0 0
Read Time:1 Minute, 31 Second

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በጋዜጠኞች፣በተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እና በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ህገወጥ እስር እና አፈና እየተፈጸመ ይገኛል ሲል ኢሰመጉ ገልጧል።

ኢሰመጉም ይህንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እና ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች መንግስት የእርምት እርምጃዎችን አንዲወስድ ሲወተውት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ይህ ሕገወጥ እርምጃ በመንግስት በኩል አሁንም እንደቀጠለ ነው ብሏል።

እንደአብነትም የፍትህ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ከቢሮው በጸጥታ ሀይሎች ተወስዶ መታሰሩን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ስለመቻሉ አስታውቋል።

በተጨማሪም 7 የሚሆኑ የአሻራ እና የንስር ዩቲዩብ ሚዲያ ጋዜጠኞች ባሳለፍነዉ ሳምንት ከራ ቦታቸዉ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተያዙ ሲሆን የት እንደሚገኙ ሳይታወቅ የቆየ ቢሆንም ይህ መግለጫ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ኢሰመጉ ባገኘው መረጃ መሰረት ደቡብ ጎንደር ጋይንት ታስረዉ እንደሚገኙ ነገር ግን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ለመረዳት ተችሏል ብሏል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከግቦት 2014 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት ህግ ማስከበር ዘመቻ በሚል ከ 4500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መግለጹ የሚታወስ ነው።

ይህንንም ተከትሎ ኢሰመጉ ባሰባሰባቸው መረጃዎች በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ እስሮች ተገቢውን የህግ ስነ ስርአት ያልተከተሉ እና እገታም የታከለባቸው መሆናቸውን ለመረዳት ችሏል።

በተጨማሪም በዚህ ሂደት በተፈጠሩ ግጭቶች እና በተወሰዱ እርምጃዎች በክልሉ በሚገኙ አካቢዎች ማለትም በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ፣ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ሞት (የ13 አመት ታዳጊን ጨምሮ)፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣እስራት እና እገታ መፈጸሙን ኢሰመጉ ገልጧል።

ተገቢውን የህግ ሂደት ሳይከተል በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እየታሰሩና እየታገቱ እንደሚገኙ ከነዚህም መካከል በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ ፣ የእናት ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዲሁም የሌሎችም ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንደሚገኙበት አክሎ ገልጧል።

በፓርቲዎች አባላት አና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስር በመንግስት አካላት የሚፈጸም የእገታ ድርጊት መሆኑን እና ይህንንም ተከትሎ አብዛኛው እየታገቱ ያሉ ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ እና ፍርድ ቤትም እየቀረቡ አለመሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል ሲል አስታውቋል።

PDF view

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator