የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን አስተዳደር ባለፉት ዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን አማራ ሕዝብ ላይ በታቀደ መንገድ የዘር ማጥፋትና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አደረገ።

የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪና የሕዝብ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በሰጡት መግለጫ በአካባቢው የአማራ ነዋሪዎች ላይ ባለፉት ዓመታት የተጠና እና የታቀደ በደል ሲፈጽም መቆየቱን አረጋግጠዋል።

መግለጫው ከ30 ዓመታት በላይ አማራ ብሎም ኢትዮጵያ ጠል አቋሙን በግልጽ ሲያሳይ የነበረው አሸባሪው ትህነግን የአገዛዝ ሥርዓት ለማሳካት የቡድን አደረጃጀት ፈጥረው ወንጀል ሲፈጽሙ እንደነበር ግልጽ ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ ተፈላጊ ግለሰቦችንና ግብረ አበሮቻቸውንም ይፋ አድርጓል።

ኮሎኔሉ ይፋ እንዳደረጉት
1ኛ የቀድሞ የዞኑ አሥተዳዳሪ የነበሩ አቶ ኢሳያስ ታደሰ እና በስራቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አቶ ተኪኡ ባህታ እና አቶ ተጠምቀ ጸጋየ

2ኛ በወቅቱ የዞኑ የፀጥታ ዘርፍ ኀላፊ የነበሩት አቶ ተኪኡ ምትኩ በስራቸው አቶ መንግስቱ ሀድጎ

3ኛ በወቅቱ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ የነበሩት አቶ እርስቁ አለማውና በስራቸው አቶ ተከላይ አደባይ

4ኛ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጀኔራል መኮነንና ከፍተኛ ሥልጣን የነበራቸው ጀኔራል ፍስሃ ኪዳኑ ወይም ፍስሃ ማንጁስ የሚል መጠሪያ የነበራቸውና በስራቸው አቶ ሀለቃ ተክሉና ወዲ ኋይሉ

5ኛ በወቅቱ የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪና የፀጥታ መምሪያ ኀላፊ አቶ ግደይ አዛናው በስራቸው መምሐረር ገዛኽኝ ዳኘው፣ አቶ ተስፋሁን መድሃኒየ፣ አቶ ጸጋየ መድሃኒየና ሀለቃ ተክለ ማሪያም ይገኙበታል።

በመግለጫው እንደተጠቀሰው እነዚህ ግለሰቦችና ግብረ አበሮቻቸው ከዚህ በፊት በወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት (ጅምላ ጭፍጨፋ) ፈጽመዋል፤ የተናጠልና የቡድን ግድያ፣ እስራት፣ የሃብት ምዝበራ፣ ማፈናቀልና ማሳደድ እንዲሁም የታቀደ በደል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ናቸው፡፡ በስራቸውም የወንጀሉ ተባባሪ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ይገኙበታል።

ተፈላጊዎቹ የሽብር ድርጊቱን ሲፈጽሙ የሚያሳዩ የዓይን እማኞች፣ የሰነድና የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎች መኖራቸውም ተገልጿል። የምርመራ መዝገቦች በአግባቡ እየተደራጁ እንደሚገኙና ጉዳዩን የሚከተታል የዞን የምርመራ ቡድን መኖሩን ኀላፊው አስረድተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑና በተገኙበት አጋጣሚ ሁሉ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መላ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው መልዕክት ተላልፏል። ከተፈላጊዎቹ መካከል አብዛኛዎቹ በማይካድራና በሌሎች አካባቢዎች በተደረገው ዘርን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተሳተፉ፣ ያደራጁ አሁንም ቢሆን አካባቢው እንዳይረጋጋ የሽብር ሥራ እየፈጸሙ የሚገኙ መኾናቸውም ተመላክቷል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator