0 0
Read Time:2 Minute, 24 Second

“የዜጎች እስር፣ እገታና መሰወር እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም ያለበት ድርጊት ነው! ጀነራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በየአካባቢው የታፈኑና የታሰሩ የፋኖ አባላት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አደርጋለሁ!”

 ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

አሁንም የትህነግ መራሹ የትግሬ ወራሪ ሀይል ለዳግም ወረራ የጦርነት ነጋሪት እየመታ ባለበት በዚህ ወቅት በህግ ማስከበር ስም የፋኖ አባላትንም ሆነ ትጥቅ ያላቸውን ዜጎች በጅምላ ማሰርና ማዋከብ፣ እንዲሁም የማገትና መሰወር ወንጀል በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባው የለየለት መንግስታዊ ውንብድና ነው ብለውታል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በመልዕክታቸው።

ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት:_

ገዢው መንግስት በፓርቲ ሰነዶቹ ላይ በግልጽ እንዳመላከተው ፋኖን ኢ—መደበኛ ኃይል ነው በሚል ፍረጃ ርምጃ እንደሚወስድበት ገልጾ ነበር።

የፋኖን አደረጃጀትና መጠናከር አስፈላጊ ያደረገው ጉዳይ ግልጽ ነበር።

ትሕነግ መሩ የትግሬ ወረሪ ኃይል የአማራ ክልልን ወርሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችን ሲገድል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን በጅምላ ሲደፍርና ከ300 ቢሊየን ብር በላይ የሚደርስ ሀብት ንብረት ሲያወድም የፌደራል መንግስቱም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ይህን አውዳሚ የሽብርና የዘረፋ ሀይል ማስቆም የሚችሉበት ቁመና ላይ አልነበሩም።

የአማራ ወጣቶች በህዝባቸው ላይ የደረሰውን ይሄንን አስከፊ ጥቃት በአይናቸው አይተዋል፣ በደረሰው ነገርም ክፉኛ ተቆጥተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ወረራው አድማሱን ሲያሰፋ መንግስት የትግሬን ወራሪና አውዳሚ መንጋ በመደበኛው የመንግስት የመከላከያና የፀጽታ መዋቅርና አደረጃጀት ማስቆም ስለማይቻል ዜጎች ያላቸውን ትጥቅ ታጥቀው፣ ስንቃቸውን ሰንቀው ወደ ግንባር እንዲዘምቱና ጠላትን እንዲደመስሱ፣ እንዲሁም በምርኮ ያገኙትን መሳሪያ እንዲታጠቁ ጥሪ ማቅረቡም ይታወቃል።

እነዚህ ሁለት የህይዎት ተሞክሮዎች ወይም ገጠመኞች የአማራን ወጣት አስተምረውታል፣ በበጎም ለውጠውታልም።

በርካታ የአማራ ወጣት ወደ መከላከያና ልዩ ኃይል እንዲቀላቀል ከማድረጉም በላይ በየአካባቢው ወታደራዊ ስልጠናዎችን የሚሰጡ የፋኖ አደረጃጀቶችን እንዲያማትር፣ መሳሪያ የመታጠቅና ወደፊት ለሚያጋጥሙ የትግሬ ወረራ ስጋቶች ራሱን እንዲያዘጋጅ ገፊ ምክንያት ሆኖታል።

አሁንም የትህነግ መራሹ የትግሬ ወራሪ ሀይል ለዳግም ወረራ የጦርነት ነጋሪት እየመታ ባለበት በዚህ ወቅት በህግ ማስከበር ስም የፋኖ አባላትንም ሆነ ትጥቅ ያላቸውን ዜጎች በጅምላ ማሰርና ማዋከብ፣ እንዲሁም የማገትና መሰወር ወንጀል በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባው የለየለት መንግስታዊ ውንብድና ነው።

ከዚህ ባለፈም ክልሉ አሁን ካለበት የፀጽታና የደህንነት ስጋት ላይ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚሆንና ይብሱን ወደ አለመረጋጋት እንዳይመራው ስጋት አለኝ። ጉዳዩ ስሱና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ነው።

በርግጥ ከፋኖ አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መቀረፍ ያለበቸው የእዝ ጠገግና ሰንሰለት፣ የተጠያቂነትና ውጤታማ ቁጥጥር እንዲሁም ከመደበኛው የህግ ማስከበር መዋቅር ጋር ያለው መስተጋብርና ትስስር መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባው ጉዳይ ነው።

ፋኖ ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር የጎንዮሽ ወይም እሱን የሚተካ እንዳልሆነና በመደበኛና የእለት ከእለት የህግ ማስከበር ውስጥ ምንም ድርሻ የሌለው፤ ይልቁንም አገርና ህዝብ የደህንነት ችግር ውስጥ ሲወድቁ የራሱን መሳሪያ ታጥቆ ከጠላት ጋር የሚፋለም ሀይል መሆኑን ሰፊ የግንዛቤና የተግባቦት ስራ እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው።

በአጠቃላይ አሜሪካን ጨምሮ በየትኛውም አለም ዘመናዊ ዴሞክራሲዎች መግባባት ላይ እንደተደረሰበትና በአለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት ወደ ማግኜት የደረሰው እሳቤ ጤናቸው የተረጋገጠና የኋላ ታሪክ ምርመራ ያለፉ ዜጎች የተመዘገበ መሳሪያ ታጥቀው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን፣ ሀብትና ንብረታቸውን እንዲሁም አገርና ህዝባቸውን ጭምር የመጠበቅ መብት አላቸው።

አሜሪካውያን second amendement right; the right to bear arms ይሉታል።

መሳሪያ የመያዝ መብት ከመሰረታዊ የሰው ልጆች በህይዎት የመኖር መብት እና ሰርቶ ሀብት አፍርቶ ከመጠቀም እንዲሁም ከነፃነት መብት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የሚተሳሰር እና ሊከበር ወይም ጥበቃ ሊሰጠው የሚገባ መብት ነው።

ቁጥጥር ያስፈልገዋል፤ ቁጥጥሩም ሲሰራ ከዜጎች ጋር በቂ ውይይት ተደርጎበትና ማህበረሰቡን ተሳታፊ ባደረገ መንገድ እንጅ ህዝቡ የጠላት ወረራ ቋፍ ላይ ባለበት ወቅት አይመስለኝም።

ጀነራል ተፈራ ማሞና አሸናፊ አካሉ እንዲሁም ሌሎች በዚህ ሰሞን የታሰሩ ፋኖዎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ችግሮች ካሉም በምክክር ይፈቱ!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator