1 0
Read Time:2 Minute, 48 Second

June 2, 2022
ግንቦት 26 2014 ዓ.ም

ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የዛሬ 31 ዓመት በውጭ ፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች እገዛ ኢትዮጵያን የተቆጣጠሩት ትህነግና ኦነግ፣ አማራ ያልሆኑና በአማራ ጥላቻ የሰከሩ አማርኛ ተናጋሪ ግለሰቦቸን በመሰብሰብ ብአዴን የሚባል ፀረ አማራ አደረጃጀት ፈጠሩ። ያለአማራው ሁነኛ ተሳትፎ የተፈጠረው ብአዴን በአማራው ማህበረሰብ ላይ ከተጫነ በኋላ የሆነኝ ብሎ አማራው የራሱን አደረጃጀት እንዳይፈጥር፤ የደህንነትና የኢኮኖሚ ተቋሞችን እንዳይገነባና እራሱን ከታቀደለት የመጥፋት እቅድ እንዳይከላከል በማድረጉ ዛሬ ላይ ለሚፈፀምበት የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ሰለባ አድርጎታል።

በፖሊሲ በስትራቴጅ እና በህግ የታጀበው መዋቅራዊ አማራን የማዳከም እና የማጥፋት ወንጀል ካለፉት31 ዓመታት ጀምሮ በብአዴን ፈጻሚነት በአማራው ሕዝብ ላይ ህወሃት አማራ ክልል ብሎ በከለለው ግዛትም ጭምር በስፋት እየተፈጸመበት ይገኛል።

የፀረ- አማራው ፖለቲካ ገና እየጎመራ እንደሚሄድ ትንቢተኛው ጀኔራል አሳምነው ፅጌን ጨምሮ ብዙወች የቀደሙት የአማራ ጀግኖች ያቃጨሉት የማንቂያ ደወል ሁነኛ ሰሚ እና ፈፃሚ ባለማግኘቱ ከምዕተ ዓመታት በፊት (በ16ኛ መቶ ክፍለዘመን) የተፈጸመውን ወረራ እና እልቂት የሚመስል “ድምፅ አልባ” የዘር ፍጅት እና ወረራ በአማራው ላይ እየተፈፀመ ይገኛል።

የዘመኑ ገዥ ኃይል ይህንን ወረራ እና የዘር ፍጅት ከግብ ለማድረስ ያመቸው ዘንድ የማንቂያ ደውሉን የሰሙት እና አማራን ነፃ የሚያወጣው ራስን የማደራጀት፣ የመሰልጠን እና የመከላከል ትግል መሆኑን ተገንዝቦ እየተገበረ ያለውን የአማራ ፋኖ ማሳደድ፣ ማፈን እና መግደል ከጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል። በብአዴን አደግዳጊነት እና ጠቋሚነት እና ተባባሪነት በኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች በህግ ማስከበር ስም የተጀመረው ወረራ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር እና አባላትን ጨምሮ ሁሉንም የፋኖ አደረጃጀቶች ዒላማ ያደረገ ነው።

ብርቅዬ ፋኖዎችን በመደምሰስ እና የፋኖ አደረጃጀቶችን በመበተን የአማራን ማህበረሰብ መሪ አልባ ለማድረግ እና በህዝቡ ላይ ፖለቲካዊ እጥበት ለመፈፀም የታቀደው ይህ የጥፋት ፕሮጀክት ዋነኛ ባለቤቱ ሌላ ቢሆንም ያለ ብአዴን ተሳትፎ እና ፈፃሚነት የሚሳካ እንዳልሆነ ይታወቃል።

የአማራ ምሁራንን፣ የእምነት አባቶችን፣ የጦር መኮንኖቻችንን፣ የማህበረሰብ አንቂዎችን (አክቲቪስቶችን)፣ ጋዜጠኞችን እና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጭምር ዒላማ ያደረገው ጥቃት ያለፍርድ ቤት እውቅና መግደልን፣ ማሰርን፣ ከሥራ በማገድ ቤተሰቡን ለረሃብ ማጋለጥን ጭምር ያካተተ ነው።

ዘርፈ-ብዙ የሆነው ጥቃት የአማራውን ገበሬ ከሌሎች ክልሎች በተለዬ ሁኔታ አንድ ኩንታል ማዳበሪያ እስከ ብር 5000 እንዲገዛ በማድረግ እሱንም ቅድሚያ ለሚሊሻው እና ለአገልጋዮቻቸው ብቻ እንዲሸጥላቸው በማድረግ ህዝቡ በኢኮኖሚ እንዲደቆስ እያደረገው ይገኛል።

በአሁኑ ሰዓት በብአዴን መሪነት፣ በከሃዲው ጀኔራል አበባው ታደሰ የበላይ አስተባባሪነት የሚከናወነው እና ከአማራ ክልልም የተለዩ አካባቢወችን ታሳቢ ያደረገው የዚህ ዘመቻና ጭፍጨፋ መዳረሻ ግቡ ኦሮሚያ የሚባል አገር ለመመሥረት ካልሆነም ኢትዮጵያን በኦሮሙማ መልክ እንደገና አፍርሶ ለመስራት ስለሆነ ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀል አድማሱን በማስፋት በሲዳማ፣ በጌዲዮና በሌሎች የደቡብ ክልል ብሔሮች ላይ እንደሚፈፀም ሳይታለም የተፈታ ነው።

ስለሆነም ለአማራ ሕዝብና ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚከተለው የትግል ጥሪ እናቀርባለን፦

1/ ከስህተቱ የመማርን ተደጋጋሚ እድል ያባከነው ብአዴን በስልጣን ላይ በሚቆይባቸው እያንዳንዱ ቀናት ውጤቱ ጥፋት በመሆኑ ብአዴን ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ የሚያስገድድ ሁሉን አቀፍ ትግል እንዲደረግ፥

2/ ሁሉም የፋኖ አደረጃጀት በተጠና እና በተናበበ መንገድ ራሱን እና አመራሮችን ከመጥፋት መታደግ የሚያስችል እና የዘማች እና አዝማቹን ቅስም የሚሰብር መራር ተጋድሎ እንዲያደርግ፥

3/ መላው የአማራ አርሶ አደር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር እንዳያገኝ በማድረግ የታወጀበትን የርሃብ ጥቃት ከወዲሁ ማክሸፍ ይቻል ዘንድ ትላንት ለህልውናው እና ለነፃነቱ ከተዋደቁለት ልጆቹ እና የፋኖ አደርጃጀቶች ጎን በመቆም ታሪካዊ ተጋድሎ እንዲያደርግ፥

4/ ሁሉም የአማራ ፖለቲካዊ ኃይሎች ነባሮቹ የአማራ ጠላቶች ህወሃት እና ኦነግ ታሪካቸውን እና ግብራቸውን አድሰው በአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥቅሞች ላይ እየተደራደሩ በመሆኑ የ1983 ታሪካዊ የፖለቲካ ሸፍጥ ተደግሞ ህዝባችን ለሌላ ዘመን ባርነት ፣ ጭቆና እና የህልውና አደጋ ከመጋለጡ በፊት ከፋኖ እና ከሌሎች የአማራ አንቂወች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ጎን ተሰልፎ በማናቸውም መንገድ ርብርብ እንዲያደርግ፥

5/ በመጨረሻም የተጀመረው ዘመቻ በዘረኛው የአብይ አህመድ መንግሥት በፖሊሲ ደረጃ የተቀረፀ መሆኑ ታውቆ ህዝቡ እንደአማራ ከመጥፋቱ በፊት በሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለሥር ነቀል ለውጥ የታለመ መራራ ትግል እንዲደረግ አስቸኳይ ዝግጅት እንዲደረግ ጥሪ እናስተላለፋለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ
ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰሜን አሜሪካ

PDF Download

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator