስ በፈጸሙት ጭፍጨፋ በትንሹ ከ15 በላይ አማራዎች ተገድለዋል፤ ከመካከላቸውም ከ6 የማይበልጡ ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል፤ የበርካታ ተፈናቃዮች አድራሻ የት እንደሆነ አልታወቀም፤ ሽህዎች ተፈናቅለው ከአርጆ ጉደቱ እንዳይወጡ ተከልክለው ያለበቂ ሰብአዊ ድጋፍና መጠለያ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

የዲጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታከለ እና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ሙላት የመንግስትን ደመወዝ እየበሉ አማራን በማስገደል የአሸባሪውን ኦነግ ሸኔን ተልዕኮ እያስፈጸሙ ነው በሚል በብዙ ተፈናቃዮች ዘንድ እየተወቀሱ ነው፤ በታዓምር የተረፍነውን ያስገድሉናል የሚል ከፍተኛ ስጋትም አላቸው።

ቅሬታ የቀረበባቸው አስተዳዳሪውና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator