በተንታ ወረዳ የፋኖ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በቀን 16/07/2014ዓ.ም ከጧቱ 12:20 ላይ በስልጠና ቦታ እያሉ በወረዳው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊና በሚኒሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አዛዥነት እስሩ እንደተፈፀመባቸው ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የታሰሩትም በቁጥር 12 ሲሆኑ ስማቸውም:_
1.ታድሷል ታምሬ/አሰልጣኝ፣
2.ምሳየ ጌታነህ/አሰልጣኝ፣
3.ብርሀነ ገብረ መስቀል፣
4.ቴዲ ብርሀኑ፣
5.ሙሀመድ ካሳ፣
6.ፈርሀት ኑርየ፣
7.አዲሱ ተፈራ፣
8.አብዱ ሙሀመድ፣
9.ሙሀመድ በሽር፣
10.መኮንን ዋስየ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ከዚህ በፊት ፋኖ አትሰለጥኑም በማለት በወረዳው መታሰራቸው ይታወሳል።
ይህ ድርጊት ሲፈፀም ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
አሁንም እስር ቤት የሚገኙ ሲሆን “ከእስር የምንለቃችሁ ከዚህ በኋላ ፋኖ አንሰለጥንም ብላችሁ ከፈረማችሁ ብቻ ነው” ተብለዋል።
ለቀረበላቸው ጥያቄም የታሰሩት ፋኖዎች “አንፈርምም፣ እንሰለጥናልም” የሞል ምላሽ ሰጥተዋል።
የወረዳው ፖሊስ ሀላፊ እንግዳውስ “ከእስር አትፈቱም እርምጃም ይወሰድባችኋል” በማለት እየዛቱባቸው መሆኑና በእስር ላይ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
መረጃው የደቡብ ወሎ ፋኖ አስተባባሪ የአቶ ኤርሚያስ አያሌው ነው።