የባልደራሱ ፍቅረ ማርያም ሙላቱ በድጋሜ ታሰረ፣ ሌሎች አባላትም እየተዋከቡ ናቸው!
“ፖሊስ ሊያስተናግደን ፈቃደኛ አይደለም” የብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት!
/
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባል የሆነው ወጣት ፍቅረ ማርያም ሙላቱ ከመኖሪያ ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። ፍቅረ ማርያም በአድዋና ካራ ማራ የድል በዓላት ምክንዬያት በግፍ ታስረው ከቆዩት የባልደራስ ከባላት መካከል አንዱ ነው።
ሌሎች የባልደራስ አባላትም(በተለይም በአድዋና በካራማራ ታስረው የነበሩ ወጣቶች) ማዋከብ ተጀምሯል።
በተያያዘ፤ በቅርቡ ከአማራ ልዩ ሃይል አዛዥነት የተባረሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአዲስ አበባ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ተናግረዋል።
፣በየፖሊስ ጣቢያው ተዘዋውረው የጠየቁት መነን “ፖሊስ ሊያስተናግደን ፈቃደኛ አይደለም። እንኳንስ ‘አሉ’ ብሎ ሊያገናኘን እንዲፈለግልን ለማስመዝገብም ፈቃደኛ አልሆነም። እንዲህ አይነት ጉዳይ አናስተናግድም” ነው የሚሉት ብለዋል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ በተለያዩ ጣቢያዎች ሄደው መጠየቃቸውንም ገልፀዋል።
ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ትናንት ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ አምስት ሰዓት ገደማ ከቤት ሲወጡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚታወቅ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ወዳጃቸው ጋር በግል ጉዳይ ለመገናኘት እንደሆነም ባለቤታቸው አረጋግጠዋል። ከእኒኝ ወዳጃቸው ጋር ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ መለያየታቸውም ታውቋል።
ብርጋዴር ጀኔራሉ ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የአገዛዙን ገመናዎች ለአደባባይ አብቅተዋል።
/