በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ፖሊስ ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ የመከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 14 ወጣቶችን አሰረ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 12 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ማርያ ሰፈር አካባቢ ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ “የፋኖን ስም በመጥራት ሆ እያላችሁ ጨፍራችኋል” የተባሉ 14 ወጣቶች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪዎች አገላለጽ የጽንፈኛ ኦነጋዊያንን አካሄድ እንደ መልካም ነገር በመቀበል እያስተናገደ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከእንዲህ ዓይነት መንግስት መንግስት ከማይሸት ህገ ወጥ የአፈና አካሄድ እንዲታቀብ ጠይቀዋል።

የዐይን እማኞች እንደሚሉ ከጆሞ 3 ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትን አክብረው ወደ ሰፈራቸው ማርያም አካባቢ እየተመለሱ እያለ ከታሰሩት መካከል:_

1) 10 የሚሆኑ የማህበረ ስላሴ ቤተ ክርስቲያን አባላት፣
2) 2 እረፍት ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ፣
3) 2 በክፍለ ከተማ በሌላ አካባቢ የተያዙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በድምሩ 14 የሚሆኑ ወጣቶችን ከበዓሉ ጋር በተያያዘ አስሮ ይገኛል።

ከመካከላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው የተባሉ 2 አባላት ጥር 12/2015 ከሰዓት በኋላ ተለቀዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ማርያም ሰፈር ጥር 11/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የጥምቀት በዓልን ሲያከብሩ የነበሩ 14 ወጣቶች ስለምን ታሰሩ ብሎ የዐይን እማኞችን አነጋግሯል።

የዐይን እማኞች እንደሚሉት:_

1) ዱላ ይዛችሁ ሆ እያላችሁ ጨፍራችኋል፣

2) በጭፈራው መሀልም የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን እና አርበኛ መሳፍንት ተስፉን፣ የጄኔራል አሳምነው ጽጌን ስም በመጥራት ና በለው ፋኖ ብላችኋል፣

3) ማህበረ ስላሴ አሳትሞ የለበሰውን ቲሸርት 7 ቁጥር ስላለው ብቻ ግንቦት 7 ናችሁ፣

4) የማርያም ሰፈርን ባጅ ይዛችሁ ለምን ወደ ጆሞ 3 ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ? የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎችን በማንሳት በማርያም ሰፈር ባለ ፖሊስ ጣቢያ አስረዋቸዋል።

የታሰሩት ሁሉ አማራዎች ናቸው የሚሉት ምንጮች ይህም የሚያሳዬው እነ አብይ አህመድ፣ አዳነች አበቤ እና ሽመልስ አብዲሳ በበላይነት የሚያሽከረክሩት አገዛዝ የአማራ ጥላቻ የማይፋታው መሆኑን ነው በማለት ቁጣቸውን በመግለጽ በየጊዜው እየተደረገ ነው ያሉትን የአፈና እስር አውግዘዋል።

ከገብርኤል ወደ ጀሞ ማርያም ሰፈራቸው እየጨፈሩ ሲመለሱ በጅምላ ታፍሰው ከታሰሩት መካከልም:_

1) ደመቀ አቤ፣
2) ኃይሉ ቢምረው፣
3) አዳሙ ቢምረው
የኃይሉ ወንድም
4) ግዛቸው፣
5) ፖሊስ ስሜነህ፣ እየተማረ ያለ፣
6) መርማሪ ፖሊስ ሙሉጌታ፣ጊዜያዊ እረፍት ስላወጣ፣
7) ክፍሌ እና
8 ሲሳይ ባዬ የተባሉ አማራዎች ይገኙበታል።

በተመሳሳይ አበበ ጌታቸው የተባለ ነዋሪ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለው ፎጣ ይዞ በመገኘቱ ብቻ ጥር 11/2015 ጠዋት ላይ ከማርያም ተነስቶ ወደ ጥምቀተ ባህሩ እየሄደ ሳለ አረንጓ ተይዞ አየር ጤና ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ነበር።

ለአንድ ሰዓት ከታሰረ በኋላ ፎጣ ይዞ መገኘት እንዴት ያሳስራል በሚል በፖሊሶች መካከል በተነሳ ክርክር ፎጣውን ቀምተው ከ1 ሰዓት የእስር ቆይታ በኋላ ለቀውታል።

በእለቱም ከያዙት ፖሊሶች መካከል አንደኛው “አንተ ነፍጠኛ ይህን መልበስ ያለብህ ከዓባይ ማዶ ነው እንጅ ከዚህ መልበስ አትችልም!” በማለት ጥላቻውን ሲገልጽ እንደነበር ታውቋል።

በተያያዘ አርሲ ዞን ጀጁ እና አቦምሳ ወረዳዎች ጥምቀቱ በድምቀት የተከበረ ቢሆንም አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ በቤተ ክርስቲያን ጭምር እንዳይያዝ ከተከለከለ ሶስት ዓመት ያለፈው መሆኑ ተገልጧል።

በጀጁ ወረዳ አዲስ ህይወት ሁሩታ ዶሬ፣ ቲቪላ የእርሻ ልማት፣ አጫሞ፣ ተስፋ ህይወት ቀበሌዎች እንዲሁም በአቦምሳ ወረዳ ከመርቲ፣ መንበረ ህይወት እስከ ቦሌ ድረስ የኢትዮጵያ ብሎም የቤተ ክርስቲያን መለያ የሆነው አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ እንዳይያዝ በመከልከሉ ደስተኛ እንዳልሆኑ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator