በአማራ ላይ የተከፈተው የተደራጀ መንግስታዊ አፈና፣ እስር እና ወከባ እንደቀጠለ ነው፤ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህር እና የውስጥ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ግርማው አሸብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህር እና የውስጥ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ግርማው አሸብር ግንቦት 16/2014 ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ከሚኖርበት ቤዛዊት ማርያም ኮንዶምኒዬም ግቢ በፖሊሶች ታፍኖ ስለመወሰዱ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

መምህር ግርማው አሸብር በባህር ዳር ቀበሌ 8 ከጋምቢ ጎን ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰረ መሆኑ ተገልጧል።

በፖሊሶች ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደ በኋላ ወደ ውስጥ ክፍል የልዩ ኃይል ልብስ የለበሱ አካላት ይዘውት ሲገቡ ተመልክተናል የሚሉት ቤተሰቦች ለምርመራ ይሁን ወይም ቤተሰብ በማይገኝበት አሳልፈው ወደ ጋይንት ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋታቸውን አጋርተዋል።

መምህር ግርማው አሸብር የ6 ወር ህጻንን ጨምሮ የሁለት ህጻን ልጆች አባት ነው።

መምህር ግርማው አሸብር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ ሲሆን ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ከተዘዋወረ ገና አንድ ዓመት አልሞላውም።

በማህበረሰብ የእሳቤ ለውጥ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ሚዛናዊ፣ ነጻ እና ለሚዲያ ተጋላጭ የሆነ ሰው መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል።

መንግስታዊ አፋኝ ቡድኑ የነቁ እና የበቁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን እያደነ በማፈን ተግባሩ እንደቀጠለበት ነው።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator