አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የጥፋት አጋሮቹ በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ወረዳ በመንጋ ተሰባስበው የአማራዎችን የጤፍ ክምር እና የመኖሪያ ቤት እያቃጠሉ ነው።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ወረዳ በመንጋ ተሰባስበው የአማራዎችን የጤፍ ክምር እና የመኖሪያ ቤቶችን እየለዩ በማቃጠል የወንጀል ድርጊታቸው ቀጥለውበታል።

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የሰፈር ምልምሎቹ ከቀናት በፊት ጀምሮ ከ24 በላይ የጤፍ ክምር አቃጥለዋል።

ህዳር አጋማሽ 2014 ባሪ አቦ በተባለ ቀበሌ ከ30 በላይ የአማራ ቤቶችን አቃጥለዋል።

ሰምቦ ጤጆ ቀበሌ ለገያ፣ኢዲ፣ግሼ እንዲሁም በአኖ ወረዳ ሀሪማሞ አካባቢ የንብረት ዝርፊያ በስፋት እየፈጸሙ ነው።

በተያያዘ መሀመድ የተባለ በሞባይል ጥገና ሙያ የሚስተዳደር የባኮ ነዋሪ በአማራዊ ማንነቱ በባጃጅ ሲጓዝ ታፍኖ ከተወሰደ አንድ ሳምንት ያለፈው ሲሆን ባለባጃጁ በእስር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator