በስቡስሬ ወረዳ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታግተው የተገደሉ የ4 አማራዎችን አስከሬን ለመፈለግና ለማንሳት በሄዱበት የታሰሩት አማራዎች ከ146 በላይ መሆናቸው ተገለጸ፤ አሁንም አልተፈቱም፤ መጠየቅም አይቻልም ተብሏል።

በሰምስራቅ ወለጋ ዞን ስቡስሬ ወረዳ ታግተው የተገደሉትን የ4 አማራዎችን አስከሬን ለመፈለግና ለማንሳት በሄዱበት የታሰሩት ከ146 በላይ መሆናቸውን የገለጹት ምንጮች እስካሁን አልተፈቱም፤ ለመጠየቅ የሄዱ እየታሰሩ ነው ብለዋል።

በስቡስሬ ወረዳ ሚያዝያ 30/2014 የጠፋ በቅሎ ፍለጋ በወጡበት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ተገድለዋል የተባሉ የ4 ነዋሪዎችን አስከሬን ለማግኘት በፍለጋ ሳሉ ተኩስ የከፈተባቸውን አሸባሪውን ኦነግ ሸኔን እያሳደዱ በነበሩ በርካታ በሚሆኑ አማራዎች ላይ ከአዋሳኙ ባኮቲቤ የመጣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከበባ በማድረግ ተኩስ ከፍቶባቸው እንደነበር ተወስቷል።

በወቅቱም ብዙ ሰዎች ሮጠው ሲያመልጡ 144 የሚሆኑት መታፈናቸው ተገልጧል።

የኦነግን አላማ ይደግፋሉ የተባሉት የልዩ ኃይል አባላት ግድያ ሳይፈጽሙ መከላከያ ደርሶ የተያዙትን አማራዎች ቆጥሮ ለስቡስሬ ወረዳ አኖ ማስረከቡ ተነግሯል።

መከላከያ ከወረዳ ወረዳ ተሻግሮ ወራሪው ኦነግ ሸኔን ሲፋለሙ በነበሩ አማራዎች ላይ ከጎን ከበባ አድርጎ ጥቃት በከፈተው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ላይ አንዳች ህጋዊ እርምጃ ሳይወስድ የአማራ ገበሬዎችን አፍኖ ለአኖ ወረዳ በማስረከብ በጥፋቱ መተባበሩ አሳዛኝ ነው ተብሏል።

እስረኛ ሊጠይቁ በሄዱበት የታሰሩ 2 ሰዎችን ጨምሮ በጥቅሉ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ 146 አማራዎች በአኖ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፤ ፍትህም እያገኙ አይደለም ይላሉ ነዋሪዎቹ።

ከመካከላቸውም ከ18 በላይ ህጻናት ይገኙበታል፤ ቁጥሩ እየጨመረ መሆኑን የገለጹት የአሚማ ምንጮች የታሰሩትም ሌሊት ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator