1)አመት ሙሉ ወራሪ ጠላትን ለመመከት የህይወት መስዋእትነት ሲከፍል የከረመ፣ ንብረቱ የወደመበት፣ ከቀየው የተፈናቀለ፣ በትምህርት ገበታ ላይ ያልከረመን በጦር ቀጠና እየኖረ ያለን ትውልድ፤ ምንም እንከን ሳይገጥመው ለፈተና ተዘጋጅቶ ከከረመ አካል ጋር እኩል ተቀምጠህ ተፈተን ውጤቱንም እኩል ልይልህ የሚል ሃገር ምን የዞረበት ቢሆን ነው?

2)ቁጥር አንድ ያለው ሳይበቃ አንድ ሰፊ ክልል ተማሪዎቹ በተሰረቀ ፈተና እንዲያልፉ በመዋቅር ደረጃ ለስድስት ተከታታይ አመታት ወንጀል ሲፈፀም በገሃድ እየታወቀ በሃገር ደረጃ ወንጀሉ እንዲፀድቅላቸው ሲፈቀድ ምን አይነት እብደት ነው?

3)ከላይ የተጠቀሱት የግፍ አይነቶች አልበቃ ብሎ የፈተናው አተራረም በተግባር የተረጋገጠ ትልቅ ችግር/ስህተት እንዳለበት እየታወቀ ባለቤትነት/ሃላፊነት ወስዶ ትምህርት ሚንስቴር ወጥ የእርምት እርምጃ አለመውሰዱ አሳፋሪ ነው። እስካሁን የምንሰማው ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎችን በተናጠል ለማስተናገድ እየሞከሩ መሆኑን ነው። The problem is systemic, the solution should match that.

4)የአማራ ክልል አስተዳደር የት ነህ? የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ ድምፅህ የት ጠፋ? የአማራ ክልል የዞን ትምህርት መምሪያዎች የት ናችሁ? የዞን አስተዳዳሪዎች አሁን አቋም ካልያዛችሁ ለመቼ ነው???


ከስር የተያያዘው ዋቢ ማስረጃ ሰነድ የሚያሳየው ሰሜን ጎንደር ውስጥ አለፉ የተባሉት ከመቶ ስሌት ከ2% እስከ13% ብቻ ነው። ከ98% እስከ 87% ያክሉ ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ማለፍ አልቻሉም ወድቀዋል ነው የተባለ። ይህን የሚቀበል ሃገር፣ መንግሥት፣ ሕዝብ ሊኖር አይገባም። ትውልድ ገደላ/ጀኖሳይድ ነው!


ሙሉነህ ዮሐንስ

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator