በአማራ ክልል ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ የሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቆሬ ሜዳ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ታጣቂዎች ወድሟል።
የኢፕድ ዘጋቢዎች በስፍራው ተገኝተው እንደተመለከቱት ቤተክርስቲያኑ አገልግሎት መስጠት እንዳይችል ሆኖ ፈራርሷል።
የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም በፈጸሙት የከባድ መሳሪያ ድብደባ ቤተክርስቲያኑ በዚህ መልክ ፈራርሷል።