ሰኔ 15 በብአዴን አማካኝነት የተፈጠረው ቀውስ ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል እያስከፈለንም ይገኛል።በዚች ሀገር የሚሠሩ የሴራ ፖለቲካዊ ኩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መልካቸውንም አይነታቸውንም እየቀያየሩ ቀጥለዋል። በእርግጥ የሴራ ፖለቲካ (political conspirecy ) በአሁኑ ክፍለ ዘመን የዓላም ፖለቲካዊ አመራር ጥበብ ተደርጎ ብዙ ምርምርና ጥናት የሚደረግበት መመሪያ ሆኗል።ኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሡ ሥርዓት መገረስስ ጀምሮ ያሉ ሀገራዊ ምስቅልቅሎሾችን የፈጠሩ የሴራ ፖለቲካ ሰበዞች በፀረ አማራነት የተከወኑ ሆነው እናገኛቸዋለን።በዚህ ዙሪያ በቀጣይ በሰፊው የምንሄድበት ስለሆነ ለዛሬው የተነሳሁበት አርዕስት ላይ እውነተኛ መረጃዎችን መሠረት አድርጌ ለመፃፍ ወደድኩኝ።
ሰኔ 15 በባህርዳር እና አዲስ አበባ የተደረጉ ኦፕሬሽኖች “መፈንቅለ የአማራ መንግስት “መሆናቸውን የተቀበልኩት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሰክረተሪያት ኃላፊ በብርሃን ፍጥነት ጉዳዩን መፈንቅለ መንግስት ብለው መግለፃቸውን ተከትሎ ነበር።ሰኔ 15 ን ቀውስ የወንድማማቾች መገዳደል ወይም የጎጠኝነት ውጤት አልያም በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የተደረገ በሚሉ ማጠፋፊያዎች የሚታለፍ አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ወቅቱ የአማራ ክልል ለ27 ዓመት አማራ ነን በሚሉ ግን ደግሞ አማራ ባልሆኑ ኢህዴኖች እየተመራ በጭቆና ኖሮ በመጨረሻም በሕዝባዊ እምቢተኝነት የትህነግ አገዛዝ ሲፈራርስ ራሱን ነፃ ለማድረግ የሚታትርበት ነበር።በዚህ ሂደት ያረጁ ያፈጁ ጥቁር አማራዎች ከክልሉ የኅላፊነት ቦታ በጡረታም በሌላም እንዲነሱ በማድረግ በሌሎቹ ወጣቶች እና ህዝባዊነት በተላበሱ አመራሮች ለመተካት ትግል ይደረግ ነበር። በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲመረጡ ሲደረግ የነበረው የህዝቡ ጥቆማና የማሕበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ የአማራ ህዝብ በነፃነት የሚመራበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከማሰብ እንደሆነ ይገባኝ ነበር።ጄኔራል አሳምነው ፅጌም ለዘመናት በእስር ቆይቶ ከተፈታ በኋላ ልረፍ እንኳ ሳይል መሰዋዕትነት የከፈለለትን ህዝብ ለማገልገል የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ የተመረጠው ያኔ ነው።
ትህነግ አማራ ክልልን በሞግዚትነት ስታስተዳድር የነበረው ኢህዴን /ብአዴን ምስለኔዋን ፈጥራ መሆኑ ይታወቃል።በዚህ ሂደት ሙሉ የፀጥታ መዋቅሩ በትህነግ እጅ የወደቀ ስለሆነ የአማራ ወጣቶች ከየትኛውም ቦታ እየተለቀሙ ከቃሊቲ እስከ ባዶ ስድስት መቀሌ ድረስ ይታሠሩ ይሰቃዩ ይገደሉ ነበር።በህዝባዊ እምቢተኝነት ተገዶ ለውጡን ተቀብያለሁ የለውጥም ኃይል ነኝ ያለው አዴፓ ጄኔራል አሳምነው ፅጌን የአማራ ክልል ሰለም ግንባታና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾመው።ይሄንን ሹመትም መላው አማራ በበጎ በማየት ተቀበለው።
ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በአማራ ህዝብ የደረሰውን በደል ተነግሮት ሳይሆን ደርሶበት ያየ የተረዳ፡በፖለቲካውም በሚሊታሪውም የአማራ ህዝብን ክፍተት ጠንቅቆ የተረዳ በመሆኑ ከተሾመበት ቅፅበት ጀምሮ ወደ ሥራ ለመግባት አልቸገረውም።ከተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት እስከ ፋኖ ድረስ እየሰበሰበ በማስልጠን የአማራን የፅጥታ መዋቅር ለማጠናከር ከፍተኛ ሥራ ሠራ።ይሄ ብቻ ሳይሆን የህዝባችንን አጠቃላይ መከላከል(public defence) ለማጠናከር በየአካባቢው ያሉ ሚኒሻዎችንና የታጠቁ ገበሬዎችን ጭምር ለሁለት ሳምንት ያክል ሁለገብ የሚሊታሪ ስልጠናዎች እንዲሰጥ አደረገ።ይሄ በመሆኑ ህዝባችን በጄኔራሉ ሥራ አመኔታ እያሳደረ ያለውን መሣሪያም ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ሆኖ እየተሳተፈ ቀጠለ። በሕልውና ስጋት ውስጥ ላለ ህዝብ የተጠና መውጫ እና ማሸነፊያ መንገዶችን ሁሉ የተረዳው ጄኔራሉ በዚህም ሳያበቃ ሌሎችንም ስልቶች ወደ መተግበሩ ገባ።
የሠለጠነ ሠራዊት ማደረጀቱን እያጠናከረ ቀጥሏል። ህዝባችንን ለራስመከላከል (self defenece) እያዘጋጀ ነው።ከለውጡ በፊት በየበረሃው ለነፃነት ሲንከራተቱ የነበሩትንም እየሰበሰበ የፀጥታ ኃይሉ ውስጥ እያቀፈ ነው። የቀድሞ ሠራዊት ምናምን የሚል ክፍልፋይ የለም እናንተ መደበኛ ሠራዊት ናችሁ ሲል ኢህዴኖች አሸነፍናችሁ እያሉ ለአፍቸው መክፈቻ የሚያደርጓቸው የነበሩ ሀገር ወዳዶችን እጁን ዘርግቶ ተቀብሎ አሠማራቸው። ከክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ያለውን አማራ የስነልቡና ከፍታውን እየጨመረ አንገቱን ቀና እንዲያደርግ ሳይታክት እየሠራ ነበር።
ይሄ ሁሉ ተደርጎ የመረጃ እና ደህንነት ሥራው የተጓደለ ከሆነ ጥሩ ቤት ሠርቶ በር አለመዝጋት ነውና የመረጃ እና ደኅንነት ሥራውን ለተቋሙ ያስፈልጋል በሚል ስልጠና እንዲሰጥ ይወሰናል።ከየቦታው ንቁ የሆኑ የአማራ ልጆች ተመልምለው ባህርዳር ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት ውስጥ ሥልጣናው እንዲወስዱ ስምምነት ላይ ተደረሰ።በዚህ ወቅት ነበረ የአማራ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ የሚችልበት ስንጥቅ ለመፍጠር የሚያስችል ሁኔታ የተፈጠረው።
ስልጠናው ተዘጋጅቶ የተመለመሉ ስልጣኞችም ጥሪ ተደርጎላቸው ባህርዳር ገብተዋል።ስልጠናውን የሚሰጡ አሰልጣኞች ከፌድራል ከክልልም ተፈልገው እንዲመቻቹ ተደረገ።የአማራ ክልል በተለይም የፀጥታው መዋቅር ራሱን እየቻለ ከማዕከላዊ መንግስቱ ሞግዚት አስተዳደር ነፃ መሆኑ እያንገበገባቸው የቆዩ እነ አብይ አህመድ ይሄንን አጋጣሚ ከመጠቀም አላለፉም። አብይ አህመድ ነፈዝ በፌድራል ያሉ ባለስልጣናትን በመጠቀም በትህነግ አመራር ወቅት እንግሊዝ ሀገር የነበረ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የገባ ስመ ብዙ የሆነ አስልጣኝ ወደ አማራ ክልል ላከ። ከዚህ ቀጥሎ የዚህን ስመ ብዙ የአማራ መፈንቅለ መንግስት ማስተር ማይንድ ማንነት ከመጀመሪያው እስከአሁኑ በፍትህ መፅሔት እስከሰጠው ምስክርነቱ እናያለን።
ስሞቹ፦
1 .ዳዊት ተረፈ ወዳጆ (እውነተኛ ስም)
2 .ቃልኪዳን ተረፈ(ሁለተኛ ስሙ)
3 .ቃልኪዳን ግርማ(ውሸተኛ ስሙ)
4 .ቦይዶ ግርማ(Boydo Girma) ውሸተኛ ስሙ ሆኖ ፌስቡክም ይጠቅምበት ነበር
5 .ቲሞቲ(Timoty) =መፈንቅለ አማራ መንግስት የመራበት ገፀ ባህርይ ነው።
ዳዊት ተረፈ ወዳጆ አዲስ አበባ ቂርቆስ ተወልዶ ያደገ ከተሜ ኦሮሞ በመሆኑ ማንነቱን ለመደበቅ ጠቅሞታል።የሂሳብ ትምህርት አስተማሪ ሆኖ ቋራ ከእነ አገኘሁ ተሻገር ጋር በአንድ ትምህርትቤት አስተምሯል።ከዚያ በኋላ የሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም(NGO) ገብቶ እየሠራ እያለ ለሌላ ሰው የመጣን የኢንተለጀንሲ የትምህርት እድል ከአለቃው ጋር በመመሳጠር ራሱ በመጠቀም ራሽያ እንደሄደ የመረጃ ምንጮቼ ይጠቁማል። ዳዊት ተረፈ ወዳጆ ራሽያ ለትምህርት እንደሄደ ጠፍቶ በመቅረት በተለያዩ የውጭ ሀገር የስለላ ተቋማት ይሠራ እንደነበር ምንጮቼ ጠቁመዋል።በለውጡ ዋዜማ እንግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ የሆነ ሬስቶራንት ከፍቶ እየሠራ በማስመሰል ለMI6 ኤጀንት ሆኖ ያገለግል ነበር። እነ አብይ አህመድ ይሄንን ሰው ለራሳቸው ሥራ በለውጡ ማግስት ጠርተው ወደ ሀገር ቤት አመጡት።ዳዊት ተረፈ ወዳጆ አማርኛ ተናጋሪ ኦሮሞ መሆኑን የሚያውቁት እነ አብይ ሰውየውን አማራ ነኝ ብለህ አማራ ክልል ሂድ ብለው ላኩት። ከላይ እንዳልኩት ነፈዝ ብአዴኖች ጠንካራ ልምድ ያለው ሰው ተገኘ በሚል ገዳይን በምንጣፍ ተቀብለው የመረጃ እና ደህንነት ስልጠናውን እንዲያሰልጥን አደረጉት።
በስልጠናው ወቅት የነበረው ቆይታ፦
ዳዊት ተረፈ ወዳጆ ወይም ቃልኪዳን ግርማ የተሰጠውን ፀረ አማራ ሚሽን እየተወነ መሆኑን ጄኔራል አሳምነው ፅጌም ሆነ ሰልጣኞች ለመጥርጠር ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር።ሰውየው በማስልጠን ስም የአማራን ፖለቲካ እየሰለለ መሆኑን የሚያሳዩ ተግባሮችን ይፈፅም ነበር።ከተሰጠው ሚሽን አንዱ የአማራ ክልልን ፖለቲካዊ አመራር ከፀጥታ አመራሩ ጋር ማፋታት ወይም ማጋጨት ነበር። ይሄንን ለማድረግ መጀመሪያ ከጄኔራል አሳምነው እና ኮረኔል አለበል ጋር ግንኙነት ፈጠረ። በሁለቱ መካከል የነበረው መተሳሰብና ተግባብቶ መሥራት እየላላ እንዲሄድ አደረገ። በወቅቱ በጄኔራል አሳምነውና በኮረኔል አለበል መካከል የነበረው እንደ ወትሮው ተግባብቶ አለመሥራት ያሳሰባቸው ሰልጣኞች በስብሰባ ጭምር የተማፅኖ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ሰምቺያለሁ።
ዳዊት ተረፈ ወዳጆ በዚህ ሳያበቃ በዶ/ር አምባቸውና በጄኔራል አሳምነው ፅጌ መካከል የነበረው መተሳሰብ እየላላ እንዲሄድ አደረገ።በሁለቱ መካከል ልዩነቱን የሚያሰፋው በmisinformation and Diinformation techniques በመጠቀም ነበር።የጄኔራል አሳምነው ፅጌ የፀጥታ ጥበቃ ሁኔታ ደካማ መሆኑን ለማሳየት ባህርዳር ከተማ የተለያዩ ቤቶችን የማቃጠል ብሎም የዝርፊያ ኦፐሬሽኖችን ይሠራ ያሠራ ነበር።አንድ ቤት ተቃጠለ ሲባል ፈጥኖ እዛ ይደርስና መረጃዎችን በማሰረጨት የፖለቲካ አመራሩ እንዲደነግጥ ያደርጋል።ከዚያ በመቀጠል እንዲህ እየሆነ ያለው በጄኔራሉ ችግር ነው የሚል ስዕል በመፍጠር መቃቃሩ እንዲሰፋ ያደርጋል።
ሰልጣኞች በአማራ ትግል ወኔ እና ተስፋ አልባ የሚያደርጉ ነገሮች እየነገራቸው ስለተበሳጩ ዳዊት ተረፈ እንዲባረር ለጄኔራሉ ይነግሩታል።ጄኔራሉም ሁኔታው ስላላማረው ቢሮየ እንዳትገባ ከእኔም ጋር እንዳትገናኝ በማለው ተቆጥቶ ከቢሮ ያስወጣዋል። የደህንነት እና መረጃ ስልጠናው በበላይነት እንዲከታተል ኃላፊነት የተሰጠው ለኮረኔል አለበል ስለነበር ኮረኔል አለበል በንቀት መንፈስ ይሁን በበዛ ድፍረት ወይም በተለየ መቀራረብ ሰውየው ሳያባርርው ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ አደረገው። ቃልኪዳን ግርማ የተሰጠውን ተልዕኮ እንደጨረሰ ሲያረጋግጥ ከባህርዳር አዲስ አበባ ሄጃለሁ ብሎ ይጠፋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠልጣኞች ምረቃ ስነሥርዓት ይደርሳል። ከመቶ በላይ የመረጃ እና ደህንነት ሠልጣች ስልጠናቸውን በብቃት ጨርሰው ተመርቅው ወደ ሥራ በሚሠማሩበት ቀን የመንግስት ባለስልጣናት እንዲገኙ ጥሪ ይደረግላቸዋል።በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ አመራር ቃልኪዳን ግርማ በሠራው ሴራ አጠቃላይ የፀጥታ ቢሮ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በስጋት ስለሚያየው ሳይገኙ ይቀራሉ። በዚህም ለህዝብ ደህንነትና ሰላም ከልቡ የሚደክመው ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያዝናል።
ፅጥታ ቢሮው ሰፋ ባለ መልኩ ያሰልጠናቸው የልዩ ኃ ይል አባላትን ሲያስመርቅም ዶ/ር አምባቸው ቀርቶ አቶ ላቀ አያሌውና አቶ እዘዝ ዋሴ መገኘታቸው ከዚሁ የቃልኪዳን ሴራዊ ክዋኔ የተነሳ መሆኑን ምንጮች ተቁመዋል።ከዚሁ የልዩ ኃይሎች ምረቃ በኋላ እንቅልፍ ያጣው በኦነጉ አብይ አህመድ የሚመራ ማዕከላዊ መንግስት “መፈንቅለ አማራ መንግስት ” የማድረግ እቅዱን ወደ ተግባር ለመለውጥ የተጠና እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ። አብይ አህመድ የአዴፓን የፖለቲካ አመራሮች እየጠራ የክልሉ ፀጥታ ከቁጥጥራቸው እየወጣ እንደሆነ ይነግራቸዋል።በደሴ በተደረገው ስብሰባ የአማራ በጀት ለሚኒሻ ስልጠና እየዋለ ነው ሲል የጓዳ ሴራውን በአደባባይ እስከመናገር ደርሶ ነበር።በምድረ ገኝ፡በአጣየ፡በጃዊ፡በጎንደር እና በሌሎችም ቦታዎች በኦነጋዊያንና በትህነግ ቅንጅት የተደረጉ ወረራዎች በተሳካ ሁኔታ መመከታቸውን እንደወንጀል በመቁጠር የክስ መዓት ያዥጎደጉዱባቸው ነበር። በአብይ አህመድ አታላይ(decaptory ) ንግግሮች የተሸወደው የአዴፓ ፖለቲካ አመራር በቀጥታ ፍልሚያውን ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር ለማድረግ ይወስናል።
በአንድ በኩል ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከክልል እስከ ወረዳ ያለውን የፀጥታ አመራር ለማስተካከል ጥናት አስጠንቶ ለመተግበር ጫፍ ላይ ነው።በሌላ በኩል የፖለቲካ አመራሩ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ አመራር ጦርነት ሰባቂ ነው በሚል እየገመገሙት ነው።ከላይ እንዳልኩት በተለያየ ቦታ በትህነጎችና ኦነጎች የተደረጉ ትንኮሳዎች በብቃት መመከታቸው አሸላሚ ክንውኖች ሁሉ ለጄኔራሉ መክሰሻ ሆነው ቀርበዋል። ከሰኔ 15 ሀለት ቀናት ቀደም ብሎ አዲስ አበባ በተደረገው ግምገማ ሁሉም የፖለቲካ አመራር ይሄንኑ አቋም መያዙ ጄኔራሉን የባይታወርነትና የመከዳት ስሜት ውስጥ አስገብቶት እንደነበር የግምገማውን ሁኔታ ከራሱ ከጄኔራሉ የሰሙ ሰዎች ይናገራሉ።
በወቅቱ በነበረው አዴፓ ፖለቲካ የተከዳው ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ነው። የአዴፓ የፖለቲካ አመራር ጄኔራሉ እንዲክዱት ያደረገው በአብይ አህመድ እቅድ መሠረት ቃልኪዳን ግርማ በሚል ስሙ ከሰሞኑ ፍትኅ መፅሔት ሐተታ ዘሰኔ 15 ልብወለድ በሚመሰል ምናብ ያስነበበው ሰላይ ነው።ይህ ሰው ሰኔ 15 እንዲፈጠር ከመሥራቱም በላይ አሁንም ተደጋጋሚ ሰኔ 15 እንዲፈጠር ሥራ ላይ መሆኑን ብዙ ሰው የተረዳ አይመስለኝም።ቃልኪዳን ግርማ በጎጠኝነትና በስልጣን ጥም የሰከሩ ከአፍንጫቸው ሥር አርቅው ማየት የተሳናቸው እያዩ የማያዩ፡እየሰሙ የማይሰሙ፡ የኛው ጉዶችን ተጠቅሞ ፖለቲካዊ ሴራውን እየተወነ ይገኛል። ፍትኅ መፅሔት የዚህን ሰውየ ማንነት እያወቀች እንዴት ይሄንን ፀረ አማራ ሴራዊ ድርሰት ይዛ ልትወጣ ቻለች የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚፈልግ ነው። ሰውየው እስካሁን የት ነበር? ስለሰኔ 15 ለመናገር ለመፃፍስ ለምን 11 ወራትን ጠበቀ? መፃፉና መናገሩ እንዳለ ሆኖ ለምን በፍትኅ መፅሔት በኩል ሀሳቡን ማራመድ ፈለገ? የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅና ማወቅ ያስፈልጋል። ተመስገን ደሳለኝን ለመከላከል በሚል የአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ሲታወጅ በድንቁርናቸው እያገዛችሁ ያላችሁ ሰዎች ራሳችሁን ብትፈትሹ መልካም ይሆናል።
ሰኔ 15 የተፈፀመው መፈንቅለ አማራ መንግስት ራሳቸው በቅድሚያ እንዳስታወቁት በእነ አብይ አህመድ እቅድ በቃልኪዳን ግርማ ተልዕኮ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ይሄን ስንል አብይ ሲተኩስ አላየሁም እንዲያውም ያሻገረን እሱ ነው የሚል ጭንቅላቱ የቀነጨረ ከአፍንጫው ሥር አርቆ የማያስብ ውርንጫላ ጋር መግባባት እንደማይቻል አውቃለሁኝ። የሚያሳዝነው ግን በእነዚህ ማሰብ በተሳናቸው የኛው ጉዶች ሰኔ 15 እየተጎተተ ከእንደገና እየገባ መሆኑ ነው።የሚገርመው የሰኔ 15 ጎታቾች ራሳቸውን ነፃ ለማድረግ የሚሄዱበትን እርቀት ማየቴ ነው። የምታገናዝብና እየሆነ ያለውን የምትረዳ አማራ ሁሉ ጉዳዩን በትኩረት እንድትከታተለው አሳስባለሁ።
በቀንም ሆነ በሌሊት በአማራ ህዝብ ላይ በተለያየ ስም የሚደረግን ፖለቲካዊ ሴራ እንበጣጥሳለን።ይሄንን የምናደርገው ያለፈው እንዳይደገም የህዝባችንም ዘላቂ ሰላምና ጥቅም እንዲከበር ከመፈለግ ነው። ሽብርተኝነትን ማስቆም የሚቻለው አሸባሪዎችን በማሸበር ነው።For terorrism act counter terrorism is a legitnate and must to be done.
መውጫ፡
ሰኔ 15 አብይ ስለፈለገ ብቻ ሳይሆን ብአዴን ስለተቀበለው የተፈፀመ መፈንቅለ የአማራ መንግስት ነው። ብአዴን የተቀበለው በተንበርካኪነትና በጌታ ቅየራ ስልብ አስተሳሰብ ራሱን ሆኖ መቆም ባለመቻሉ ነው።ስለዚህ ሰኔ 15 በተግባር አፈፃፀሙን ስናየው መፈንቅለ አማራ መንግስት ቢሆንም ችግሩ ግን የብአዴን ቀውስ መሆኑን ማስመር ያስፈልጋል።ብአዴን ከጀኔራሉ ጋር ተስማምቶ በሩን ቢዘጋ ኖሮ ሰኔ 15 በፍፁም አይፈጠርም ነበር። ብአዴን ሳይጠፋ አማራ አይድንም የምንለው በስሜት ሳይሆን በእውቀትና በመረጃ ነው።ያኔም ሰኔ 15 እንዲፈፀም የሠሩት አሁንም ሰኔ15 እንዲመጣ የሚሠሩት ራሳቸው ብአዴኖችና ተከፋዮቹ ናቸው።
የአማራ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!!!