አፋኙ ቡድን ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን ፍለጋ እነብሴ እና ጎንቻ እየዞረ እንደሆነ ተሰማ።
ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል ባጋራው መልዕክቱ
አፋኙ ቡድን ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን ፍለጋ እነብሴ እና ጎንቻ እየዞረ እንደሆነ ተሰምቷል ይለናል።
ሙሉ መልዕክቱ ይህ ነው:_
ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ በህልውና ዘመቻው ከAPF ምስረታ አስቀድሞ ከእነ ገዱ አንዳርጋቸው እና ላቀ አያሌው ጋር የልዩ ኃይል ስልጠናወችን እና የምሊሻ ምልመላውን ሲያስተባብር ነበር።
ቆይቶም ከምሊሻው ጋር ዘምቷል። ግምባር ላይ እያለም ከነ ምሬ ወዳጆ ጋር የወሎን ፋኖ አደራጅቷል። ይህን ሁሉ ሲሆን የብልፅግና አመራሮች አብረውት ነበሩ።
ዛሬ ካፕቴኑን ለማፈን የተላከውን ጦርም የሚመሩት እነኝህ አመራሮች ናቸው።
ህወሃት እንደ ማስረሻ የበደለው ሰው የለም። ማስረሻም እንደ ህወሃት የሚጠላው የፖለቲካ ኃይል የለም።
የእንቆቅልሹን ፍች የሚያውቁት ህወሃትን ልንዋጋ ስለሆነ አስቀድመን እነ ማስረሻን እናጥፋ የሚለውን ፕሮጀክት የነደፉት ብቻ ናቸው።