በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና አካባቢ የኦሮሚያ የጸጥታ አካላት እንቅስቃሴ እና የክምችት መጠን በተለይ ከመጋቢት 20/2014 ጀምሮ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ተገልጧል።

የአውራ ጎዳና እና አካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከመጋቢት 20/2014 ጀምሮ የገባው መከላከያ መጋቢት 22/2014 መነሳቱን አውስተዋል።

መከላከያ ከአውራ ጎዳና መውጣቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ጥምር ኃይል የቡድን መሳሪያ ይዞ ከመተሃራ ወደ ቦሰት አቅጣጫ ከተማዋን ከ6 ጊዜ በላይ ዞሯል፤ ለጠባጫሪነትና ለጥናት ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባን መስመር ጨምሮ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይል በመመጓጓዝ በወረንጭቲ እና በመተሃራ እየሰፈረ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎች በአማራ ክልል በኩል ግን መዘናጋት እየተስተዋለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ በኩል እየተደረገ ያለው ኃይለኛ የሆነ ዝግጅት ነገ ከነገ ወዲያ በተዘናጋ የአማራ የጸጥታ አካል እና ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል እንዳይፈጸም ከፍተኛ ስጋት ስላለን በአስቸኳይ ይህ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አካሄድ ሊወገዝና ሊስተካከል ይገባዋል ሲሉ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ የአውራ ጎዳና ነዋሪዎች ጥሪ አድርገዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator