0 0
Read Time:2 Minute, 23 Second

በጌታቸው ሽፈራው

የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝባችን አስመትቷል ስንል የጠላትን ብቻ አይደለም። ኃላፊነት እያለባቸው ያለ አግባብ እንደፈለጉት ሲናገሩ የከረሙ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮችም ሕዝባችን አስመትተዋል።

የራሳቸውን ስራ መስራት ሲገባቸው በማያገባቸው እየገቡ በቀን አስር ጊዜ መግለጫ ሲሰጡ የከረሙ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ሕዝባችን አዘናግተው አስመትተውታል። አሁን ዳግመኛ ይህ ጥቃት እንዲደርስብን አንፈቅድም። ከስር እንደምታዩት ሌ/ጀ ባጫ ደበሌ ትህነግ የኢትዮጵያ ስጋት አልነበረም፣ አይሆንምም ብሏል። ይሄ ግልፅ ወንጀል ነው። ክህደት ነው!

1) እንዴት ነው አንድን ትልቅ፣ ያውም 80 በመቶ ከባድ መሳርያ የታጠቀ ሰራዊት የመታና ያገተ ቡድን የአገር ህልውና ስጋት ያልነበረው? ከዛ በላይ ምን ሊያደርግ ነው? የአገር ዘብ ነው የተባለ ሰራዊትን ከመምታት ውጭ ምን ሊያደርግ ነው? አንድ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራር ይሄን ፕሮፖጋንዳ መንዛቱ ክህደት ካልተባለ ምን ሊባል ነው?

2) የትግሬ ወራሪ ኃይል (ትህነግ) አማራና አፋርን ሲወር የፈፀመው ውድመትና ጭፍጨፋ ለእነ ባጫ አይታያቸው። ግድ የለም። የጅቡቲን መስመር ዘግቸ የኢትዮጵያን ጉሮሮ አንቃለሁ ያለ ቡድን ለኢትዮጵያ ስጋት አይደለም የሚባለው በምን መስፈርት ነው? ያውም በሰራዊቱ ከፍተኛ አመራር!

3) አማራ ክልልን ወደ 30 አመት ወደኋላ የጎተተ ቡድን ነው። የህክምና ተቋማትን፣ የትምህርት ተቋትን ወዘተ ሲዘርፍና ሲያወድም በሕዝብ ሕልውና ላይ ነው የመጣው። ከስጋት አልፎ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በርሃብ እየተሰቃየ ነው። በርካቶች ሞተዋል። ከዚህ አልፎ ወደ አማራ ከተሞችና አስመራ ሚሳኤል ሲተኩስ የነበረ ኃይል ነው። እንዴት ነው ይሄ ስጋት የማይሆነው?

4) በደባ የሰራዊቱን በርካታ መሳርያ ነጥቆ ያጠቃን ኃይል ነው። በሱዳን፣ በአፋር፣ በአማራ ክልል በርካታ አቅጣጫዎች ጦርነት የከፈተ ቡድን እንዴት ነው ስጋት የማይሆነው? በአገር ቤትም በውጭ አገርም እየዶለተ ያለ ቡድን እንዴት ነው ስጋት ያልሆነው? እንዴት ነው የኢትዮጵያ ስጋት የማይሆነው?

5) ላኪዎቹ ለኢትዮጵያ ስጋት ስለሆነ ነው የላኩት። የትህነግ ስጋት የሆነው አስተሳሰቡ ነው። ክፋቱ ነው፣ የሕዝብና የአገር ጠላት መሆኑ ነው። የውጭ ጠላቶች የመረጡት ይህን ለኢትዮጵያ ስጋት የሆነ ኃይል ነው። ስጋት የማይሆን ኃይል መርጠው ለማጥፋት ይልካሉ?

6)ተገንጣዮችን ሰብስቦ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ ያለ ቡድን ነው። ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚለው መፈክርም የመጣው ዝም ብሎ አይደለም። አዋጅ የታወጀው ዝም ብሎ አይደለም። ሁሉም ወደጦር ግንባር የተባለው ዝም ብሎ አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘምቻለሁ ያሉት እንዲሁ አይደለም። የአገርና የህዝብ አደጋ ስለሆነ ነው።

7) ከዚህ የደረሰውነው ባጫን ጨምሮ የመከላከያ አመራሮች፣ እንዲሁም ይህን ዜና የሚያሰራጩት የፓርቲ ሚዲያዎች የሚገባቸውን መስራት ባለመቻላቸው ነው። መንግስት በተለያዩ አንዳንዶቹ ከሕልውና አንፃር እርባና የሌላቸው ጉዳዮች ላይ ተጠምዶ እያዘናጋ ነው የተመታነው።

እንዴት ዛሬ ብቅ ብለው ስጋት አይደለም ይሉናል? ገና ከአፋርና ከአማራ ክልል ሳይወጣ ይህን የሚሉ ሰዎች ክህደት እንደሰሩ መታወቅ አለበት። ወንጀል ነው።

8) እንደ አማራ ሕዝብ ደግሞ የህለውና ጉዳይ መሆኑ ታምኖበታል። አንድም ይሁን ሁለት ሰው ቢቀር እንኳን የትህነግ አስተሳሰብ በባሕሪው ፀረ አማራና አማራን ካላጠፋሁ የሚል ነው።

ገና ማንፌስቶ ሲቀርፅ ጀምሮ ስጋት ነው ተብሎ የሚታመንበት ነው። ታዲያ ስራቸውን በአግባቡ ያላከናወኑ ሰዎች ከየትም መጥተው ትህነግ ስጋት እንዳልሆነ ይነግሩናል። ክህደት ደግሞ ወንጀል ነው!

ትህነግ ስጋት ስለሆነ የአማራ አርሶ አደር ሰብል ስብሰባውን ትቶ ዘምቷል። ትህነግ ስጋት ስለሆነ አማራ ክልል ስራ ቆሞ ሁሉም ወደጦርነት ተብሏል። ትህነግ ወቅታዊ ብቻ አይደለም የህልውና ስጋታችን ነው። እናንተ ደጋግማችሁ በተሳሳታችሁ ቁጥር ሕዝባችን ዳግም እንዲወጋ አንፈቅድም። ማንም ሞቅ ሲለው የተናገረውን እየወሰዳችሁ የምትለጥፉ ሚዲያዎችም ልታፍሩ ይገባል። በጦርነቱ መሃል ላለመጨቃጨቅ እንጅ ስህተቶች ስለሌሉ አይደለም። ሞልተዋል።

ትህነግ ስጋቴ ነው ብሎ ደሙን እየሰጠ ያለ አካል አለ። አይደለም የሚሉ ከፈለጉ ገለል ይበሉ። በተደጋጋሚ በሚፈጥሩት ስህተት ደጋግመው እንዲያስመቱን አንፈቅድም። ይበቃል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator