“በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት በመሳሪያ አፈሙዝ እና በሰደፍ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ በድብደባው ምክንያት ሙሉ ሰውነቴ ቆስሏል፤ የጀርባ አጥንቴ ላይ ህመም ይሰማኛል፤ በእግሬ ላይ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡”

በቀለ ቢራራ ባይህ_

አጣዬ ተይዘው ለአንድ ወር ገደማ በመከላከያ ከታሰሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማቆያ ከተዛወሩት መካከል

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)

ሰኔ 25/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ በኩል ከ38 ተጎጅዎች ተሰብስቦ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የተደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍ/ቤቱ በኩል ተቀባይነት አግኝቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዲመረምር እና ሪፖርቱን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የተሰጠበት መሆኑ ታውቋል።

በአያያዝ እና በእስር ወቅት የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል ያሉ በእነ መላክ ምሳሌ መዝገብ የ16 እና የ12 ሰዎችን በድምሩ የ28 ሰዎችን አቤቱታ በየመዝገባቸው አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከአሁን ቀደም ማጋራቱ ይታወቃል።

በአጠቃላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል በሚል አቤቱታ ያቀረቡ በ3 መዝገቦች እንዲደራጁ የተደረጉ ግለሰቦች 38 ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል የቀሪ አንድ መዝገብ:_

በእነ በቀለ ቢራራ (10 ሰዎች) ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንዲጣራላቸው ያቀረቡትን አቤቱታን ደግሞ ከዚህ እንደሚከተለው አጋርተናል።

የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል ያሉ በእነ በቀለ ቢራራ መዝገብ፣ ከሸዋ አጣዬ የተያዙ።

የእስረኞች ብዛት_10

1ኛ. በቀለ ቢራራ ባይህ፣

2ኛ. ፍቃዱ አሰፌ አበበ፣

3ኛ. ኤርሚያስ ደረሰ ሰፊው፣

4ኛ. ዳንኤል ደምሰው ገሰሰ፣

5ኛ. በላይ ጋሻው አራጌ፣

6ኛ. ሔኖክ መንገሻ ይርጋታ፣

7ኛ. ክብረት ይርዳው ተመቼ፣

8ኛ. ደጉ አያሌው ወርቁ፣

9ኛ. መላኩ ደርብ ንጉሴ እና

10ኛ. ደፋሩ ሰማው ሞላ የተባሉ ከአጣዬ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉ ግለሰቦች ናቸው። አሁን ላይ ከአስሩ መካከል 6 ሲፈቱ 4ቱ ይግባኝ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።

ጉዳዩ፡- ከአያያዝ ጋር በተገናኘ በተፈጸመብን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ እርምጃ

እንዲወሰድ የቀረበ አቤቱታ፤

ግለሰቦች በ21/09/15 ዓ.ም ለችሎት በፖሊስ ተይዘን በቀረብን ወቅት በተያዝን ጊዜ የተፈጸመብን የሰብዓዊ መብት መደፈርና ጥሰት ለፍ/ቤቱ አቅርበን ችሎቱ ጉዳዩን በጽሁፍ እንድናቀርብ ባለው መሰረት ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን:_

1) በቀለ ቢራራ ባይህ:_

ግንቦት 01 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ16 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት በመሳሪያ አፈሙዝ እና በሰደፍ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡

በድብደባው ምክንያት ሙሉ ሰውነቴ ቆስሏል፤ የጀርባ አጥንቴ ላይ ህመም ይሰማኛል፤ በእግሬ ላይ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡

2) ፍቃዱ አሰፌ አበበ:_

ሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ18 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ በድብደባው ምክንያት ሰውነቴ ቆስሏል፤ ማንነትን መሰረት ያደረገ ስድብ ተሰድቤያለሁ፡፡

3) ኤርሚያስ ደረሰ ሰፊው:_

09/09/2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ከዚህ ውስጥ ለ8 ቀን በመከላከያ ካምፕ ውስጥ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡ በተያዝኩበት ወቅት ማንነትን መሰረት ያደረገ ስድብ ተሰድቤለሁ።

4) ዳንኤል ደምሰው ገሰሰ:_

በ03/09/2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ14 ቀን በመከላከያ ካምፕ ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡

በተያዝኩበት ሰዓት ለተወሰነ ሰአት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እጄን በገመድ የኋሊት አስረውኝ ስለነበር አሁን የጀርባ ህመም ይሰማኛል፡፡

5) በላይ ጋሻው አራጌ:_

ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ17 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅትድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡ በድብደባው ምክንያት ሰውነቴ ቆስሏል፡፡

6) ሔኖክ መንገሻ ይርጋታ:_

ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ17 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት በመሳሪያ አፈሙዝ እና በሰደፍ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡

በቆምኩበት በጥይት ክንዴን ተመትቼ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡

7) ክብረት ይርዳው ተመቼ:_

ሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዪ ተይዤ ለ19 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት ልብሴን በማስወለቅ ስለደበደቡኝ ሰውነቴ ቁስል ነው፤ ጆሮዬ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡

8) ደጉ አያሌው ወርቁ:_

ሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ18 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡

በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት በመሳሪያ አፈሙዝ እና በሰደፍ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡

በድብደባው ምክንያት የደረት አጥንቴ ተሰብሮ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡

9) መላኩ ደርብ ንጉሴ:_

07/09/2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ10 ቀን ያህል ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡ በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅት ማንነትን መሰረት ያደረገ ስድብ ተሰድቤለሁ።

10)

ሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አማራ ክልል አጣዬ ተይዤ ለ18 ቀን ያህል በፖሊስ ጣቢያ ታፍኜ ቆይቻለሁ፡፡ በመከላከያ ሰራዊት በተያዝኩበት ወቅትከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡

በድብደባው ምክንያት ጥርሴ ይነቃነቃል ጀርባዬ ላይ ህመም ይሰማኛል፡፡

ስለሆነም የተከበረው ፍ/ቤት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት መደፈር እና ጥሰት ላይ የፌደራል ፖሊስ ምርመራ አድርጎ ለችሎቱ ውጤቱን እንዲያሳውቅ እንዲታዘዝልን እናመለክታለን።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator