0
0
Read Time:42 Second
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ባነሱ የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ላይ መንግስታዊ አፈና ፈጽም ተብሎ ተመርጦ ስምሪት የተሰጠው የልዩ ኃይል ክፍል ተኩስ በመክፈት በፈጸመው ጥቃት የተገደሉ ወጣቶች ብዛት 7 መድረሱ ታውቋል።
ጥቃቱ የየፈጸመው ሰኔ 24/2014 ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ ስለመሆኑና በየአቅጣጫው እያሳደዱ በንጹሃን ላይ ይተኩሱ እንደነበር ተገልጧል።
የሸዋሮቢት ነዋሪዎች እንደሚሉት ለወለጋ የአማራ ሰማዕታት ድምጽ በመሆናቸው ብቻ ሰኔ 24/2014 በግፍ የታሰሩ ወጣቶች ይፈቱ ብሎ በሰላማዊ መልኩ መጠየቅ እስከ መገደል አድርሷል።
እስካሁን የሟቾች ቁጥር 7 መድረሱን የሚናገሩት የአሚማ ምንጮች የቆሰሉ ወጣቶችም በርካታ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ስርዓተ ቀብራቸውም ሰኔ 25/2014 እንደሚፈጸም ተገልጧል።
በግፍ ታስረዋል የተባሉት ወጣቶችም አሁንም እስር ላይ ናቸው።
ግድያ ከፈጸሙት የጸጥታ አካላት መካከል እስካሁን አንድም አካል በህግ ተጠያቂ የሆነ የለም።
ይህ ጥቃት ቀስ ብሎ በይፋት ፋኖ ላይ አፈና እና ትጥቅ ለመንጠቅ ለመሸጋገር እንደ መንደርደሪያ ለመጠቀም ታስቦ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።
About Post Author
Admin
Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF.
ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።