ተነስ አማራ
ምክር በጋራ


ካለፈው የቀጠ :- ያለፈው link

አለምአቀፋዊ የአማራ ግብረሀል

፫.አለምአቀፋዊ ግንኙነት(ዲፕሎማሲያዊ) ዘመቻ፤ማካሄድ

በዝህ ሙያ የተካኑ አያሌ አማሮች በመላው አለም፤እንደሚገኙ የታወቀ ነው።በመሆኑም
በጡረታ ላይ የሚገኙትን
በሥራ ላይ ያሉትን
በሙያው በትምህርት ላይ ያሉትና የአማራውን ወደጆች ያካተተ ስብስብ ፈጥሮ ዘመቻውን በተጠናና በታቀደ መልክ ማካሄድ ወሰኝነት አለው። ለምሳሌ የአባይ ወንዝ ጉዳይ ከአማራ ህልውና ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤የትግሉ አጋዥ ሊሆን ይችላል።

፬.አለምአቀፋዊ የአማራ የህግ ባለሙያወች ሥራ

ይህም ከላይ ከተጠቀሰው ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሊከናወን ይችላል።ዝርዝሩ ለባለመያወቹ ይተው።

ነገርን ነገር ያነሳዋልና ከሁለት አመታት በፊት ፤እዝሁ አፍንጫችን ሥር ሆነው የኦሮሞ፤ፅንፈኞች “ኢትዮጵያ መፈራረስ አለባት” ብለውና አማራውን አብጠልጥለው አዋጅ አስነግረው ዜና ከሆነ በኃላ ፤ተጯጩህን እንደነበረ የሚታወስ ነው።ይህ በራሱ የሚያሳየው ፤ያደረጃጀትን ፍቱንነት ነው።እነዝህ ከላይ የተዘረዘሩት ፤አለም አቀፉ የአማራ ግብረ ሀይል ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንጂ፤ሥራውን ከጀመረ በኋላ ሌሎች ተከታታዮች ይቀጥላሉ፤በተለይ በየአገሩ ያለውን የአማራ ወጣት ትውልድ በሚገባው ቋንቋ የማሰባሰቡ ነገር በብርቱ ሊታሰበበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

የሰኔ 15 ክስተት

ይህ ቀን ብዙ የጓጓንላቸውን ወንድሞቻችንን ያጣንበት መርገመት የሆነና የታሪክ ጠባሳችን ነው።ሀዘኑ የቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን የመላው አማራ ነው።ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማርልን።
ደማቸው በከንቱ ፈሶ ሊቀር አይገባም ። ቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆኑ አማራ ፍትሕ ማግኝት አለበት። “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ከሆነበት ሥርአት ፍትህን መሻት ሞኝነት ነው። ይሁንና የአማራ ሕዝብ፤የዳኝነት ጥበቡንና የዳበረ ሥርአተ ሽምግልናውን ተጠቅም የግዜ ጉዳይ እንጅ፤ፍትሕ እንደሚያመጣ ጥርጥር የለውም።
ከዚች ርጉም ቀን ጀምሮ ተጋግሎ የነበረው የአማራ ሕዝባዊ ትግል መቀዛቀዙን ማንም አይክድውም። ምክንያቱም ፤

ሀ.በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭም ያሉ የአማራ ጠላቶች ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመካሄዳቸው፤

ለ.ተጎጂው መላው አማራ ሕዝብ ሆኖ ሳለ፤ከተጋረጠበት የሕልውና አደጋ አንድ ሆኖ በአሸኔፊነት እንዳይወጣ፤አንዱን ሟች፤ሌላውን ገዳይ፤አንዱን አሳሪና አባራሪ፤ሌላውን ታሳሪና ተሳዳጅ በማድረግ(ከዝሁ ጋር በተያያዝ ፤የተገደሉ፤እስካሁንም ታሥረው የሚገኝ፤እየተሳደዱም ያሉ ብዘወች ናቸው) የረቀቀ አማራውን የመከፋፈል ሴራ በመጀመሩ ነው።

የአማራው ጠላቶች ይህንን መጥፎ ክስተት አሁንም የፖለቲካ መሳሪያቸው አድርገው መቀጠላቸው የማይቀር በመሆኑ መላው አማራ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

ከዝህ አስከከፊና ውስብስብ ሁኔታ እንዴት እንውጣ?

በየግዜው በአማራ የዜና አውታሮች፤ማህበራትና ድርጅቶች አማከኝነት እንዲሁም ግለሰቦች መግለጫወችና ተማፅኖወች በተደጋጋሚ እየተሰሙ ቢሆንም፤ለውጥ አላመጡም።በዝህ መልክ መቀጠሉም ፤ ከግዜ ወደ ግዜ እየተወሳሰበ በላው የኢትዮጵያ ሁኔታ፤የአማራውን ህልው የበለጠ አደጋ ላይ መጣል ስለሆነ ፤ ወደ ኋላ አንድ እርምጃ በመኽድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለ አማራ በሩን ዘግቶ መክሮ ፤ሶስት እርምጃ አመር የሚልበት. ሁኔታ መፈጠር አለበት።

በአገር ውስጥ

ከአገር ሽማግሎች፤ከእምነት አባቶች፤ከምሁራን ፤ከፋኖ፤ ከሴቶችና ከወጣቶች ማህበራት ፤የተወጣጣ፤ምክርቤት ተቋቆሞ፤ከሕዝብ ጋር መክሮ ፤በጥበብ ከዝህ ችግር የምንወጣበት ሁኔታ ሊፈጠር ይገባናል።

በውጭ አገር

በውጭ የምንኖር አማሮችና ትውልደ አማሮች፤ምንም እንኳ ከአገራችን በያሌ ሺ ኪሎሜትሮች ርቀን ብንገኛም ፤የወገናችን ጉዳይ የየእለቱ መነጋግሪያ አጃንዳችን እንደሆነ የማይካድ ነው ።ርቀን መኖራችን ከአካላዊ ጉዳት ብንድን እንጂ በወገኖቻችንን ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ ዘወትር እንዳሳሰብንና እንዳስቆጨን ነው።በአማራነት መደራጀት ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም ፤በብዛት ግን እንደ ችቦ እየተቀጣጠለ የመጣው ፤በግንባር ቀደምነት ታግሎ ለውጡን ያመጣው አማራ፤ ክህደት ከተፈጸብት በኋላ ነው።በአጭር ግዜ የተገኘው ለውጥ የማይናቅ ቢሆንም፤ከአደረጃጀት ድክመት የተነሳ አንዳንድ እንቅፋቶች መፈጠራቸው አልቀረም።ከነዝህም አንዱ ከሰኔ 15ቱ ክስተት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር ነው።ይህንንም በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡

1.በለየላቸው የአማራው ጠላቶች በረቀቀ መንገድ የሚደረገው አማራን የመከፋፈል ዘመቻ

2.ለጥቅምና ለዝና ሲሉ(ብዙ ተከታይ ለማግኝት)በሚንቀሳቀ የአማራ ማህበራዊ አንቂወች(አክቲቪስቶች) ነን ባዮች የሚደረግ መሰሪ ተግባር

3.አካባቢያዊ ልዩነቶቻችን ውበት ሆኖ ሳለ፤በተቃራኒ ቁመው በአውራጃዊ (ጎጠኝነት) ስሜት በሰከሩ ህዝብ አደንቋሪወች(አክቲቪስቶች) የሚደረግ አማራን የመከፋፈል እኩይ ተግባር ሌላው ፤ነው፤ ለዝህ አንዱም ማሳያቸው ፤ ወንድሞቻችን፤አንዱ “አማራ ሲጥል እንጂ ሲታገል አይታይም” የሚለውን ብሂል አስታውሶ “ሙያ በልብ ነው”ብሎ፤” ሌላው ተከበናል” እያለ የአማራውን የህልውና አደጋ እያሳየ ባለበት ሁኔታ ሁሉም ለአማራ ሲሉ መውደቃቸውን መላው አማራ አውቆት፤ ሟቾችም፤ሀዘንተኞችም እንኛው ሆነን ሳለ ፤የሟች ወንድሞቻችንን ፎቶ ለጥፈው፤አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ፤በማድረግ የሚርዙት መርዝ ነው።

ከዝህ እንዴት እንላቀቀ?

ልክ እንደ አገርቤቱ፤በውጭ ያላችሁ የእምነት አባቶች፤ሽማግሌወችና ምሁራን፤ጉባኤ አድርጋችሁ፤ ስለ ወንድሞቻችንን ቤተሰቦችና ስለ አማራው ስትሉ፤በግዝትም ሆነ በምክርና በግሳጼ፤አማሮች ነን ባይ ከፋፋዮችን አስቁሙልን።

ሌሎቻችንስ ምን እናድርግ?

እንደሞኝነትና የዋህነት ካልተቆጠረብኝ፤ የሚከተሉትን ብናደርግ በውጭ ያለውን የአማራ ትግል አንድ ርከን ከፍ አደረግነው ማላት ነው።

1.በግለሰብም ሆነ በስብስብ(በማህበር )፤የተጋጩ ቢኖሩ ፤ ለአማራ ህልውና ሲባል ስምምነት መፍጠርና በአንድነት መቆም፤

2.የወንድሞቻችንን ስም በከንቱ አለማንሳትና ፎቶወቻቸውንም ፤በሚከፋፍል ስሜት አንጠቀም፤ ከፋፋይከሆኑምአስተያየቶች፤እንቆጠብ፤የእስከዛሬው ይበቃል።

3.ከሰኔ 15 ጋር በተያያዘ፤በጽሁፍም ሆነ በፊልም ዘገባ ለማዘጋጀት በግልም ሆነ በቡድን የጀመሩና ያሰቡ ቢኖሩ፤ለአማራ እንድነት ቢችሉ ይተወት ወይም ላልተወሰነ ግዜ(ሁኔታወች እስኪሰክኑ) ያዘግዩት።

4.ተካፋይና ከፋፋዮቹን ለይተን በማወቅ እንራቃቸው፤ወይም ቋንቋቸውን የምታውቁ፤በሚገባቸው ሁኔታ አናግሯቸው፤ጠላት መምጫው አይታወቅምና፤አንዱ ሁሉም፤ሁሉም ለእንዱ ይቁም፤ሁላችንም ለአንድ አማራ እንቁም።

      አደረጃጀት እንዴት?

ዋናው ነገር የአላማ አንድነት ነው።አማሮች አሁን ካጋጠመን የሕልውና አደጋ በአሸናፊነት፤ለመወጣት ፤እስከዛሬ ከነበረው የአደረጃጀት ስልት መልካም መልካሙን በመውሰድ፤መሬት ላይ ወርዶ የሚታይ የአደረጃጀት ስልት መቀየርም ግድ ይለናል።ዝርዝሩ በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረግን ዘመቻና አደረጃጀት አስፈላጊነት፤ማናችንም አንስተውም፤ሆኖም ፤ይህ በተጨባጭ መሬት ላይ ወርዶ በ ተግባር ካልተደገፈ፤የአንድ ሰሞን ወሬ ይሆንና ግለቱ ቀዝቅዞ ፤ፍጥነቱ ይቀንሳል ወይም፤ይረሳል።ለዝህ መድሐኒቱ፤ወደ ጥንታዊ የአማራ፤ባህላዊና እምነት ነክ አደረጃጅቶች መመለስና እነዝህን ማዘመን ነው።ዝርዝሩ ይቆየን ።ቀደምቶቻችን፤አገራችንን ከነቋንቋ፤ነታሪክ፤ባህልና እምነት እንዴት አቆዩን?
ከዝሁ ርዕስ ጋር በተያያዘ እንድ ብርቱ ጉዳይ ላንሳ፤እሱም ከስድስት ወራት በላይ ታግተው ስለሚገኙት ተማሪወቻችን ጉዳይ ነው።
ዜናው እንደተሰራጨ፤በማሕበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ፍጥነት ተጧጡፎ የነበረውን የይፈቱልን ዘመቻ ስናስታውስ ፤በወር ወይም በእጭር ግዜ ውስጥ ይፈታሉ ብለን ተስፋ አድርገን የነበረ ስንቶቻችንን ነበርን?አሁንስ ምን እየተደረገ ነው?ወደፊትስ?
ይህ የሚያሳየን በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ የሚደረግ ዘመቻ፤”ላም አለኝ በሰማይ ወተተቷንም አላይ” ወደሚለው አባባል የሚወስድን መሆኑን ነው።
ነገር ግን የማህበራዊ ሚዲያውን አጋዥነት ተጠቅመን፤እያንድንዳችን በየቤታችንም ሆነ በየስብሰባ አዳራሾች መክረን ዘክረንበት፤ልዩ አልምአቀፋዊ ግብረ ሀይል፤አቋቁመን፤በባለሙያወች የተደገፈ ዘመቻ ጀምረን ቢሆን ኖሮ አማራውን፤ትውልደ አማራውን፤የአማራን ወዳጆችና የስብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችንንና ግለሰቦችን በማስተባበር ፤ብራስለሰንና ኒዮርክን በአካል ተገኝተን አጥለቅልቀን ቢሆን ኖሮ፤አንዲሁም፤በየምኖርባቸው አገሮች ያሉ መሪወችን (መንግስታትን) ያለማቋረጥ በራቸውን አንኳኩተን ቢሆን ኖሮ፤አንድ ተጨባጭ ነገር በተገኝ ነበር።የይፈቱልን ዘመቻችን በተቀነባበረና በተቀናጅ መልክ አልተካሄደም፤በኛው ውስጥ ተወስኖ ነው የቀረው ብል ያጋነንሁ አይመስለኝም።

ሁላችንም በየግላችንም ሆነ በቡድን በቁጭት በየአካባቢያችን መቻውን የጀመርንው ቢሆንም ፤የተቀናጀና የተቀነባበረ አለምአቀፋዊ ቅርርጽ እንዲኖረው አላደረግንውም።የናጄሪያ ሴት ወጣቶች በቦኮ ሀራም ታግትው በተወሰዱ ግዜ በአለም አቀፍ የዜና አውታሮች(BBC, Dochevele (የጀርመን ድምጽ) CNN ,ABC etc)የነበረውን ዘገባ እስቲ እናስታውስ፤ የኛወቹስ ታጋቾች ምን ያህል ትኩረት አግኝተዋል?ካልተዘገበስ ለምን?የናይጄሪያወቹ የይፍፈቱልን ዘመቻ እስክ ዋይት ሀውስ(White House) ደርሶ ፤ የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ባለቤት የሴት ልጆቻችንን አምጡልን(Bring our girls back)አለማቀፋዊ ዘመቻ የተጫወቱትን ሚና እናስታውሳለን።በአለም ላይ ተሰራጭቶ የሚገኘው የጠቢቡ አማራ ትውልድ እንዴት ከራሱ አልፎ አለምን ማንቃነቅ አቃተው? ቀደም ሲል የጠቀስሁት፤የአለማአቀፋዊ ተቋም አስፈላጊነት አንዱ ማሳያ ይህ ነው።የእንግሊዝኛ ጣቢያ ተቋቁሞ፤ቢሆን፤ኖሮ፤ዘገጋቢወቻቸው እንካ ባይመጡ፤ዘገባችንን ወደ እነሱ(አለም የዜና አውታሮች )በወሰድንው ነበር፤ወይም የአለም ህዝብ ፤በታገቱ ልጆቻችንን ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራው ላይ የተሰራውን ግፍ፤አሁንም እየተደረገ ያለውን ጭፍጨፍና የወደፊቱንም አደጋ ለማሳየት በታቻለ ነበር።
“ከተደበቁበት እስኪወጡ እንጠብቃለን” ወይም “የበላቸው ጅብ ይጮሀል” በሚለው፤የቀልድና የንቀት አነጋገር ከመቆጨት ይልቅ፤እማራ ወንዱ ቀበቶውን፤ሴቷ መቀነቷን ጠበቅ በማድረግ፤ካለፈ ስህተቶቻችን ተምረን፤በመቻቻልና በመማማል ቆርጠን ልንነሳ ይገባል፤”ድር ቢያበር አንበሳ ያሥር”ይሏልና።

ከፍያለው

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator